ዶናልድ ትራምፕ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ጄፍ ሴሽንስን አባረሩ

ዶናልድ ትራምፕ ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ጄፍ ሴሽንስን አባረሩ

የፎቶው ባለመብት, AFP

የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ጄፍ ሴሽንስ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተባረሩ።

''ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ጄፍ ሴሽንስ ለአገልግሎታቸው እናመሰግናለን፤ መልካም ሁሉ አንዲገጥማቸው እንመኛለን!'' ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ዶናልድ ትራምፕ አስፍረዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያ ጋር በተያያዘ የተካሄደባቸውን ምርመራ ጄፍ ሴሽንስን በተደጋጋሚ ይወቅሱ ነበር።

ትራምፕ ጠቅላይ አቃቢ ሕጉ በፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ኃላፊ ማቲው ዊትኬር እንደሚተኩ አስታውቀዋል።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

የአላባማ ሴናተር እና ቀደም ሲል የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ የነበሩት ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ጄፍ ሴሽንስ ለዋይት ሃውስ ባስገቡት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ይህ የሥራ መልቀቅ ውሳኔ ከእራሳቸው እንዳልመጣ በግልጽ አስፈረዋል።

''ክቡር ፕሬዚዳንት፤ በእርስዎ ጥያቄ መሰረት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብቻለሁ'' ሲሉ ቀኑ ባልተገለጽ ደብዳቤ ላይ ጽፈዋል።

እኤአ 2017 ጄፍ ሴሸንስ የሩሲያ ምርመራ በሚካሄድበት ወቅት ራሳቸውን ገሸሸ በማድረጋቸው ዶናልድ ትራምፕ የሕግ አሰፈጻሚ አካሉን አምርረው ሲወቅሱ ነበር።

ምረመራው የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳና በወቅቱ ሞስኮ የነበራትን ተሳትፎ ለማወቅ የተካሄደ ነበር።

በዶናልድ ትራምፕ ውሳኔ ዲሞክራቶች ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተዋል። ዲሞክራቶች አዲሱ ተሿሚ ሹመታቸው በሴኔቱ መጽደቅ አለበት ሲሉ ይሞግታሉ።