የዝንጀሮ ፈንጣጣ፡ ስለ በሽታው መጨነቅ አለብን ወይስ ችላ እንበለው?

በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ህጻን

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ህጻን

ከኮቪድ19 ወረርሽኝ ስጋት ገና ከመላቀቅዎ ሌላ ቫይረስ ብቅ ብሏል። አሁን ጊዜው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ነው።

እንግሊዝን ጨምሮ በ11 አገሮች ወደ 80 የሚጠጉ ሰዎች መያዛቸው ተረጋግጧል። እነዚህ አገራት በተለምዶ በሽታው ይከሰትባቸዋል ተብለው የማይጠበቁ ናቸው።

ታዲያ ምን እየሆነ ነው? የምንጨነቅበት ጊዜ ነው? ወይንስ ከኮቪድ-19 ጋር በመኖራችን ከመጠን በላይ እየተደሰትን ነው?

ግልጽ እንሁን፡ ይህ ኮቪድ-19 አይደለም።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ስርጭትን ለመግታት ያለመንቀሳቀስ እገዳ በመጪዎቹ ቀናት አይኖሩም።

ሆኖም ይህ ያልተለመደ እና ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ነው።

በሽታው ላይ ያተኮሩ ሳይንቲስቶችን ያስገረመም ነው። ቫይረሱ ባህሪውን ሲቀይር ሁልጊዜም አሳሳቢ ነው።

እስካሁን ድረስ የዝንጀሮ በሽታ መተንበይ የሚቻል ነበር።

የቫይረሱ ተፈጥሯዊ መኖሪያ የዱር እንስሳት ሲሆኑ ከዝንጀሮዎች ይልቅ አይጦች ናቸው ተብለው ይታሰባሉ።

በምዕራብ እና በመካከለኛው አፍሪካ በሚገኙ ደኖች ውስጥ ያለ አንድ ሰው በበሽታው ከተያዘ ፍጡር ጋር ከተገናኘ በበሽታው ይያዛል።

ቆዳቸው በሽፍታ ይፈነዳል። ቀጥሎም መነሳት ይጀምራል።

ቫይረሱ አሁን ከወትሮው ቤቱ ውጭ ስለሆነ ለመዛመት እየታገለ ነው። ለመዛመት ረዥም የቅርብ ንክኪ ያስፈልገዋል። ስለዚህ ወረርሽኙ ትንሽ ሲሆን በራሱ ጊዜ ይቋረጣል።

ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ከዚህ ቀደም በዓለም ውስጥ በቫይረሱ ተይዘዋል። ሁሉም ቫይረሱ ወዳለበት አገር ተጉዘው የተመለሱ ናቸው።

አሁን ጉዳዩ ይህ አይደለም።

  • ለመጀመሪያ ጊዜ ቫይረሱ በምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ጋር ግልጽ ግንኙነት በሌላቸው ሰዎች ላይ ተገኝቷል
  • ሰዎቹ ከማን እንደያዛቸው ግልጽ አይደለም
  • የዝንጀሮ ፈንጣጣ በወሲባዊ ግንኙነቶች ወቅት እየተስፋፋ ነው
  • ከተጎዱት መካከል ብዙዎቹ ከተመሳሳይ ጾታ እና ከተለያዩ ጾታዎች ጋር ወሲብ ፈጽመዋል

የኦክስፎርድ የወረርሽኝ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ሰር ፒተር ሆርቢ "በጣም የተለየ ሁኔታ ላይ ነን። ይህ የሚያስደንቅ እና የሚያስጨንቅ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ "ኮቪድ ቁጥር ሁለት አይደለም" ቢሉም ቫይረሱ "በእርግጥ ልናስወግደው የምንፈልገው ነገር" በመሆኑ ቫይረሱን ለመከላከል "እርምጃ መውሰድ አለብን" ብለዋል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ያለባቸውን ታማሚዎች ያከሙት ዶ/ር አድለርም በዚህ ይስማማሉ። "ከዚህ በፊት ያየነው ዓይነት አይደለም - ይህ የሚያስደንቅ ነው" ብለዋል።

የቫይረሱ ምልክት

የፎቶው ባለመብት, UKHSA

ምን እየተከናወነ ነው?

ይህ ወረርሽኝ የተለየ እንደሆነ ቢታወቅም ለምን እንደተለየ ግን አይታወቅም።

ሁለት መላ ምቶች ግን አሉ። ቫይረሱ ተለውጧል ወይም የድሮው ቫይረስ ለመሰራጨት በሚፈልገው ትክክለኛው ጊዜ ራሱን አግኝቷል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ የዘረ መል ቫይረስ ስለሆነ ልክ እንደ ኮቪድ-19 ወይም ጉንፋን በፍጥነት አይለወጥም።

በጣም ቀደም ብሎ የነበረው ዘረ መል እንደሚያሳየው፣ አሁን ያሉት ቫይረሶች በ2018 እና 2019 ከታዩ የቫይረስ ዓይነቶች ጋር በጣም የተቀራረቡ ናቸው።

እርግጠኛ ለመሆን ጊዜው ባይሆንም ይህ አዲስ ዝርያ ስለመሆኑ ምንም መረጃ የለም።

ካለፉት አስር ዓመታት ከኢቦላ እና ከዚካ ቫይረስ ያልተጠበቁ ትላልቅ ወረርሽኞች እንደተማርነው ቫይረስ አጋጣሚውን ለመጠቀም ራሱን መቀየር የለበትም።

የለንደን የሃይጂን እና የትሮፒካል ሕክምና ትምህርት ቤት ፕሮፌሰር የሆኑት አደም ኩቻርስኪ "በኢቦላ ለመያዝ ቀላል እንደሆነ እናስብ ነበር" ብለዋል።

የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች እና ከሁለቱም ጾታ ጋር የሚገናኙ ወንዶች ለምን ባልተመጣጠነ ሁኔታ እንደሚጎዱ ግልጽ አይደለም።

ወሲባዊ ባህሪያት በቀላሉ ለመስፋፋት ቀላል ያደርጉታል? ወይስ በአጋጣሚ ብቻ ነው? ስለጾታዊ ጤና ጠንቅቆ የሚያውቅ እና የሚመረመር ማኅበረሰብ ነው?

ለዝንጀሮ ፈንጣጣ መስፋፋት ቀላል እየሆነ ሊሆን ይችላል። ያለፉት ጅምላ የፈንጣጣ ክትባቶች ከአሁኑ ይልቅ ለቀድሞ ትውልዶች መከላከያ ይሰጡ ነበር።

ይህ ወረርሽኝ ራሱን ያጠፋል ብለው የሚጠብቁት ዶ/ር አድለር "በፈንጣጣ ዘመን ከነበረው በበለጠ ውጤታማ በሆነ መንገድ እየተላለፈ ነው። ነገር ግን እየተስፋፋ ሊሄድ እንደሚችል የሚጠቁም ነገር እያየን አይደለም" ብለዋል።

ይህ ወረርሽኝ እንዴት እንደጀመረ መረዳት በቀጣይ ምን እንደሚሆን ለመተንበይ ይረዳል።

እኛ የምናየው ከብዙው ጥቂቱን ብቻ ነው።

ምክንያቱም የተያዙት ሰዎች የተላለፈበትን ምሥል አይሰጡም። ይልቁንም ብዙዎቹ ቫይረሶች የተገኙት ተዛማጅነት በሌላቸው ሰዎች ስለሆነ የጎደሉ አገናኞች አሉ።

ይህም በመላው አውሮፓ ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ የተስፋፋ ሊያደርገው ይችላል።

እንደ ፌስቲቫል ባሉ ቦታዎች ላይ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው በዝንጀሮ ፈንጣጣ ተይዘው ወደ ተለያዩ አገራት የወሰዱበት ግዙፍ ክስተት የወቅቱን ሁኔታ ሊያብራራ ይችላል።

ለብዙ ግንኙነት ለሌላቸው ሰዎች በቫይረሱ መያዝ ሌላ ምክንያት ቫይረሱ በብዙ ሰዎች እየተላለፈ ለብዙ ጊዜ ሳይስተዋል ቆይቶ ሊሆን ይችላል።

ያም ሆነ ይህ፣ ተጨማሪ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ይቀጥላል ተብሎ ይገመታል።

የለንደን ሃይጂን እና ትሮፒካ ሜዲሲን ትምህርት ቤት ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ጂሚ ዊትዎርዝ በበኩላቸው "በዚህ ደረጃ ሕዝቡ መጨነቅ ያለበት አይመስለኝም። ነገር ግን እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያወቅን አይመስለኝም። እኛ ይህንን እየተቆጣጠርን አይደለም" ብለዋል።

አስታውሱ ከኮቪድ-19 ጋር የነበረን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ግን አይደለንም።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ አዲስ ሳይሆን የታወቀ ቫይረስ ነው። ክትባቶች እና ሕክምናዎች አሉ።

በአብዛኛው ሕመሙ መለስተኛ ቢሆንም በሕፃናት፣ በእርጉዝ ሴቶች እና ደካማ የበሽታ መከላከያ ሥርዓት ባላቸው ላይ የበለጠ አደገኛ ሊሆን ይችላል።

ከኮቪድ አንጻርም በዝግታ ይሰራጫል።

የተለየ እና የሚያሰቃይ ሽፍታ በመሆኑም በቀላሉ ሊለይ ይችላል።

ይህ ምናልባት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለማግኘት እና በበሽታው የመያዝ ስጋት ያለባቸውን ለመከተብ ቀላል ያደርገዋል።

ሆኖም የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ዳይሬክተር ሃንስ ክሉጅ "ወደ በጋ ወቅት እንየገባን በመሆኑ በሕዝብ መሰባሰቢያዎች፣ በዓላት እና ድግሶች ምክንያት ስርጭቱ ሊፋጠን ይችላል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።