ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ቦይንግ 737 ተንሸራቶ ወንዝ ውስጥ ገባ
አሜሪካ ቴክሳስ ውስጥ አንድ የቦይንግ አውሮፕላን ካረፈ በኋላ ተንሸራቶ ወንዝ ውስጥ ገብቷል። አውሮፕላኑ ያረፈው መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ እየዘነበ ሳለ ነበር።
በቦይንግ 737 ተሳፍረው የነበሩት 143 ሰዎች የከፋ ጉዳት አልደረሰባቸውም። ሆኖም ከተሳፋሪዎቹ መካከል ወደ 20 የሚሆኑት ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና መስጫ ተወስደዋል።
በሚያሚ ኤር ኢንተርናሽናል ስር የሚተዳደረው አውሮፕላኑ ጉዞውን የጀመረው ከኩባ ጓንታናሞ ቤይ ነበር።
ተሳፋሪዎቹ እንዳሉት በዝናብ ወቅት ያረፈው አውሮፕላኑ ሴንት ጆን የተባለ ወንዝ ውስጥ ተንሸራቶ ገብቷል።
ከተሳፋሪዎቹ አንዱ ቼሪል ቦርማን ለሲኤንኤን "አውሮፕላኑ መሬቱን ነክቶ ነጠረ። አብራሪው መቆጣጠር እንዳቃተው ያስታውቅ ነበር" ብለዋል።
ተሳፋሪዋ እንደገለጹት፤ አውሮፕላኑ የገባው ወንዝ ውስጥ ይሁን ባህር ውስጥ አላወቁም ነበር፤ "ሁኔታው አስፈሪ ነበር" ብለዋል።