ግዙፉ የሳዑዲ መንግሥት የነዳጅ ኩባንያ በታሪክ ትልቁን ትርፍ አስመዘገበ

የአርማኮ ስራ አስፈጻሚ አሚን ናስር

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, የአርማኮ ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሚን ናስር

ግዙፉ የሳዑዲ የነዳጅ ኩባንያ አራምኮ በአውሮፓውያኑ 2022 161.1 ቢሊዮን ዶላር ማትረፉን አስታወቀ።

ለኩባንያው ትረፍ መመንደግ የነደጃ ዋጋ ማሻቀብና ብዛት ያለው ምርት ማቅርቡ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው።

ኩባንያው በ2022 ያገኘው ትርፍ ከቀደመው ዓመት ትርፉ ጋር ሲነጻጸር የ46.5 በመቶ ጭማሪ አስመዝግቧል።

አራምኮ ባለፈው ዓመት ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረችና የነዳጅ ዋጋ ጣሪያ ከነካ በኃላ ትርፉን ይፋ ያደረገ ሌላኛው ኩባንያ ሆኗል።

በተመሳሳይ ዓመት የአሜሪካው ሞቢል 55.7 በሊዮን ዶላር ያተረፈ ሲሆን የብሪታኒያ የነዳጅ ኩብንያ ሼል ደግሞ 39.9 ቢሊዮን ዶላር አግኝቷል።

አራምኮ ባለፈው ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ካገኘው ገቢ 19.5 ቢሊዮን ዶላር ለትርፍ ክፍፍል በዚህ ዓመት እንደሚያቀርብ አሳውቋል።

ከትርፍ ክፍፍሉም አብላጨው የሚሄደው የኩባንያው 95 በመቶው ባለቤት ወደሆነው የሳዑዲ መንግሥት ነው።

አራምኮ ትላንት ባወጣው መግለጫ ያገኘው ከፍተኛ ትርፍ በደፍድፍ ነዳጅ ዋጋ መጨመር፣ ለሽያጭ ያቀረበው ምርት ብዛት እና በተጣራ ምርት ላይ በሳየው መሻሻል የተደገፈ ነው ብሏል።

የአራምኮ ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሚን ናስር ኩባንያው ወደፊት ከነዳጅ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመቅረፍ የነዳጅ አና የኬሚካል ምርቶቹን ከማሳፋፋት በተጨማሪ ዝቅተኛ የካረበን ልቀት ያላቸው ቴክኖሎጂዎች ላይ መዋዕለ ንዋዩን እንደሚያፈስ አስታውቋል።

በዓለም ከአሜሪካው አፕል በመቀጠል ሁለተኛው ከፍተኛ ሃብት ያለው ተቋም የሆነው አራምኮ፤ በአየር ንብርት ለውጥ አሉታዊ ተጽእኖ ከሚያሳድሩ ኩባንያዎች መካከል ተጠቃሽ ነው።

አራምኮ ትርፉን ማሰወቁን ተከትሎ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ጸሃፊ አንገስ ካላማርድ በሰጡት አስተያየት ለአየር ብክልት ቁጥር አንድ መንስኤ የሆነውን ነዳጅ ሽጦ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ161 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማትረፍ አስደንጋጭ ነው ብለዋል።

ኃላፊዋ ጨምረውም ይህ ትርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኑሮ ውድነት በጨመረበት እና ሩሲያ ዩክሬን ላይ ወረራ ፈጽማ የጋዝ ዋጋ ከፍ ባለበት ጊዜ መሆኑ ይበልጥ አስደንጋጭ ያድርገዋል ብልዋል።