2020 በፎቶ ፡ ከኮሮናቫይረስ ጨረቃ ላይ ሰንደቅ አላማ እስከማስቀመጥ

2020 በፎቶ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ዓለም በኮሮናቫይረስ የተፈተነበት የፈረንጆቹ 2020 ሊያበቃ ነው። ዓመቱን ወደኋላ መለስ ብለን በፎቶ ስብስብ እንዲህ ቃኝተናል። ከጥር ወር እንጀምር።

ጥር

ቻይና ዉሃን ውስጥ የተቀሰቀሰው ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ የግድ ነው። ከወራት በፊት በመላው ዓለም የጭምብል እጥረት ተከስቶ ነበር።

ቻይና ቢጂንግ ውስጥ ከፕላስቲክ የተሠራ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አድርገው በረራ የሚጠባበቁ ታዳጊዎች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የካቲት

በከዋክብት ሳይንስ እጅግ አስደናቂ የሆነው ሙሉ ጨረቃ ቱርክ በሚገኘው ሰልሚዬ መስጂድ አቅራቢያ የታየው በዚህ ዓመት ነው።

በቱርክ፣ ኤድሪን የሚገኘውና በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተገነባው ሰልሚዬ መስጊድ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

መጋቢት

አብዛኛው ሰው ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ጓደኛ ለማግኘት እንደ ዙም ያሉ የተለያዩ መተግበሪያዎችን ለመጠቀም ተገዷል። ይህ ፎቶ ሆንግ ኮንግ ውስጥ የሚገኝ መምህር ለተማሪዎቹ በበይነ መረብ ትምህርት ሲያስተላልፍ የተነሳ ነው።

ሆንግ ኮንግ ውስጥ የሚገኝ መምህር ለተማሪዎቹ በበይነ መረብ ትምህርት ሲያስተላልፍ።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ሚያዝያ

ወረርሽኙን ለመከላከል አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ መርህ በዓለም ዙሪያ ተግባራዊ ሆኗል። አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ የካቶሊክ ቄስ ጸበል ለመርጨት ፈጠራ የተሞላበት መንገድን ተጠቅመዋል።

በርቀት ምዕመናንን ጸበል የሚረጩ የካቶሊክ ቄስ

የፎቶው ባለመብት, Jim West/ZUMA Wire/Shutterstock

ግንቦት

ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ እጅ መገደሉ በአሜሪካና በሌሎች አገራትም ዘረኝነትን የሚቃወም ንቅናቄ አስነስቷል።

ካሊፎርንያ፣ ሳክርመንቶ ውስጥ የተካሄ የተቃውሞ ሰልፍ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ሰኔ

እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ከመጣሉ በፊት ባርሴሎና ውስጥ በሚገኘው ግሬን ቴትሬ ደል ሊሲዮ ከሁለት ሺህ ለሚበልጡ ችግኞች ሙዚቃ ቀርቧል።

ሙዚቃ ለእፀዋት

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ሐምሌ

ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎችም የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች እንዲሁም በሕንድ፣ በፓኪስታን እና በኢራን ውስጥ የተስፋፋው የአንበጣ መንጋ ስጋት የሆነበት ዓመት ነው። በምስሉ ኬንያ ውስጥ አንዲት ሴት ሰብል በአንበጣ መንጋ ተወሮ ስትመለከት ይታያል።

ኬንያ ውስጥ አንዲት ሴት ሰብል በአንበጣ መንጋ ተወሮ ስትመለከት

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ነሐሴ

በሊባኖስ መዲና በቤይሩት የተከሰተው ፍንዳታ ኒውክሌር ነክ ካልሆኑ ፍንዳታዎች ሁሉ ትልቁ ነው። ከ200 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፎቶው የሚያሳየው ፒያኖ ተጫዋቹ ሬይመንድ ኢሳያም ከደረሰበት ጉዳት ባሻገር ቤቱን አጥቷል።

ፒያኖ ተጫዋቹ ሬይመንድ ኢሳያ በፈረሰ ቤቱ ውስጥ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

መስከረም

የብራዚል አማዞን ጫካ እጅግ በሚያስፈራ ሁኔታ የእሳት አደጋ ደርሶበታል። የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ቃጠሎው አሳስቧቸዋል። አንድ ጃጓር መዳፉ ተቃጥሎ ከእሳቱ ተርፏል።

ከእሳት ቃተሎ መዳፉ ተቃጥሎ የተረፈ አንድ ጃጓር

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ጥቅምት

ኮሮናቫይረስ ከፍተኛ ተጽዕኖ ካሳደረባቸው መካከል ነጋዴዎች በዋነኛነት ይጠቀሳሉ። በጣሊያን መዲና ሮም የሚገኘው ሬስቶራንት የንግዱ መቀዛቀዝ ተምሳሌት እንዲሆን አጽም አስቀምጧል።

በምግብ ቤት ውስጥ የተቀመጠ አጽም

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ኅዳር

በታይላንድ ተቃውሞ ከሚሳተፉ አንዱ ሚትሬ ቺቲንዳ ነው። ጸጉሩን የተቆረጠው ተቃውሞውን እንደሚደግፍ በሚጠቁም የሦስት ጣት ምልክት ነው። ይህ ምልክት 'ሀንገር ጌምስ' ከተባለው ፊልም የተወሰደ ነው።

የተቃውሞ ለመግለጽ በጸጉር ቁርጥ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ኅሣ

ቻይና ጨረቃ ላይ ሰንደቅ አላማዋን በመትከል ከዓለም ሁለተኛዋ አገር ሆናለች። በተጨማሪም ቼንጅ-5 የተባለው የሕዋ ጉዞ ከ44 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጨረቃ አለት አምጥቷል።

A flag of China on a pole on the lunar surface

የፎቶው ባለመብት, EPA