የኬንያ ፖሊስ የልጇን አፍ የሰፋችውን እናት እያደነ ነው

የኬንያ ፖሊስ የልጇን ከንፈሮች አጋጥማ የሰፋችውን እናት እየፈለገ እንደሆነ አንድ የመንግሥት ኃላፊ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

የናኩሩ ግዛት ኮሚሽነር ጁሊየስ ንያጋ እንደገለፁት የተሰፋው ህፃን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው።

ኮሚሽነሩ አስገራሚው ሁኔታ እንዴት እንደተፈፀመ ሲናገሩም አንድ መምህር ህፃኑን እርሳስና ላጲስ እናቱን እንዲያስገዛ ትእዛዝ ይሰጡታል።

ልጁም እናቱን በጠየቀበት ወቅት መምህሩ ራሱ ይግዛልህ የሚል ምላሽ በመስጠቷ ተማሪውም የተባለውን ሄዶ ለትምህርት ቤቱ እንደተናገረ ይኼው ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

ትምህርት ቤቱም ወላጅ እናቱን ጠርቶ ስለ ጉዳዩ ሲጠይቅ አላልኩም ብላ ከመካዷ በተጨማሪ በቀጣይነት የወሰደችው እርምጃ የልጆቿን ከንፈሮች አገጣጥማ መስፋትን እንደሆነ ኮሚሽነር ጁሊየስ ገልፀዋል።