ኮሮናቫይረስ፡ የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ባለሙያዎች መልዕክት ስለ ኮሮናቫይረስ

የፎቶው ባለመብት, VIDEO
የተለያዩ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በጋራ በመሆን ስለ ኮሮናቫይረስ ግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶች በተንቀሳቃሽ ምስሎች በመስራት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን እየለቀቁ መሆኑን የቡድኑ አባል የሆነው የፊልም ባለሙያ ክብረዓለም ፋንታ ለቢቢሲ ገለጸ።
እነዚህ "እጅ አንስጥ እጅ እንንሳ" እና "አብረን እንጂ ብቻችንን አንድንም" የሚሉ መልዕክቶች የያዙ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ናቸው።
አቶ ክብረዓለም ከእርሱ ባሻገር ሚካኤል ሚሊዮን፣ አክሊሉ ገብረመድኅን፣ ሰው መሆን ይስማው መኖራቸውን በመግለጽ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪ የኪነጥበብ ባለሙያዎች መልዕክቱን በማስተላለፍም መሳተፋቸውን ይናገራል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 1
ይህ በተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን የተሰራጨው የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ፣ በሲዳምኛና በጌዲዮኛ መሰራቱን አክሊሉ ለቢቢሲ አረጋግጧል።
ባለሙያዎቹን በማኅበራዊ ሚዲያ ጥሪ በማቅረብ ለማሰባሰብ ሙከራ መደረጉን በመግለጽ በቂ ባለሙያ በበጎ ፈቃደኝነት ባለመምጣቱ የጃኖ ባንድ አባሉን ኃይሉ መርጋንና ተዋናይት ማኅደር አሰፋን በግል በማናገር እንዲሳተፉ ማድረጋቸውን ይጠቅሳል።
ይህንን የግንዛቤ ማስጨበበጫ መልዕክትን ለማዘጋጀት ምክንያታቸው ምን እንደሆነ ያብራራው ክብርዓለም፤ በርካታ ሰዎች ስለኮሮናቫይረስ መረጃው ቢኖራቸውም መዘናጋት በማየታቸውና የጉዳዩ አሳሳቢነትን አቅልሎ የማየት ጉዳይ በመኖሩ ለመስራት መወሰናቸውን ይናገራል።
ክብረዓለም የሌሎችን አገራት ተሞክሮም በመጥቀስ የተለያዩ የተሳሳቱ ግንዛቤዎች በማኅበረሰቡ ውስጥ መኖራቸውና ይህም በፍጥነት መታረም እንዳለበት ያስረዳል።
አንዳንድ ሰዎች ወጣቶችን አይነካምና አፍሪካዊያንን አይዝም የሚሉ ተሳሳቱ አመለካከቶችን መስማታቸውና የሚናገረው አክሊሉ፤ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ሰምቶ የምር በመውሰድ ተግባራዊ ማድረግ ላይ ዳተኝነት በመመልከታቸው በዚህ መንገድ መልዕክቱን ለማስተላለፍ መወሰናቸውን ያስረዳል።
የመጣውን ነገር በጋራ ካልሆነ ለብቻችን አንችለውም የሚለው ክብረዓለም፤ ሁሉም ተጽዕኖ ማሳደር የሚችል ሰው የበኩሉን በኃላፊነት መማድረግ እንዳለበት ያስረዳል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 2
አክሊሉ እንደሚለው ሁሉንም የጥንቃቄና፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶች እነርሱ መስራት እንደማይፈልጉ በመጥቀስ ስልክ ያላቸው እና ተሰሚነቱ ያላቸው ግለሰቦች በስልካቸው አጫጭር መልዕክቶችን በመቅረጽ ለተከታዮቻቸው ቢያስተላልፉ ይህ ወረርሽኝ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በማድረግ በኩል አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ።
በአሁኑ ሰዓት መስማት ለተሳናቸው በምልክት ቋንቋ እንዲሁም ለተለያዩ ኃይማኖት ተከታዮች መልዕክቶችን እያዘጋጁ መሆኑን በመጥቀስ ሁሉም ሰው መረጃውን በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲያስተላልፉ ጥሪያቸውን ያስተላልፋሉ።
ተንቀሳቃሽ ምስሉን ማንኛውም ግለሰብ ሆነ ተቋም በባለቤትነት ወስዶ መጠቀም እንደሚችል በመግለጽም ምስሎቹን ለመስራት አራቱ ባለሙያዎች ከኪሳቸው በማውጣት ወጪውን እንደሸፈኑ ገልጿል።













