ፌስቡክ ከሁለት ሊንክ በላይ ለማጋራት ደንበኞቹን ሊያስከፍል ነው

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ፌስቡክ አንዳንድ ተጠቃሚዎች በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኩ ላይ ሊለጥፉ የሚችሉትን የበይነመረብ ሊንክ ብዛት የሚገድብ አሠራር እየሞከረ ነው።
በየዑናይትድ ኪንግደም እና በአሜሪካ የሚገኙ አንዳንድ ተጠቃሚዎች ሊያጋሯቸው የሚችሉትን የሊንክ መጠን በሚመለከት መልዕክት እየደረሳቸው ይገኛል።
ከተቀመጠው ሊንክ በላይ ለማጋራት በወር 9.99 ፓውንድ የአባልነት ከፍያ መፈጸም እንዳለባቸው ታውቋል።
ሜታ "ሊንኮችን በብዛት ማጋራት መቻል ለደንበኝነት ተመዝጋቢዎች ተጨማሪ እሴት ስለመጨምሩ ለመረዳት የሚደረግ አነስተኛ ጥናት ነው" ሲል ገልጾታል።
የማኅበራዊ ሚዲያ ባለሙያ የሆኑት ማት ናቫራ ኩባንያው በመድረኮቹ ላይ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት የሚያደርገውን ጥረት ያመለክታል ብለዋል።
"ይህ ከደንበኝነት ምዝገባ ጀርባ ያለደንበኛን ከማቆየት ጋር የሚያያዝ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ሜታ ቬርፋይድ የፌስቡክ እና የኢንስታግራም ተጠቃሚዎችን ሰማያዊ ምልክት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን "የተሻሻለ" ድጋፍ እና ከተመሳሳይ ሐሰተኛ አካውንት ጥበቃ ይሰጣቸዋል።
ናቫራ እንዳሉት ከሆነ ኩባንያው እንደዚህ ዓይነት አሠራሮች አስቀድሞ ዋጋ ስላስቀመጠ፣ አሁን ለይዘት ስርጭት እና "የሰዎችን የመላክ መሠረታዊ ችሎታ" ወደ ሌሎች የኢንተርኔት ክፍሎች ተመሳሳይ ነገር በማድረግ ላይ ነው።
ከታህሳስ 16 ጀምሮ በወር ሁለት ሊንኮችን ብቻ ማጋራት እንደሚችሉ ማሳወቂያ ከደረሳቸው ከመካከል ናቫራ ይገኙበታል።
"የይዘት ፈጣሪ ወይም የንግድ ተቋም ከሆኑና ፌስቡክ የእድገትዎ ወይም የደንበኞችዎ ስትራቴጂያዊ አካል ከሆነ አካሄዱ የዋጋ መለያ አለው ብዬ አስባለሁ" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
"ለተወሰነ ጊዜ እየተሄደበት ያለ አቅጣጫ ቢሆንም ይህ አዲስ ነገር ነው።"
"ከባድ እውነታ"
እንደ ሊንክዲን ካሉ ሌሎች ማኅበራዊ መድረኮች ሁሉ ሜታም ተጠቃሚዎቹ ተጨማሪ አገልግሎትን ለማግኘት ራሳቸውን ቬሪፋይ እንዲያደርጉ አበረታቷል።
ኤለን መስክ ትዊተርን በ2022 ከገዛ በኋላ ቬሪፋይ የማድረጊያ መንገዱን አሻሽሏል። የኤክስ ሰማያዊ ምልክቶችን በክፍያ ማግኘት የሚቻል ሲሆን ተጨማሪ የተሻለ ጥቅም እንዲያገኙ አድርጓል።
ይህ አወዛጋቢ ሆኖ ከመገኘቱም ባለፈ የአውሮፓ ኅብረት በታህሳስ ወር 120 ሚሊዮን ዩሮ ቅጣት ጥሎበታል።
የማርክ ዙከርበርጉ ሜታም ብዙም ሳይቆይ ተመሳሳይ አሠራር አስተዋውቋል።
የመስክን ለውጦች በማስተጋባት ተጠቃሚዎች አሳሳች ጉዳይ ሲገጥማቸው የሚያሳውቅ አካሄድ እንደሚያስተዋውቅ ገልጿል።
ፌስቡክ ቴክ ክራንች ለተሰኘው የቴክኖሎጂ መገናኛ ብዙኃን እንደገለጸው ሙከራው ለተመረጡ ጠቃሚዎች ተዘርግቷል።
አሠራሩ በመድረኩ ላይ ያለውን ይዘት ለማስተዋወቅ እና በተጠቃሚዎች ላይ እንዴት እንደሰራ ግንዛቤ ለማግኘት በብዙ ፈጣሪዎች እና ንግዶች ይመረጣል።
"ለፈጣሪዎች ፌስቡክ አስተማማኝ የደንበኛ መሣቢያ አለመሆኑን እና ሜታ ከተጠቃሚዎች እየራቀ መሆኑን የሚያሳይ ከባድ እውነታን ያሳያል" ሲሉ ናቫራ ተናግረዋል።
ይህም "ሜታ ሁልጊዜ ለሜታ ቅድሚያ እንደሚሰጥ" ለማስታወስ አገልግሏል ብለዋል።
"እንደዚህ ያሉ ሙከራዎች በማንኛውም መድረክ ላይ ከመጠን በላይ ጥገኛ መሆን ለምን አደገኛ እንደሆነ ያሳያል" ብለዋል።















