ልጁን ጨምሮ 160 የወሲባዊ ጥቃቶችን በማድረስ ሲፈለግ የነበረው ጣልያናዊ ተያዘ

ከ160 በላይ መድፈርና ወሲባዊ ጥቃቶችን አድርሷል ብላ ጀርመን ስትፈልገው የነበረው የ52 አመቱ ጣልያናዊ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ግለሰቡ በተለይም ታዳጊ ህፃናትን ሲደፍር እንደነበር የተገለፀ ሲሆን የፈረንሳይ ድንበርንም ሲያቋርጥ ነው የተያዘው።

የፈረንሳይ የወንጀለኞች አዳኝ ቡድን ቢኤንአርኤፍ ግለሰቡን ባለፈው ሳምንት አርብ ሩመርሺም ለ ሃውት በሚባል ቦታ ይዞታል።

ግለሰቡ ወሲባዊ ጥቃቱን በአብዛኛው ያደረሰው የፍቅር አጋሮቹ ታዳጊ ልጆች ላይ ሲሆን ለበርካታ አመታትም ሲፈፅመው የነበረ ነው ተብሏል።

መረጃውም እንደሚያሳየው ከጎሮጎሳውያኑ 2000-2014 ድረስ ነው ይህንን ተግባር ሲፈፅም የነበረው።

በጀርመን 122 ክሶች እንደተከፈቱበት ገልጿል።

ግለሰቡ ከተጠረጠረባቸው ወንጀሎች መካከል በልጁ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት በማድረስ ነው።

ለአመታትም ያህል ልጁን በመድፈር ተጠርጥሮም ክስ እንደቀረበበት የፈረንሳይ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ተጠርጣሪው ወደ ፈረንሳይ የገባው ከሶስት ሳምንት በፊት መሆኑን መረጃ የሰሙት የጀርመን ባለስልጣናት ለፈረንሳይ አሳወቁ።

በመጨረሻም ያለበት ትክክለኛ ቦታ የታወቀ ሲሆን ከሳምንት በኋላም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ኮልማር በሚባል የፈረንሳይ ግዛት የሚገኝ ሲሆን ወደ ጀርመንም ተላልፎ ይሰጣል ተብሏል።