ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ኡጋንዳ ስደተኞችን ከእስራኤል ለመቀበል ስምምነት ማድረጓን አስተባበለች
የምታስወጣቸውን ስደተኞች ለመቀበል ከእስራኤል ጋር ያደረገችው ምንም አይነት ስምምነት እንደሌለ የኡጋንዳው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄንሪ ኦሪም ኦኬሎ መግለፃቸውን ዴይሊ ሞኒተር ዘግቧል።
ሚኒስትሩ ኡጋንዳ እስራኤል የምታስወጣቸውን በሺህ የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞች ልትቀበል እንደሆነ የሚገልፀው ሪፖርት ከየት እንደመጣ ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል።
እስራኤል የገቡት በህገወጥ መንገድ ነው ያለቻቸውን ስደተኞች ለመቀበል የተደረገ ምንም አይነት ስምምነት አለመኖሩንም አረጋግጠዋል።
"በእስራኤል የሚገኙ የሌላ አገር ስደተኞችን ለመቀበል ከእስራኤል ጋር ያደረግነው ስምምነት የለም።ሪፖርቱም ግራ አጋብቶናል።በዚህ ረገድ ከአገሪቱ ጋር ምንም ዓይነት አጋርነት የለንም።ስለጉዳዩ ዝርዝር ነገር ከፈለጋችሁ እነሱን ጠይቋቸው።"ብለዋል።
ከእስራኤል ይውጡ የተባሉት ስደተኞች አብዛኞቹ የኤርትራና የሱዳን ዜጎች ሲሆኑ ወደ አገራቸው መመለስ ለህይወታቸው እንደሚያሰጋቻው ይናገራሉ።