ትራምፕ "በአሜሪካ ለወጣቶች አስፈሪና ፈታኝ ጊዜ ነው"

ፕሬዝዳንት ትራምፕ እጃቸውን በማውለብለብ ሰላምታ ሲሰጡ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ትራምፕ በአሜሪካ ጊዜው ለወጣቶች አስፈሪና ፈታኝ ነው አሉ።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት አሁን ወቅቱ ለወጣቶች አስፈሪና አስቸጋሪ ጊዜ ነው ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በዋይት ሐውስ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

"ሕይወቴን በሙሉ ስሰማ የኖርኩት 'ጥፋተኛ መሆንህ እስካልተረጋገጠ ድረስ ነፃ ነህ ' የሚለውን ነው፤ አሁን ግን 'ንፁህ መሆንህ እስኪረጋገጥ ድረስ ወንጀለኛ ነህ'፤ ይህ ደግሞ በጣም በጣም አስቸጋሪ ፍረጃ ነው" ብለዋል።

"በአሜሪካ ወጣቶች ላላጠፉት ጥፋት ወንጀለኛ ሆኖ መገኘት ፈታኝ ጊዜ ነው"

ይህ የትራምፕ አስተያየት የተሰማው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ሹመት በእጩነት ያቀረቧቸውና በወሲብ ቅሌት ለተጠረጠሩት ብሬት ካቫናህ ያላቸውን ድጋፍ በድጋሚ በገለፁበት ወቅት ነው።

ዳኛ ካቫናይ ላይ የሚሰጠው ድምፅ የዘገየው እርሳቸው የካዱትን የወሲብ ቅሌት ተግባር ኤፍ ቢ አይ እያጣራ በመሆኑ ነው።

ትራምፕ የሀገሪቱ ሃገሪቱ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሹመቱን እንደሚያፀድቀው ሙሉ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ይህ ሹመት ከፀደቀ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድቤት ስልጣን ለረጅም ዓመታት በወግ አጥባቂዎቹ እጅ ይቆያል ማለት ነው።

ፕሬዝዳንቱ የኤፍ ቢ አይ የምርመራ ውጤትን እየጠበቁ መሆኑን ገልፀው ምንም ዓይነት ነገር ማቋረጥ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል።