የባራክ ኦባማ መጽሐፍ በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ መጽሐፍ ጽፈዋል፡፡
የኅዳሩን የአሜሪካ ምርጫ አስታኮ ገበያ ላይ ይውላል ተብሏል፡፡
የአሜሪካ የመጀመርያው ጥቁር ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ መጽሐፉ የፕሬዝዳንት ዘመኔን ትውስታዎች በሐቅ ያሰፈርኩበት ነው ብለዋል፡፡
የመጽሐፉ ርእስ ኤ ፕሮሚስድ ላንድ ‹‹A Promised Land›› የሚል ሲሆን በኅዳር 17 የአሜሪካ ምርጫን በሁለት ሳምንት ተከትሎ ገበያ ላይ ይውላል። የዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ የነበሩት ባራክ አሜሪካንን ለሁለት የስልጣን ዘመን መርተዋል፡፡
የአሁኑ የዲሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪና የዶናልድ ትራምፕ ተፋላሚ የኦባማ ምክትል ሆነው ለ8 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ኦባማ በትዊተር ሰሌዳቸው ያሰፈሩት መልእክት ‹‹መጽሐፍ ጽፎ እንደመጨረስ ያለ መልካም ስሜት አላውቅም፡፡
በዚህኛው መጽሐፌ ጥሩ ስሜት ነው ያለኝ ብለዋል፡፡ የኦባማ መጽሐፍ ዳጎስ ያለ ነው፡፡ 768 ገጾች አሉት፡፡ ዝነኛው ፔንጉይን ራንደም ሀውስ ያሳተመው ሲሆን ወደ 25 ቋንቋዎች ተመልሷል ተብሏል፡፡
ኦባማ በመጽሐፋቸው አሜሪካንነና ዓለምን ችግር ውስጥ ከትቶ ስለነበረው ስለ ፋይናንስ ቀውስ፣ ስለ ጤና መድኅን እንዲሁም ስለ ቢን ላደን አገዳደል አውስተዋል፡፡ 44ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከዚህ ቀደም ሦስት መጻሕፍትን አበርክተዋል፡፡
ድሪምስ ፍሮም ማይ ፋዘር፣ ዘ ኦደሲቲ ኦፍ ሆፕ እንዲሁም ኦፍ ስሪ ሲንግ የሚል የልጆች መጽሐፍ አላቸው፡፡
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
ባለቤታቸው ክብርት ሚሼል ኦባማ የጻፈችው ቢካሚንግ የተሰኘ መጽሐፍ በ5 ወራት 10 ሚሊዮን ቅጂ በመሸጥ የዓለምን ክብረ ወሰን ይዟል፡፡












