አውሮፓ፡ ፖላንድ ጽንስ ማቋረጥን ከለከለች

ፖላንድ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የፖላንድ ፍርድ ቤት ጽንስ ማቋረጥን ከለከለ። ፍርድ ቤቱ ጽንሱ መሠረታዊ ችግር ቢኖርበትም ጽንሱን ማቋረጥ ሕጋዊ አይሆንም ብለዋል።

ፖላንድ ከዚህ ቀደምመ ከጽንጽ ማቋረጥ ጋር በተየያዘ ጥብቅ ክልከላ ሚደረግባት አውሮፓዊት አገር ስትሆን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከሁለት ምንያቶች ውጪ በማናቸውም ሁኔታ ጸንስ ማቋረጥን የሚከለክል ይሆናል ተብሏል።

በፖላንድ ጽንስ ማቋረጥ የሚፈቀደው የተረገዘው ጽንስ እናት ተደፍራ ከሆነ አልያም ከቅርብ ዘመድ የተረገዘ ከሆነ እንዲሁም ጽንሱ በወላዷ ላይ የጤና ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ሲታመንበት ነው።

የሰብዓዊ መብት ተካራካሪዎች መንግሥት በጽንስ ማቋረጥ መብት ላይ ሌላ ተጨማሪ ክልከላ እንዳያደርግ ሲጠይቁ ነበር።

የአውሮፓ ሕብረት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ "ለሴቶች መብት አሳዛኑ ቀን ነው" ብለውታል።

Presentational grey line

የቢቢሲው ዘጋቢ አዳም ዊስተን ከዚህ ቀደም በፖላንድ 98 በመቶ ጽንስ የሚቋረጠው ጽንሱ ከፍተኛ ሆነ ችግር አለበት በሚል ምክንያት ነበር። የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ እንዲቋረጥ መደረጉ በፖላንድ የጽንስ የማቋረጥ ተግባርን በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል ተብሏል።

አዳም እንደሚለው ከሆነ ጠንካራ ፖላንድ ጠንካራ ካቶሊክ ሃይማኖት ተከታዮች ይኑሯት እንጂ ጽንስ ማቋረጥን የሚደግፉት በርካቶች ናቸው። ከዚህ ቀደም የተሰሩ ጥናቶች አብዛኛዎቹ ፖላንዳዊያን ጽንስ ማቋረጥ የሚከለክሉ ሕጎችን እንደሚቃወሙ አመላክቷል።

እአአ 2016 ላይ አብዛኛዎቹ ሴቶች የነበሩበት ወደ 100ሺህ ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ጽንስ የማቋረጥ መብትን ሚጋፋ ሕግ መውጣት የለበትም በሚል አደባባይ ወጥተው ነበር።

አሁን ላይ በኮቪድ-19 ምክንያት ከ10 በላይ ሰዎች በአንድ ላይ መሰብሰብ ስለማይችሉ ፖላንዳዊያን የፍርድ ቤቱን ውሳኔ የሚቃወሙበት ሌላ አማራጭ እየፈለጉ ነው።

ባለፈው ዓመት ሕግን ተከትለው ጽንስ እንዲቋረጥ ያደረጉት ሴቶች ቁጥር 1ሺህ ገደማ ነበር። አንድ የሴቶች መብት ተከራካሪ ቡድን እንደሚለው ከሆነ ከ80ሺህ እስከ 120ሺህ የሚሆኑ ሴቶች ወደ ሌሎች አገር በመሄድ እርግዝናቸውን ለማቋረጥ ሙከራ አድርገዋል።