ቶተንሃም ከቼልሲ፤ ሊቨርፑል ከአስቶን ቪላ... የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶች

አስረኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ቅዳሜ፣ እሑድ እና ሰኞ እንዲከናወኑ መርሐ ግብር ወጥቶላቸዋል።
ሰባት ጨዋታዎች ቅዳሜ፤ ሁለት ጨዋታዎች እሑድ ቀሪው የሳምንቱ ጨዋታ ሰኞ ይካሄዳሉ።
ቶተንሃም ሆትስፐር በሜዳው ቼልሲን ሲያስተናግድ በተመሳሳይ ቅዳሜ ዕለት ሊቨርፑል አንፊልድ ላይ አስቶን ቪላን የሚያስተናግዱበት ጨዋታዎች ተጠባቂ ናቸው።
የእነዚህን ጨምሮ የቀሪዎቹን ጨዋታዎች የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ልሪስ ሱተን እንደሚከተለው ገምቷል።
ቅዳሜ
ብራይተን ከ ሊድስ
ሊድስ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ከተመለሰ በኋላ ጥሩ አጀማመር አሳይቷል።
በአርሴናል ከደረሰባቸው ከባድ ሽንፈት ውጭ ጥሩ ተፎካካሪ ለመሆን ችለዋል።
ይህንን ጨዋታ ግን ብራይትን እንደሚያሽንፍ እገምታለሁ።
ቡድኑ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ጥሩ ካለመጫወቱም በላይ ከካራባኦ ዋንጫ በአርሴናልም ቢሸነፉም በሜዳቸው ሽንፈት አላስተናገዱም።
ግምት፡ 2 - 0

በርንሌይ ከ አርሴናል
አርሴናል ጨዋታዎችን በተለያዩ መንገዶች ማሸነፍ መቻሉ ሊጉን እንዲመሩ አስችሏቸዋል።
ጥሩ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆኑ በቆሙ ኳሶችም ጎሎችን ማስቆጠር ይችላሉ።
በርንሌይ ጥሩ መፎካከር መቻሉን ከሊቨርፑል እና ማንቸስተር ሲቲ ጋር አሳይቷል።
በዚህ ጨዋታም ፉክክር እንደሚያደርጉ ብጠብቅም ጨዋታውን መድፈኞቹ ያሽንፋሉ።
ግምት፡ 0 - 1
ክሪስታል ፓላስ ከ ብሬንትፎርድ
ሁለቱም ቡድኖች በሊጉ አጋማሽ ላይ የሚገኙ ሲሆን በካራባኦ ዋንጫ ጨዋታም አሸንፈዋል።
ብሬንትፎርድ ያለ ብሪያን ምቡሞ እና ዮአን ዊሳ ተፎካካሪ መሆን እንደሚችል ለማሳየት እየሞከረ ነው።
ሁለቱም ቡድኖች በመልሶ ማጥቃት መጫወትን የሚመርጡ በመሆናቸው ለማየት የሚያጓጓ ጨዋታ ይሆናል።
ግምት፡ 1 - 0
ፉልሃም ከ ዎልቭስ
ዎልቭስ አንድም ጨዋታ ሳያሸንፍ በሊጉ ግርጌ ላይ ተቀምጧል።
ፉልሃምም አራት ተከታታይ ጨዋታዎችን ተሸንፎ ከባድ ጊዜ እያሳለፈ በመሆኑ ለሁለቱም ቡድኖች ወሳኝ ጨዋታ ይሆናል።
ዎልቭስ በርካታ ጎሎችን ማስተናገዱን መፍታት አልቻለም።
ይህ ሁለቱም ቡድኖች ሊሸነፉ የሚችሉበት አይነት ጨዋታ ቢሆንም ፉልሃም እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።
ግምት፡ 2 - 1
ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ማንቸስተር ዩናይትድ
የኖቲንግሃም ፎረስት ደጋፊዎች በአዲሱ አሰልጣኝ ሾን ዳይሽ ደስተኞች ሲሆኑ እንደሚታገሷቸውም አስባለሁ።
በምቡሞ እና በማቲየስ ኩኛ ጥሩ ብቃት ማንቸስተር ዩናይትድ ከፍ ከፍ እያለ ነው።
ሆኖም ቡድኑ የተከላካይ መስመሩ ክፍተት አለበት።
ሦስት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ቢችሉም የማሸነፍ ጉዟቸው የሚገታ ይመስለኛል።
ግምት፡ 1 - 1
ቶተንሃም ከ ቼልሲ
የሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች ስለማይዋደዱ ፉክክር ያለበት ጨዋታ ይሆናል።
በዚህ ጨዋታ ቼልሲ የተሻለ ውጤታማ ሲሆን ካለበት ውጣ ውረድ አንጻር ከዚህ ጨዋታም ውጤት ይፈልጋል።
ቶተንሃም ጥሩ ጅማሮ ቢያደርግም የተጎዱ ተጫዋቾች ሲመለሱ የተሻለ እንደሚንቀሳቀስ ይጠበቃል።
ጨዋታውን ለመገመት ስለመቸገር አቻ ይለያያሉ ማለትን መርጫለሁ።
ግምት፡ 1 - 1

ሊቨርፑል ከ አስቶን ቪላ
ሊቨርፑል ካለፉት ሰባት ጨዋታዎች በስድስቱ ተሸንፏል።
ቡድኑ ከዚህ በኋላ ሪያል ማድሪድና እና ማንቸስተር ሲቲን ያሰተናግዳል።
ቪላ ደግሞ ያለፉትን አራት ጨዋታዎች አሸንፏል።
ካላቸው ወቅታዊ አንጻር ቪላ ያሸንፋል ቢባልም ሊቨርፑል በሞ ሳላሃ ሃትሪክ አሸናፊ እንደሚሆን እገምታለሁ።
ግምት፡ 3 - 1
እሑድ
ዌስት ሃም ከ ኒውካስል
ኒውካስል ባለፈው ዓመት የዋንጫ ባለቤት በሆነበት የካራባኦ ዋንጫ ዘንድሮም ጉዞውን እያሳመረ ነው።
ዌስት ሃም በበኩሉ የውጤት ቀውስ ውስጥ ሲሆን ኑኖ ስፕሪንቶ ሳንቶ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው።
ዌስት ሃም የቆሙ ኳሶችን መከላከል ላይ የሚቸገር ሲሆን ኒውካስል አሸኛፊ የሚሆንብት ጨዋታ ይሆናል።
ግምት፡ 0 - 2
ማንቸስትር ሲቲ ከ በርንመዝ
ሲቲ ዘንድሮ በግዙፎቹ ኧርሊንግ ሃላንድ እና ጂያንሉጂ ዱናሮማ ላይ መንጠላጠላቸው መቀየር አለበት።
ቡድኑ ከቆሙ ኳሶች ጎል ያላስቆጠረ ብቸኛው የሊጉ ቡድን ሆኗል።
በጨዋታ ዕድል መፍጠር ላይ ብቻ ማተኮር ተገቢ አይመስለኝም።
በርንመዝ ጎል ማስቆጠር ቢችልም ሲቲ ሦስቱን ነጥቦች ያገኛል።
ግምት፡ 3 - 1
ሰኞ
ሰንድርላንድ ከ ኤቨርተን
ይህንን ጨዋታ ሰንደርላንድ ያሸንፋል ወይም ደግሞ አቨርተን ምንም ነጥብ አያገኝም ለማለት ይከብዳል።
ኤቨርተን ካለፈው ሳምንት ሽንፈት ለማገገም ይጫወታል።
ቤቶ ባለፈው ሳምንት በርካታ ዕድሎችን ቢያመክንም ጎል አስቆጥሮ ለቡድኑ ነጥብ እንደሚያስገኝ እገምታለሁ።
ግምት፡ 1 - 1















