ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ሴ ሺ ላፕ፡ 'የኤሺያው ኤል ቻ' ለአውስትራሊያ ተላልፎ ሊሰጥ ነው
በእስያ የአደንዛዥ ዕጽ ንግድ የተሠማራው እና ከታዋቂው ሜክሲኳዊ ኤል ቻፖ ጋር የሚነጸጻጸረው ግለሰብ በሆንላንድ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ለአውስትራሊያ ተላልፈፎ ሊሰጥ ነው።
ሴ ሺ ላፕ በእስያ-ፓስፊክ አገራት፣ ከጃፓን እስከ ኒው ዚላንድ የተዘረጋና በቢሊዮን የሚቆጠር የሚንቀሳቀስበት የአደንዛዥ እጽ ንግድ ይመራል ተብሏል።
ሴ ሺ ላፕ በጥር ወር በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ የደች ፍርድ ቤት ተላልፎ እንዲሰጥ የቀረበውን ጥያቄ አጽድቋል።
የተከሳሹ ጠበቃው ደንበኛው ይግባኝ ይጠይቃል ብለዋል።
በዜግነት ካናዳዊ በትውልድ በቻይናዊው የሆነው ሴ በዓለም ላይ ካሉት ግዙፍ የአደንዛዥ ዕጽ አዘዋዋሪዎች ቡድኖች መካከል አንዱን በመምራት ተጠርጥሯል። በመላው እስያ በ 70 ቢሊዮን ዶላር የሕገ-ወጥ ዕጾችን ገበያ በበላይነት የሚቆጣጠር ኩባንያን እንደሚመራ ይነገራል።
የአውስትራሊያ ፖሊስ ሳም ጎር ሲንዲኬት ተብሎ የሚጠራው ኩባንያው በሻይ ቅጠል እሽጎች ውስጥ የተደበቁ ሜት፣ ኬታሚን እና ሌሎች ዕጾችን ጨምሮ እጅግ በጣም ብዙ ሕገ-ወጥ ንጥረ ነገሮችን እንዳዘዋወረ ያምናሉ።
ዘዴው ቡድኑን ተጽኖው ከፍተኛ እንዲሆን አግዞታል ተብሏል። ቡድኑ ወደ አውስትራሊያ ለሚገቡ ህገ-ወጥ ዕጾች ውስጥ እስከ 70 በመቶው ተጠያቂ ነው።
ሴ ይመራዋል የተባለው ድርጅት መጠን ከሜክሲኮው ቀንደኛ የዕጽ አዘዋዋሪ ጆአኪን "ኤል ቻፖ" ጉዝማን ጋር እንዲነጻጸር ምክንያት ሆኗል።
በዓለም እጅግ በጣም ተፈላጊ ሰዎች አንዱ የሆነው ሴ አውሮፕላን ለመሳፈር ሲሞክር ባለፈፈው በጥር ወር በአምስተርዳም ሺሎፕል አውሮፕላን ማረፊያ ነበር በቁጥጥር ስር የዋለው።
ከአስር ዓመት በላይ ሲያድነው የነበረው የአውስትራሊያ ፖሊስ ግለሰቡ በአውስትራሊያ እንዲዳኝ ይፈልጋል።
ሴ ግን የዕጽ ዝውውሩ መሪ አይደለሁም በሚል ይከራከራል። የአውስትራሊያ ባለሥልጣናት የፈጠራ ክስ መሆኑን በመግለጽ በሕገ-ወጥ መንገድ ከታይዋን ወደ ካናዳ እንዲያቀና መደረጉን እና በጉዞውም በኔዘርላንድስ እንዲያርፍ በማድረግ እንዲታሰር ማድረጋቸው አመልክቷል።
ጠበቃው ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመውሰድ ተላልፎ የመስጠት ውሳኔ ላይ ይግባኝ አቀርባለሁ ብለዋል።
ለአውስትራሊያ አሳልፎ በመስጠቱ ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠው የኔዘርላንድስ መንግሥት ይሆናል።
በከፍተኛ ጥበቃ ስር በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ የሚገኘው ሴ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በማካው፣ በሆንግ ኮንግ እና በታይዋን መካከል መጓዙ እየተነገረ ነው።
እአአ በ 1990 ዎቹ አሜሪካ ውስጥ በአደንዛዥ ዕጽ ማዘዋወር ክስ ተመስርቶበት ዘጠኝ ዓመት በእስር ቆይቷል።