የኬፕታውን ባለስልጣናት ሃገር በቀል ያልሁኖ ዛፎችን ሊያስወግዱ ነው የሚሉና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

ባህር ዛፍ

የፎቶው ባለመብት, DEA / L. ROMANO

አፍሪካ

• ዚምባብዌ ውስጥ አንድ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በእሳት ተቀጣጥሎ የ42 ሰዎች ህይወት አለፈ።

እሳቱ የተነሳው አንድ ተሳፋሪ የያዘው የሲሊንደር ጋዝ ፈንድቶ እንደሆነ ተገልጿል።

• ሞሮኮ በሰአት 320 ኪሎሜትር የሚጓዘውን በአፍሪካ ፈጣኑን ባቡር ዛሬ አስመረቀች።

ሙሉ ወጪው 2.4 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፤ ለማጠናቀቅ ሰባት ዓመት ፈጅቷል።

• አልፕስ ተራሮችን አቋርጠው ወደ ፈረንሳይ ሊገቡ የነበሩ 10 አፍሪካውያን ወጣቶች በበረዶ ምክንያት በፖሊስ ተያዙ።

ወጣቶቹ በረዶው ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው መንቀሳቀስ አልቻሉም።

• በደቡብ አፍሪካ የኬፕታውን ከተማ ባለስልጣናት እንደ ባህር ዛፍ ያሉ ሃገር በቀል ያልሆኑ ዛፎችን ልናስወግድ ነው ብለዋል።

ምክንያታቸው ደግሞ ተክሎቹ ከፍተኛ የውሃ እጥረት እንዲከሰት አድርገዋል የሚል ነው።

• አሜሪካ አፍሪካ የምታሰማራቸውን ወታደሮቿን በሚቀጥሉት ዓመታት 10 በመቶ ልትቀንስ ነው።

7200 የአሜሪካ ወታደሮች በአፍሪካ የሚገኙ ሲሆን፤ ከዚህ በኋላ የመረጃ ድጋፍና ምክር ላይ ትኩረት ይደረጋል ተብሏል።

ጣልያን

• ጣልያን ውስጥ በቁንጅና ውድርድ የመጨረሻ ዙር የደረሰች ሞዴል ላይ አሲድ የደፋው ግለሰብ የ15 ዓመት እስራት ተፈረደበት።

ጌሲካ ኖታሮ የተባለችው ሴት አሁን ከጉዳቷ አገግማ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሆናለች።

አሜሪካ

• አሜሪካ ውስጥ ለአንድ የጎዳና ተዳዳሪ 400 ሺ ዶላር እርዳት ያሰባሰቡት ባልና ሚስት ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ሰዎቹ ከጎዳና ተዳዳሪው ጋር በመተባበር ገንዘብ ለማግኘት የውሸት ታሪክ ፈጥረዋል በሚል ክስ ነው ፍርድ ቤት የቀረቡት።

ህንድ

• ህንድ ውስጥ እናታቸው በቅርቡ በሰዎች የተገደለችባቸው ሁለት ነብሮች ጥቃት ከማድረሳቸው በፊት እየተፈለጉ ነው።

እናትየው 13 ሰዎችን የገደለች ሲሆን ለሁለት ዓመታት ስትፈለግ ነር።

ካምቦዲያ

• የቀድሞው የካምቦዲያ ፕሬዝዳንትና ምክትላቸው በዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

የ87 እና የ92 ዓመት የቀድሞ ባለስልጣናቱ ሙስሊሞችንና ቬትናማውያንን በመጨፍጨፍ ነው የከተሰሱት።