ኢትዮጵያ በሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ ማግኘቷ የፈጠረው ስሜት

ለሜቻ ግርማ

የፎቶው ባለመብት, NurPhoto

ለሜቻ ግርማ በጃፓን ቶኪዮ ኦሎምፒክስ ላይ በሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያን ማግኘቱ በርካታ የስፖርት ወዳጅ ኢትዮጵያውያንን አስደንቋል እንዲሁም አስደስቷል።

በዚህ የኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ በዘርፉ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ መሆኗ ለየት ያለ ነገርን አምጥቷል። ኢትዮጵያ በአርባ አንድ ዓመታት ታሪኳ ውስጥ በወንዶች መሰናክል የተገኘ የመጀመሪያ ሜዳሊያ ሲሆን እስካሁን በአጠቃላይም ሦስት ሜዳሊያዎችን ብቻ ነው ማግኘት የቻለችው።

ከዚህም በተጨማሪ ለሜቻ አወዛጋቢ በሆነ ሁኔታ በመጨረሻው ደቂቃ ነው ኃይለ ማርያም አማረን ተክቶ የተወዳደረው። በውድድሩ ተሳታፊ በሚሆኑ አትሌቶች ዙሪያ ውዝግቡ የተፈጠረው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መካከል ነው።

በዘጠኝ ኦሊምፒኮች በዘርፉ ስትመራ የነበረችን የኬንያን የበላይነት ባበቃው በዚህ ውድድር የሞሮኮው ሱፊያን ኤል ባካሊ የወርቅ ሜዳልያ አግኝቷል።

ይህንን የውድድር ርቀት ለብዙ አሥርት ዓመታት ለረጅም ጊዜ ተቆጣጥረው ከነበሩት ከኬንያ አትሌቶች በተለየ፣ በዋናነት በረዥም ርቀት ሩጫዎች ለሚታወቁት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በመሰናክል ላይ ድል ማድረጋቸው በጣም ያልተለመደ ነው።

"በለሜቻ ግርማ በጣም ኮርቻለሁ። በሕይወቴ ውስጥ በ3000 ሜትር መሰናክል የምንወዳደር አይመስለኝም ነበር እና እስከ 100 ሜትር ድረስ አትሌቱ ተስፋ ሰጥቶናል። ብሩን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ" በማለት መላኩ ሃብቱ የተባለ የትዊተር ተጠቃሚ ተናግሯል።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

እሸቱ ቱራ በሞስኮ በተካሄደው የ1980 እአአ የኦሊምፒክ በ3000 ሜትር ውድድር ያሸነፈ የመጨረሻው ኢትዮጵያዊ ነበር። በዚህ ወቅት ኬንያ ራሷን ከውድድሩ አግልላላ ነበር።

ከአውሮፓውያኑ 1980 ወዲህ በተደረጉ የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ ማንም ከኬንያውያን ውጪ የወርቅ ሜዳሊያውን ወስዶ አያውቅም።

ከዚያ በፊት በሞንትሪያን ካናዳና በሞስኮ ሶቪየት ኅብረት በተደረጉት የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ ኬንያ ባለመሳተፏ እንጂ የዘርፉ የበላይነቷ ቀደም ካለው ጊዜ ሊጀምር ይችል ነበር።

ሰኞ ዕለት በተደረገው የቶኪዮው ኦሊምፒክ የ3ሺህ ሜትር ውድድር ላይም ኬንያውያን ቢያንስ ወርቁን እንደሚወስዱ ቢጠበቅም ሳይሆን ቀርቶ ሞሮኳዊው ሱፊያን ኤል ባካሊ ወርቁን በመውሰድ ኬንያውያን በውድድሩ ለዘመናት የያዙትን የበላይነት ሰብሮታል።

ይህም ሳይበቃ በሩጫ ውድድር የኬንያውያን ዋነኛ ተቀናቃኝ ከሆኑት ኢትዮጵያውያን መካከል ለሜቻ ግርማ የብር ሜዳሊያውን በመውሰዱ ኬንያዊው ቤንጃሚን ኪጌን የቀረችውን የነሐስ ሜዳሊያ ወስዷል።

በዚህም ሳቢያ ኬንያውያን በማኅበራዊ ሚዲያ ዎች ላይ ለመቀበል ስለተቸገሩት የመሰናክል ሩጫ ውጤት የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ ለውጤቱ በመላሸት ምክንያቱ ምን እንደሆነ እየጠየቁ ነው።

ኢትዮጵያ ግን ከረጅም ዓመታት በኋላ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ በለሜቻ ግርማ የብር ሜዳሊያ በማግኘት ወደ ውድድሩ ተፎካካሪነት መመለሷ ታይቷል።

ከዚህ በተጨማሪ እየተካሄደ ባለው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በ5000 ሜትር ውድድር በጉዳፍ ፀጋይ አማካኝነት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።

ባለፈው አርብ ደግሞ ሰለሞን ባረጋ በ10 ሺህ ሜትር በማሸነፍ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ውድድር ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቱ የሚታወስ ነው።

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ለቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዝግጅት ምን ይመስላል?