መዓዛ መንግሥቴ፡ 'ቡከር' በተባለው ዓለም አቀፍ ሽልማት የታጩት አፍሪካዊ ሴት ደራሲዎች

መዓዛ መንግሥቴና ፂፂ ዳንጋሬምባ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

'ቡከር ፕራይዝ' በቀድሞ ስሙ 'ቡከር ሚክኮኔል ፕራይዝ' እና 'ዘ ማን ቡከር ፕራይዝ' በመባል ይታወቃል።

ዓለም አቀፍ የሽልማት ድርጅቱ በየዓመቱ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተፃፉ እና በዩናይትድ ኪንግደም ወይም በአየርላንድ የታተሙ ወጥ የልብ-ወለድ መፅሐፍትን አወዳድሮ ይሸልማል።

የሽልማት ድርጅቱ የተቋቋመው በጎርጎሮሳዊያኑ 1969 ሲሆን የመጀመሪያውን ሽልማት የሰጠውም በዚያው ዓመት ነበር።

ላለፉት ከ50 ዓመታት በላይም ይህንን ሲያደርግ ነው የቆየው።

በዘንድሮው ዓመትም ሁለት ሴት አፍሪካዊያን ደራሲዎች ለሽልማቱ ታጭተዋል።

በትውልድ ኢትዮጵያዊ- አሜሪካዊት መዓዛ መንግሥቴ አንዷ ናት። 'ዘ ሻዶው ኪንግ' [The Shadow king] በሚል ርዕስ የታተመው መፅሐፏ ነው ለሽልማቱ የታጨው።

መጽሐፉ መቼቱን ያደረገው የሁለተኛው አለም ጦርነት ጅማሮ የሚባለውና ፋሽስት ጣልያን ኢትዯጵያን በወረረችበት ወቅት ነው።

መፅሀፉ በጦርነቱ ውስጥ ሴት የነፃነት ታጋዮች ከፍተኛ ተጋድሎ ቢያደርጉም ምን ያህል ከታሪክ መዝገብ እንደተፋቁ የሚዘክርና የነበራቸውንም ግዙፍ ሚና ያወጣ ነው።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ መዓዛ በጎርጎሮሳዊያኑ 2010 የወጣው 'ቢኒዝ ዘ ላየንስ ጌዝ' [Beneath the Lion's Gaze] በተሰኘው መጽሐፏ ጨምሮ በሌሎች ሥራዎቿ ትታወቃለች።

በወቅቱም የጋርዲያን የአፍሪካ ምርጥ 10 መፅሐፍት ተርታ ተመድቧል።

መዓዛ እጩ መሆኗን በሰማች ወቅት በትዊተር ገጿ ላይ "ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም። ኦ ፈጣሪየ!" ስትል ነበር ደስታዋን የገለፀችው።

የ X ይዘትን ይለፉት, 1
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ, 1

ለሽልማቱ ከታጩት 6 መጽሐፍት መካከል ለሽልማቱ የታጨው ሁለተኛው መጽሐፍ በዚምባብዌያዊቷ ደራሲ ጺጺ ዳንጋሬምባ ድርሰት ነው።

መጽሐፏ ' ዚስ ሞርነብር ቦዲ' 'This Mournable Body' ይሰኛል። ከዚህ ቀደም ያወጣችውና ከፍተኛ እውቅናን ያተረፈላት 'ነርቨስ ኮንዲሽንስ' ተከታይ ነው።

ዚምባብዌ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ መውጣቷን ተከትሎ የመጣውን የድህረ-ቅኝ ግዛት ጭቆና፣ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት አገሪቱን ማሽመድመድና ካፒታሊዝም ጥምረት ምን ያህል መርዛማ እንደሆነም ያስቃኛል።

መፅሀፉ 'ሾና' ቤተሰቦች ላይ የሚያጠነጥን ነው። የሾና ህዝብ በደቡባዊ የአፍሪካ አካባቢዎች ይኖራሉ።

አሁን ላይ 10 ሚሊየን ገደማ ሾናዎች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተብሎ ይገመታል። አብዛኞቹ የሚኖሩት በዚምባብዌ ነው።

ጺጺ ለሽልማቱ በመታጨቷ ደስታ እንደተሰማት በትዊተር ገጿ ላይ አጋርታለች።

የ X ይዘትን ይለፉት, 2
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ, 2

ደራሲ ፣ የተውኔት ፀሐፊ እና ፊልም ሰሪዋ ጺጺ፤ ይህን መጽሐፏን ከሁለት ዓመታት በፊት ቢቢሲ ዓለምን ከለወጡ 100 መጽሐፍት አንዱ አድርጎ መርጦት ነበር።

ባለፈው ዓመት እንግሊዛዊ ናይጀሪያዊቷ ደራሲ ቤርናዲኔ ኢቫሪስቶል ሽልማቱን በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት ነበረች።

ከዚህ ቀደም ናዲን ጎርዲመር፣ ጀም ኮትዜ እና ቤን ኦኪሪን ጨምሮ ሌሎችም የሽልማቱ አሸናፊ ሆነዋል።

ለዚህ ዓመቱ ሽልማት እጩ የሆኑት ሌሎቹ መፅሐፍት፦

•በዲያኔ ኩክ የተፃፈው 'ዘ ኒው ወይልደርነስ' [The New Wilderness]

•በአቭኒ ዶሽ የተፃፈው 'በርንት ሹገር' [Burnt Sugar]

•በብራንደን ቴይለር 'ሪል ላይፍ' [Real Life]

•በዳግላስ ስቱዋርት የተፃፈው 'ሹጌ ቤን' [Shuggie Bain]

አሸናፊዎቹ 64 ሺህ ዶላር ሽልማት ይበረከትላቸዋል ተብሏል።

በእንግሊዝኛ የተፃፈ እና በዩናይትድ ኪንግደም የታተመ ማንኛውም መፅሐፍ በውድድሩ ላይ መሳተፍ ይችላል።