ሶማሊያዊቷን ታዳጊ ደፍረው የገደሉት በሞት ተቀጡ

የጠመጠመች ግለሰብ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በሶማሊያዋ ራስ መር ፑንት ላንድ ግዛት የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት ታዳጊዋን ደፍረው ገድለዋል ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች የሞት ቅጣት በይኖባቸዋል።

ታዳጊዋ የአስራ አራት አመት ልጅ ነበረች ተብሏል።

የመድፈርና ግድያ ወንጀሉን የፈፀሙት መሃመድ አብዲ ፋራይና አብደራህማን መሃመድ አይዛክ የሚባሉ ግለሰቦች ናቸው። በባለፈው አመት በቦሳሶ ከተማ አግተው እንደወሰዷትና ወንጀሉንም እንደፈፀሙ ተናዘዋል።

በሶማሊያ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መጨመር በርካቶችን ስጋት ላይ ጥሏል።

በተለይም በቅርብ ወራት ውስጥ እንዲህ አይነት ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ መሆኑንም መረጃዎች ያሳያሉ።

ፖሊስም በርካታ የመደፈር ወንጀሎችንና መገደሎችንም እየመረመረ ይገኛል። ባለፈው ወር በሶማሊያዋ መዲና ሞቃዲሾ የ19 አመት ግለሰብ በቡድን ተደፍራ ተገድላለች። ግለሰቧ ከስድስት ፎቅ ላይ ወርውረዋት ነው ህይወቷ የጠፋው። ፖሊስም ይህንን ወንጀልም እየመረመረም እንዳለ ተገልጿል።