የዩክሬን ወታደሮች ሩሲያ 'ቀስ በቀስ እያሸነፈች ነው' አሉ

የፎቶው ባለመብት, BBC/GOKTAY KORALTAN
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ “ጠንካራ ይዞታ” እየሉ በሚጠሯት እና በምስራቂ የአገሪቱ ክፍል የምትገኘውን ባክሙት ከተማ ለመያዝ የሩሲያ ጦር የሚያደርገውን ጥረት አጠናከረ።
ይህቺን ከተማ ለመቆጣጠር ስድስት ወር የፈጀ ሙከራ ስታደርግ የቆየችው ሞስኮ አሁን ላይ የበለጠ በአከባቢው ጧሯን አጠናክራለች።
ከዜሮ በታች የሆነ ቅዝቃዜ የሚመዘገብባት ባክሙት፤ የከተማ ውጊያና እየተካሄደ ቢገኝም እስካሁን ድረስ በዩክሬን ኃየሎች ቁጥጥር ሰር ትገኛለች።
ይሁን እንጂ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ወታደራዊ ዘመቻ ከአንድ ዓመት መታሰቢያ በፊት ከተማዋን የመያዝ ዕቅድ እንዳላት ዩክሬናውያን ይገልጻሉ።
93ኛው ብርጌድ የፕሬስ ኃላፊ የሆነው ኢራያ ሩሲያ ከተማዋን ለመቆጣጠር ከባለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ ስትሞክር እንደነበር ይገልጻል።
“ቀስ በቀስ እያሸነፉ ነው። ብዙ መሳሪያ አላቸው ስለዚህ ውጊያውን አራዝመው ከቀጠሉ ያሸንፋሉ። ያ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ መገመት ግን ይከብዳል። ተስፋ የማደረግው ምን አልባት መሳሪያ እንዲያጥራቸው ነው" ብሏል።
በአከባቢው የሚዋጋውና የዩክሬን 93ኛ ብርጌድ አባል የሆነው ካፒቴን ማይኪሎ ጦሩ የጥይት እጥረት እንዳጋጠመው ይናገራል።
“ሊጠለፍ የማይችል የግኙነት መሳሪያና ወታደሮቻችን የምናመላልሰበት ብረት ለበስ ተሽከርካሪ ከምዕራባውያን አጋሮቻችን እንፈለጋለን። እጥረት ቢኖርም ግን አሁንም እየተዋጋን ነው። ከዚህ ጦርነት ያገኘነው አንዱ ትምህርት በትንሽ ሃብት እንዴት መዋጋት እንደሚቻል ነው” ሲል አክሏል።
ከባድ ጦርነት እያስተናገድች የምትገኘው ባክሙት በጥይት እሩምታዎች እና ጭስ ታፈናለች። የሩሲያ ጦር ቀስ በቀስ በአካቢው ያለውን ቁጥጥር እያሰደገ ነው። ቅጥረኞቹ የዋግነር ወታደሮች በዚህ አከባቢ መሰማራተቸውም ተሰምቷል።
ሞስኮ የባክሙንን ሁለት ዋና ዋና መንገዶች በቁጥጥሯ ስር ያዋለች ሲሆን አንድ መጋቢ መንገድ ብቻ የአቅርቦት መስመር ሆኖ በዩክሬን ቁጥጥር ሥር ይገኛል።
በከተማው የብረት ለበስ ጦር አዛዥ የሆነው ኢሆር “እየከበቡን ከተማውን ለቀን እንድንወጣ እየሞከሩ ነው። ያ ግን አልሰራም። በከፍተኛ የአየር ደብደባ ውስጥ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ቀጥሏል። በእረግጥ ኪሰራ ገጥሞና፣ ግን እጅ አልሰጠንም። ወድ ድል መጓዝ ያለን ብቸኛ አማራጭ ነው” ብሏል።
ከባክሙት ሳይረፍድ አፈግፍጎ የመውጣት አማራጭ ቢኖርም ወታደሮቹ ግን ያንን ለማድረግ ፍላጎቱ ያላቸው አይመስለም።
ካፒቴን ማይሂሎ “ከዋናው መስሪያ ቤት እንደውንወጣ ከተነገረን እናደርገወለን፤ ትዕዛዝ ትዕዛዝ ነው። ለመፈግፈግ ከሆነ ግን ይህን ሁሉ ወር እዚህ ለምን ቆየን?” ሲል ይጠይቃል።
ካፒቴን ማይሂሎ ከተማዋን ለማስጠበቅ “ሀገራቸውን የሚወዱ በርካታ ሰዎች ” እንደተገደሉም አስታውሷል።
በባክሙት ያሉ ወታደሮች የሚወጡ ከሆነ ሩሲያ በምራቃዊ ዩክሬንን ያሉ እንደ ካራማራቶርስና ስሎቫያንስክ ያሉ ትልልቅ ከተሞች እንድትይዝ መንገድ ይከፍታል።
የሩሲያ ጦር በምስራቃዊና ደቡባዊ ዩክሬን በሚገኙ ሌሎች የጦር ግንባሮች ላይ የሚያደርሰው ጥቃት እየጨመረ ይገኛል። ዩክሬንም የሩሲያ አዲስ ጥቃት እየጨመረ መሆኑን ገልጻለች።
ክሬምሊን ዩክሬን የተወረረችበትን አንድ ዓመት እየጠበቀች ነው።
“‘የድል ቀን’ ብለው እየተዘጋጁ ነው” ይላል ካፒቴን ማይካሂሎ።
ከተማዋ የማያቋርጥ የፍንዳታ ድምጽ በብርሃን ቢሞላትም የሕይወት እንቅስቃሴዎች ቀጥለዋል።












