እውን አውስትራሊያ ምስሉ ላይ እንደሚታየው እየተቃጠለች ነው?

እውን አውስትራሊያ ምስሉ ላይ እንደሚታየው እየተቃጠለች ነው?

የፎቶው ባለመብት, እውን አውስትራሊያ ምስሉ ላይ እንደሚታየው እየተቃጠለች ነው?

የአውስታራሊያ ሠደድ እሳትን የሚያሳዩ ፎቶዎች፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎችና በማሕበራዊ ድር-አምባዎች ላይ እየተሠራጩ ነው።

ነገር ግን ከሰሞኑ የተሠራጨና አውስታራሊያ ስትንቦገቦግ የሚያሳይ የሳተላይት ምስል ብዙዎችን አጃኢብ አሰኝቷል።

የብዙዎቹ ለጣፊዎች ዓላማ አውስትራሊያ እና የተፈጥሮ ሃብቷ፤ በተለይ ደግሞ የዱር እንስሳት ላይ እየደረሰ ያለው እልቂት አሳስቧቸው 'ኧረ እንደርስላቸው' ነው።

ከጀመረ ወራትን ያስቆጠረው የአውስታራሊያ ሰደድ እሣት 25 ሰዎችን ሲገድል በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዱር እንስሳትም ሰለባ ሆነዋል። አልፎም 2000 መኖሪያ ቤቶችን ከጥቅም ውጭ አድርጓል።

ምንም እንኳ ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የጣለው ዝናብ ሁኔታውን በትንሹም ቢሆን ጋብ ቢያደርገውም የእሣት አደጋ ሰዎች ቃጠሎው እንደ አዲስ ሊባባስ ይችላል የሚል ስጋር አላቸው።

የሳተላይት ምስሉ ምስጢር

ሪሃናን ጨምሮ በበርካታ ታዋቂ ሰዎች ትዊተርና ኢንስታግራም ገፃቸው ሲንሸራሸር የነበረው ከላይ የሚታየው ምስል ሰደድ እሣቱ ቢስፋፋ ምን ሊመስል እንደሚችል ምናባዊ እይታ እንዲሰጥ ተደርጎ በአንድ ግለሰብ የተሠራ እንጂ እውነተኛ አይደለም።

የ X ይዘትን ይለፉት, 1
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ, 1

አርቲስት አንተኒ ሃርሲ የተሰኘው ይህ ግለሰብ ባለፉት ወራት እሣት የተነሳባቸውን ቦታዎች ምስል ከሰበሰበ በኋላ ሰደዱ በአንድ ጊዜ ቢከሰት ይህን ይመስላል የሚል መረጃ ለመስጠት የሠራው ሥራ ነው።

አርቲስቱ ፎቶው በማሕበራዊ ድር-አምባዎች እውቅና ካገኘ በኋላ በትዊተር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት እርግጥ ነው የሳተለይት ምስል ግነት ይታይበታል፤ ቢሆንም እውነታን መሠረት አድርጌ ነው የሠራሁት ሲል ፅፏል።

ሌላኛው በርካቶች ሲጋሩት የነበረው የአውስትራሊያን ካርታ የሚያሳየው ምስል አህጉሪቱ ስትንበለበል ያሳያል።

የ X ይዘትን ይለፉት, 2
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ, 2

ምስሉ የተገኘው ከአውስትራሊያ መንግሥት ድረ-ገፅ ሲሆን የሠደድ እሣቱን መስፋፋት የሚሳይ ሳይሆን የሙቀት መጠንን ለማሳየት የዋለ ነው። ካርታው ላይ የሚታዩት ቀያይ ነጥቦች ተፈጥሯዊውም ሆነ ሰው ሠራሽ ሙቀት በአካባቢው መኖሩን የሚያመላክቱ እንጂ ከእሣት ጋር ብቻ የተያያዙ እንዳልሆኑ መንግሥት አስታውቋል።

እነዚህ ምስሎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች በርካታ የሳተላይት ምስሎች የአውስትራሊያን ሠደድ እሣት ለማሳየት ጥቅም ላይ እየዋሉ ሲሆን ግማሾቹ አሳሳች ናቸው እየተባለ ነው።