ከ12 ሚስቶች 102 ልጆች የወለዱት አባት የቤተሰብ ዕቅድ ለመጠቀም ወሰኑ
ከ12 ሚስቶች 102 ልጆች የወለዱት አባት የቤተሰብ ዕቅድ ለመጠቀም ወሰኑ
ሙሳ ሃሳህያ ኡጋንዳ ውስጥ በአንዲት የገጠር መንደር ውስጥ ይኖራሉ። 12 ሚስቶች እና 102 ልጆች አሏቸው። የልጅ ልጆቻቸውም 578 ደርሰዋል።
የልጆቻቸውን ስም ማስታወስ ስለማይችሉ የስም መጻፊያ ዝርዝር አዘጋጅተዋል። የልጆቻቸው ቁጥር ስለበዛባቸው የ68 ዓመቱ አዛውንት አሁን ሚስቶቻቸው የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት እንዲጠቀሙ አድርገዋል።
በኡጋንዳ ከአንዲት በላይ ሚስት ማግባት በሕግ የተፈቀደ ነው። ሙሳ ይህንን ሁሉ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩት በሁለቱ ሄክታር መሬት ብቻ ነው።
አሁን ግን የሁሉንም ልጆቻቸውን እና ሚስቶቻቸውን ፍላጎት ማሟላት “ከብዶኛል” እያሉ ነው።



