የውጭ ጉዳይ ሚንሰትሩ ኢትዮጵያ የአባይን 'ሐይቅ' ለፈለገችው ዓላማ ልትጠቀም ትችላለች አሉ

የፎቶው ባለመብት, EPA
የኢትዮጵያ የውጨ ጉዳይ ሚንሰትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ የአባይን 'ሐይቅ' ለፈለገችው ዓላማ ልትጠቀም ትችላለች አሉ።
የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ይህንን ያሉት በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት አጭር መልዕክት ሲሆን ኢትዮጵያ የአባይን ውሃ አስፈላጊ ነው ላለችው ዓላማ ልትጠቀምበት እንደምትችል አመልክተዋል።
ባሰፈሩት ጽሁፍ "አባይ ወንዝ ነበር ተገርቶ ወንዝም ሐይቅም ሆነ" ያሉት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ፤ "ከእንግዲህ በወንዝነቱ ይፈሳል። በሐይቅነቱ ኢትዮጵያ ለፈለገችው ልማት ሁሉ ለመዋል እጅ ሰጥቷል። እውነትም አባይ የእኛ ሆነ!!" ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

የፎቶው ባለመብት, Twitter
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ይህን ያሉት፤ ኢትዮጵያ ትናንት ምሽት በመጀመሪያው ዓመት ለመሙላት የታቀደው የውሃ መጠን መሞላቱን ይፋ ካደረገች በኋላ ነው።
አሁን ያለው የዝናብ ሁኔታ የህዳሴ ግድቡን በውሃ ለመሙላት አመቺ እንደነበረና በመጀመሪያው ዓመት ለመሙላት የታቀደው የውሃ መጠን ሞልቶ በግድቡ አናት ላይ እየፈሰሰ መሆኑን የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።
የጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ እንደተገለጸው፤ በዚህ ዝናባማ ወር ውስጥ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በነበረው መልካም የዝናብ ሁኔታ በመጀመሪያው ዓመት ለመሙላት የታቀደው የውሃ መጠን ሞልቶ፤ ውሃው በግድቡ አናት ላይ እየፈሰሰ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የግድቡ የውሃ ሙሌት ሐምሌ አጋማሽ ላይ እንደሚጀምር ቁርጠኝነቱን ሲያሳውቅ ነበር።
ግብጽ እና ሱዳን በበኩላቸው በግድቡ ዙሪያ ሙሉ ስምምነት ሳይደረስ ውሃ መሙላት መጀመር ለድርድር ሂደት እክል ይሆናል እያሉ ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 1
የሦስቱ አገራት መሪዎች እና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሰብሳቢ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ የሚመሩት ውይይት አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቦ መጠናቀቁ ተነግሯል።
ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ ውይይቶችን በማድረግ አጠቃላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስማምተዋል ብሏል መግለጫው።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳም የተካሄደው ውይይት ውጤታማ እንደነበረ ጠቅሰው፤ የሦስቱ አገራት ውይይት ይቀጥላል ካሉ በኋላ፤ የአፍሪካዊያንን ችግር በአፍሪካ መፍትሄ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት በስበሰባው የተሳተፉትን አካላት አመስግነዋል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 2
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንሰትር አብደላ ሃምዱክ በተመሳሳይ የተደረገው ውይይት ስኬታማ እንደነበረ ገልጸዋል። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር ግድቡ የሚሞላበትን እና የሥራው ሂደት በተመለከተ ድርድሮች እንዲቀጥሉ ተግባብተናል ብለዋል።
አሃረም ኦላይን የፕሬዝደንት አል-ሲሲን ቢሮ ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ግብጽ ከኢትዮጵያ እና ከሱዳን ጋር ግድቡ የሚሞላበት እና የግድቡን አሰራር በተመለከተ ከስምምነት ለመድረስ ተስማምታለች ብሏል።
የሚፈልጉት ይዘት የለም
በ Facebook ተጨማሪ ይመልከቱቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም.የ Facebook ይዘት መጨረሻ
መግለጫውን ተከትሎ በርካቶች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የእንኳን ደስ አለን መልዕክት ሲለዋወጡ አምሽተዋል።
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍጹም አረጋ፤ ግድቡ ውሃ መያዝ መጀመሩን በመግለጽ በፌስቡክ ገጻቸው የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላለፈዋል።
የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ 6ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ይሆናል። 65 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንም የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደሚያገኙ ይታመናል።















