ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አፍሪካውያን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ
አፍሪካውያን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ምን ያህል ስኬታማ ናቸው? በርካታ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጨዋቾች አውሮፓውያን ናቸው። አፍሪካውያን እግር ኳሰኞች ከእሲያ እና ደቡብ አሜሪካ ተጨዋቾች የበለጠ በፕሪሚየር ሊጉ ቁጥር አላቸው።
አፍሪካውያን ተጨዋቾች ለሚጫወቱባቸው ክለቦች የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሱ ቀላል የማይባል አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ናይጄሪያና ሴኔጋል ደግሞ 39 እና 35 ተጫዋቾችን በሊጉ በማሳተፍ የቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ። ዝቅተኛ የሚባል የተጫዋች ቁጥር ያላት ጋና ስትሆን ቁጥራቸውም 26 ነው።
የአይቮሪ ኮስት እግር ኳሰኞች በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሌሎች ሃገራት በላይ አስራ ሁለት ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ቀዳሚ ናቸው። በሁለተኝነት የምትከተላት ደግሞ ናይጄሪያ ስትሆን፤ በአጠቃላይ 11 ሜዳሊያዎችን በእንግሊዝ ውድድሮች ማግኘት ችለዋል።