ከሳምንታት በፊት ከእስራኤል እስር ቤት ያመለጡት ሁሉም ፍልስጥኤማውያን ተያዙ

ከሁለት ሳምንት በፊት ከእስራኤል እስር ቤት ያመለጡትና የተቀሩት ሁለት ፍልስጥኤማውያን እስረኞች መያዛቸውን እስራኤል አስታወቀች።

የእስራኤል ጦር ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ካመለጡት ስድስት ፍልስጥኤማዊ መካከል የመጨረሻዎቹን ሁለቱን በቁጥጥር ማዋሉን አስታወቀ።

እስራኤል ባለፈው ሳምንት አራቱን እስረኞች የያዘች ሲሆን የተቀሩትን ሁለት የእስላማዊ ጂሃድ አባላት የሆኑትን እስረኞች በዌስት ባንክ ከተማ በፀጥታ ኃይሎች ከተከበቡ በኋላ ተይዘው ወደ እስር ቤት መወሰዳቸውን ነው የእስራኤል መከላከያ ሃይል ሰራዊት ያስታወቀው።

በፍልስጥኤማውያን ዘንድ ከፍተኛ ደስታን ፈጥሮ የነበረው የእስረኞቹ ማምለጥን በተመለከተ ምርመራ ተጀምሯል።

ዛሬ [እሁድ]በዌስት ባንክ የተቀሩትን ሁሉቱን እሰረኞች ለመያዝ በተደረገው እንቅስቃሴ በእስራኤል ኃይሎች እና በፍልስጥኤማውያን ተቃዋሚዎች መካከል ግጭ ተቀስቅሶ የነበረ ቢሆንም እስረኞቹ ግን ያለማንገራገር እጅ መስጠታቸውን የእስራኤል ፖሊስ ገልጿል።

ከእስረኞቹ የአንዱ አባት ለአሶሺየትድ ፕሬስ እንደተናገረው ልጃቸው የሸሸጉትን "የቤት ባለቤቶች አደጋ ላይ ላለመጣል" እጁን ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነዋል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት ዋሻ ሰርተው ያመለጡትን እስረኞች በቁጥጥር ስር ለማዋል የተደረገው ዘመቻ "አስደናቂ ፣ የተራቀቀ እና ፈጣን ነው ያሉ ሲሆን " ስህተቶችም ሊታረሙ ይችላሉ" ብለዋል።

ክስተቱ ለእስራኤል የእስር ቤት አገልግሎት አሳፋሪ ሆኖ ያለፈ ሲሆን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በርካታ የደህንነት ጉድለቶችን ሲያመላክቱም ቆይተዋል።

እስረኞቹ ለወራት ዋሻው ሲቆፍሩ መቆየታቸው የተገመተ ሲሆን ከሁለት ሳምንት በፊት ጥብቅ ጥበቃ ከነበረው እስር ቤት ማምለጣቸው መነጋጋሪያ ሆኖ ነበር።

ካመለጡት እስረኞች መካከል የአንዱ ጠበቃ ደንበኛዋ እስር ቤቱን ለመቆፈር ማንኪያ ፣ ሳህኖች እና የእቃ መያዥያ እጀታ ተጠቅሟል ብለዋል።

እናም ከዚህ ክስተት በኋላ ማንኪያዎች በፍልስጥኤም ደጋፊዎች ተቃውሞዎች ማንኪያን መያዝ የተለመደ ሆኖል።

ያመለጡት እስረኞች በእስራኤላውያን ላይ በማሴር ወይም ጥቃቶችን በመፈጸሙ ክስ ተመስርቶባቸው ወደ እስር ቤት የተላኩ ነበሩ።

የእስራኤል ጦር ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ካመለጡት ስድስት ፍልስጥኤማዊ መካከል የመጨረሻዎቹን ሁለቱን በቁጥጥር ማዋሉን አስታወቀ።

እስራኤል ባለፈው ሳምንት አራቱን እሰረኞች የያዘች ሲሆን የተቀሩትን ሁለት የእስላማዊ ጂሃድ አባላት የሆኑትን እስረኞች በዌስት ባንክ ከተማ በፀጥታ ኃይሎች ከተከበቡ በኋላ ተይዘው ወደ እስር ቤት መወሰዳቸውን ነው የእስራኤል መከላከያ ሃይል ሰራዊት ያስታወቀው።