ሞ ሳላህ እያሽከረከረ ሞባይል ሲጠቀም የሚያሳየው ቪዲዮ ፖሊስ ጋር ደረሰ

ሞሃመድ ሳላህ

የፎቶው ባለመብት, Laurence Griffiths

የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች የሆነው ሞሃመድ ሳላህ ሞባይል ስልክ እየተጠቀመ ሲያሽከረክር የሚያሳይ ቪዲዮ ሊቨርፑል እጅ ከደረሰ በኋላ ክለቡ ለፖሊስ ጥቆማ አድርሷል።

የሊቨርፑል ፖሊስም በትዊተር ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ተንቀሳቃሽ ምስሉን መመልከቱንና የሚመለከተው ክፍል ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

የሊቨርፑል ክለብ ቃል አቀባይ እንዳሉት ክለቡ ለፖሊስ ጥቆማውን ከማድረሱ በፊት ከተጫዋቹ ጋር መነጋገሩን አሳውቋል። ቃል አቀባዩ ጨምረውም ተጫዋቹም ሆነ ክለቡ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ነገር ማለት አይፈልጉም።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት የተሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ግብጻዊው ተጫዋች እያሽከረከረ ስልኩን ሲጠቀም ያሳያል።