ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አሜሪካዊው ራፐር ካንዬ ዌስትና ኪም ካርዳሽያን ዩጋንዳዊ ስም ተሰጣቸው
ታዋቂው የሂፕሆፕ አቀንቃኝ ካንዬ ዌስትና ባለቤቱ ኪም ካርዳሽያን በዩጋንዳ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ ጋር ተገናኝተዋል።
ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በባለፈው ወር ስሙን የ በሚል ለቀየረው ካንዬ ዌስት ካንሲግየ የሚል መጠሪያ የሰጡት ሲሆን ትርጉም "አምናለሁ" ማለት ነው።
ለባለቤቱ ኪም ካርዳሺያን ደግሞ ኬሚጊሻ የሚል ስም ሰጥተዋታል፤ ትርጉሙም "የአምላክ ስጦታ" ማለት እንደሆነ የፕሬዚዳንቱ ቢሮ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።
ራፐሩና ባለቤቱ ፕሬዚዳንቱ አዲስ ስም ስለሰተጧቸውም መደሰታቸውንም ጭምር ተገልጿል።
ፕሬዚዳንቱ ጨምረውም ዩጋንዳ የሁሉም አገር እንደሆነች ገልፀውላቸዋል።
"ይህች መሬት የሰው ልጅ መገኛ ናት፤ ነጭ ህዝቦች ራሱ መነሻቸው ከዚህ ነው" በማለት ፕሬዚዳንቱ እንደተናገሩ በፌስቡክ የሰፈረው ፅሁፍ ያስረዳል።
ራፐሩ በበኩሉ ዩጋንዳ በመምጣቱ ደስተኛነቱን ገልፆ ሁለተኛ ቤቴ ሲልም ተናግሯል።
"ካንዬ ለፕሬዚዳንቱ ደረጃውን የጠበቀ የቱሪዝም ትምህርት ቤት እንደሚከፍት አስታውቋቸዋል። ይህ ለዩጋንዳ ብቻ ሳይሆን ለምስራቅ አፍሪካ ጠቃሚ ይሆናል" በማለት የፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት በመግለጫው ጨምሯል።