የጋሬዝ ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን፡ ሳላህ፣ ፖግባ፣ ዛሃ፣ ዎከር . . . ። ሌሎችስ እነማን ናቸው?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ያለፈው ዓመት ሻማፕዮኖች የዘንድሮውን የውድድር ዘመን አርሴናልን በማሸነፍ ጀምረዋል። የውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታ በነበረው ማንቸስተር ዩናይትድ ሌስተር ሲቲን አሸንፏል።
በሌሎች ጨዋታዎች ቨርፑል እና ቶተንሃምም አሸናፊ ለመሆን ችለዋል።
ዎልቭሶች ሁለት ጊዜ ከኋላ በመነሳተር ከኤቨርተን ጋር አቻ ለመለያየት ችለዋል።
በሳምንቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ እነማን ሊካተቱ ይችላሉ? እነሆ የጋሬዝ ክሩክስ ምርጥ 11።
ግብ ጠባቂ- ዴቪድ ደ ሂያ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ዴቪድ ደ ሂያ በፕሪሚር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ላይ ድንቅ ብቃቱን ማሳየት ጀምሯል።
በእሱ ደረጃ ላለ ተጫዋች ከስፔን ጋር ያሳለፈው የዓለም ዋንጫ አስደንጋጭ ቢሆንም ከሌስተር ጋር ይህ አልተደገመም። ያዳናቸው ሁለት ኳሶች ማንቸሰተር ዩናይትድ ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ አስችሎታል።
ይህን ያውቃሉ? ማንቸስትር በመጀመሪያ ጨዋታው ሌስተርን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ሶስት ኳሶችን አድኗል።
ተከላካዮች፡ አሮን ዋን-ቢሳካ፣ ካይል ዎከር፣ ቪጂል ቫን ዳይክ እና ሉክ ሾው

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
አሮና ዋን-ቢሳካ፡ የ20 ዓመቱ ተጫዋች ድንቅ እንቅስቃሴ አሳይቷል። ዋን ቢሳካ ሪያን ሴሴኞን፥ አንድሬ ሹርለን እና አቡባከር ካማራን በፍጥነት ካለፈ በኋላ ከአሌክሳንደር ሚትሪቪችን በጉልበት በመብለጥ ለዊልፍሬድ ዛሃ ያቀበላት ኳስ ከመረብ አርፋለች።
ፓላሶች አልማዝ ያገኙ ሲሆን እኔ ብሆን ለረዥም ጊዜ የሚያቆየውን ውል በፍጥነት አስፈርመው ነበር።
ይህን ያውቃሉ? ዋን-ባሰካ ለጎል የሚሆን ኳስ ከማመቻቸቱም በላይ ጎል እንዳይቆጠርባቸው እገዛ አድርጓል።
ካይል ዎከር፡ ዎከር ድንቅ ተጫወች እየመሰለ ነው። አርሰን ቬንግር አይሆነውም ባሉት የሶስት ተከላካይ መስመር ላይ በመሰለፍ በዓለም ዋንጫው ላይ ጥሩ ተንቀሳቅሷል።
በፕሪሚየር ሊጉ መክፈቻ ከአርሴናል ጋር በነበረው ጨዋታ ድንቅ ተከላካይ ሆኖ አምሽቷል።
ይህን ያውቃሉ? ዎከር ከአርሴናል ጋር በነበረው ጨዋታ 23 ጊዜ በፍጥነት ሲምዘገዘግ ነበር። ይህ ደግሞ በመጀመሪያው ሳምንት በተከላካኦች ከተደረጉት ሁሉ የላቀው ነው።
ቪጂል ቫን ዳይክ ፡ ሊቨርፑል ዌስት ሃምን 3 ለ 0 እየመራ ባለበት ወቅት እንኳን አብረውት ያሉትን ተከላካዮች ጎል ሳይቆጠርባቸው ጨዋታውን ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ሲያሳስብ ነበር።
ይህ ቫን ዳይክ ወደ ቡድኑ ከመምጣቱ በፊት እና አሁን ያለው ሊቨርፑል ልዩነት ነው።
ይህን ያውቃሉ? ከዌስት ሃም ጋር በነበረው ጨዋታ 98.4 በመቶ የተሳኩ ኳሶችን አቀብሏል።
ሉክ ሾው ማንቸስተሮች ባሳዩት ጥሩ እንቅስቃሴ ውስጥ ወደ አሰልጣኝነት የተቀየረው ማይክል ካሪክ ሚና እንደነበረው አምናለሁ። ሾው በጨዋታው ላየዕ ይሳተፋል ብዬ አላሰብኩም ነበር።
ሾው ከሁለት ዓመት በፊት ከቼልሲ ጋር በነበረ ጨዋታ ላይ ግራ ተጋብቶ እንደነበር አስታውሳለሁ። ከሌይስትር ጋር ግን ተከላካዩ ድንቅ ነበር።
ይህን ያውቃሉ? ሾው በ134 ጫወታዎች የመጀመሪያ ጎሉን ነው ያስቆጠረው።
አማካዮች ሮቤርቶ ፔሬራ፣ ሩበን ኔቬስ እና ፖል ፖግባ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሮቤርቶ ፔሬራ፡ ክሪስ ሃተን ጥሩ የቅድመ ውድድር ጊዜ ማሳለፋቸውን እና ለዋትፎርድ ዝግጁ መሆናቸውን ቢገልጹም ፔሬራ ነጥብ አሰጥሏቸዋል።
ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረው ሮቤርቶ ፔሬራ በሊጉ አራት ተከታታይ ዓመታት የቆዩትን ዋትፎርዶችን ለሌላ ተጨማሪ ዓመት በሊጉ ለመቆየት የሚችሉ አይነት አስመስሏሰቸዋል።
ይህን ያውቃሉ?ባለፉት ስድስት የዋትፎርድ የሊጉ ጎሎች ውስጥ ፔሬራ ተሳትፎ ነበረው። አምስት አስቆጥሮ አንድ አመቻችቶ በማቀበል።
ሩበን ኔቬስ: ፖርቹጋላዊው ተጫዋች ገና በ 21 ዓመቱ ድንቅ መሆኑን አሳይቷል።
ዎልቭሶችን በሊጉ ማቆት የሚችል ከሆነ ባርሴሎና ወይንም ሪያል ማድሪድ ሊወስዱት ማሰባቸው አይቀርም። ይህ ከሆነ የክለቡ ደጋፊዎችም ተጫዋቹ ስለመቆየቱ ጥርጣሬ ይገባቸዋል።
ይህን ያውቃሉ? ካለፈው የውድድር ዓመት ጀምሮ ከእንግሊዝ አራት ከፍተኛ ሊጎች ውስጥ ከፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውጭ ሰባት ጎሎችን በማስቆተር ቀዳሚ ነው።
ፖል ፖግባ፡ ጆሴ ሞውሪንሆ በውድድር ዓመቱ መክፈቻ ጨዋታ ላይ ፖል ፖግባን የቡድናቸው አምበል ያደረጉት ሲሆን ይህም ከየዓለም ዋንጫ አሸናፊው ከአሰልጣኙ የሚያገኘው ብቸኛ ማበረታቻ ሊሆን ይችላል።
ተጫዋቹም ከሌስትር ጋር በነበረው ጨዋታ ድንቅ በመሆን ምላሹን ሰጥቷል።
ይህን ያውቃሉ? ፖግባ በሶስተኛው ደቂቃ ኣስቆጠራት ጎል ማንቸስትር ዩናይትድ በውድድር መክፈቻ በፍጥነት ያስቆተራት ጎል ናት። ከዚህ በፊት ድዋይት ዮርክ በሰባተኛው ደቂቃ ላይኤቨርተን ላይ አስቆትሮ ክብረወሰኑን ይዞ ነበር።
አጥቂዎች- ሞሃመድ ሳላህ፣ ዊልፍሬድ ዛሃ እና ሪቻርልሰን

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሞሃመድ ሳላህ: የተለመደው አገልግሎት ተጀምሯል። ሳላህ አንፊልድ ላይ ብቃቱን ማሳየቱን ቀጥሏል።
ሊቨርፑሎች አሁን እያሳዩ ያሉትን አጨዋወት አደንቃለሁ። ኳስ በሚገርም ፍጥነት ወደ ተቀናቃኝ ሜዳ ይዘው ይሄዳሉ።
ይህን ያውቃሉ? ሳላህ ሊቨርፑል በሊጉ ከዌስት ሃም ጋር ባደረጋቸው ሶስት ቸዋታዎች በአምስት ጎሎች ላይ በቀጥታ ተሳትፎ ነበረው።
ዊልፍሬድ ዛሃ: ይህ ከዛሃ ያየሁት ምርት እንቅስቃሴ ባይሆንም ከሪያን ሴሴኞን የምጠብቀውን ነው ያደረገው። ስለፉልሃሙ ተጫዋች ብዙ የሰማሁ ሲሆን ይህን ለማየትም እየጠበቅኩ ነው።
ፓላስ ውስጥ ጊዜው የዛሃ ሲሆን ሴሴኞን ግን ገና ታዳጊ ነው የሚመስለው።
ይህን ያውቃሉ?ዛሃ ለክሪስታል ፓለስ በፕሪሚየር ሊጉ 23ኛ ጎሉን ነው ያስቆጠረው። ይህም ከክሪስ አርምስትሮንግ ጋር እኩል አድርጎታል።
ሪቻርልሰን: ለተጫዋቹ ይህ ድንቅ አጀማመር ነው። ቡድኑ ዳኛው በወሰኑት ውሳኔ ባይጎዳ የሪቻርልሰንን ጎሎች ተጠቅሞ ለማሸነፍ ከጫፍ ደርሶ ነበር።
በአወዛጋቢ ውሳኔዎቻቸው ምክንያት የእንግሊዝ ዳኞች ተመራጭ አይደሉም። የሊጉ ዳኞች ለዓለም ዋንጫ ለምን እንደ፥ኣይመረጡ ለማወቅ ክሬግ ፓውሰን ፊል ጃጊኤልካን ከሜዳ ያሰናበቱበትን ሁኔታ ማየት በቂ ነው።
ይህን ያውቃሉ? ለኤቨርተን ካደረጋቸው ሁለት ሙከራዎች ነው የመጀመሪያውን ጎል ያስቆጠረው። ወዋትፎርድ እያለ 53 ጊዜ ሞክሮ ጎል ማስቆተር አልቻለም ነበር።














