በፓኪስታን በአንድ እስላማዊ የፖለቲካ ሰልፍ ላይ በደረሰ ፍንዳታ 44 ሰዎች ተገደሉ

በፓኪስታን አንድ እስላማዊ ፓርቲ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 44 ሰዎች ተገደሉ።

ጄዩአይ-ኤፍ የተሰኘው ፓርቲ በሰሜን ምዕራብ ባጃውር ግዛት ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ በደረሰው ፍንዳታ ከ100 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ፖሊስ ለቢቢሲ እንደገለጠው ፍንዳታው የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁም ማስረጃ አለ።

የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሥራቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን በፍንዳታው ጉዳት የደረሰባቸው በሙሉ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

ባለሥልጣናት የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ገልጠው 15 ሰዎች በጠና ተጎድተው አስጊ ሁኔታ ላይ ናቸው ብለዋል።

ጥቃት የደረሰበት ምክንያት እስካሁን አልታወቀም። የደኅንነት ሰዎች አደጋ የደረሰበት ሥፍራ አጥረው ምርመራ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በመቶወች የሚቆጠሩ ሰዎች የፓርቲውን እሑድ ዕለት ኻር በምትባለው ከአፍጋኒስታን ድንበር ብዙ በማትርቀው ከተማ እየታደሙ ነበር።

ምስሎች እንደሚያሳዩት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፍንዳታው ከመድረኩ አቅራቢያ ሲፈንዳ አንድ ዳስ ውስጥ ነበሩ።

በፓኪስታን አንድ እስላማዊ ፓርቲ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 44 ሰዎች ተገደሉ።

ጄዩአይ-ኤፍ የተሰነው ፓርቲ በሰሜን ምዕራብ ባጃውር ግዛት ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ በደረሰው ፍንዳታ ከ100 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።