የሚሊኒየም አዳራሽ 18 ዓመታት - የዐቢይ እና ኢሳያስ መገናኘት፣ የቢዮንሴ ኮንሰርት፣ የኮቪድ ሕክምና ማዕከልነት

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የንባብ ጊዜ: 5 ደቂቃ

የዛሬ 18 ዓመት ኢትዮጵያ ሚሊኒየምን ለመቀበል ሽር ጉድ ስትል ነበር ሚሊኒየም አዳራሽ የተገነባው።

በጊዜያዊነት የተገነባው ሚሊኒየም አዳራሽ፤ ሁለት አሥርታት ለሚጠጋ ጊዜ በርካታ ሰዎች የሚታደሙባቸው ኹነቶች ዋነኛ ማዘጋጃ ሥፍራ ሆኖ ቆይቷል።

ሚሊኒየም አዳራሽ ከሙዚቃ ኮንሰርት እስከ ዐውደ ርዕይ፣ ከሃይማኖታዊ ክንውን እስከ ፖለቲከኞች ንግግር አስተናግዷል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማዕከልነቱም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሥልጣን መያዝ በኋላ ወደ አገር ቤት የተመለሱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በአዳራሹ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ከእነዚህም መካከል ጀዋር መሐመድ ይጠቀሳል።

አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለረዥም ጊዜ ተማሪዎቹን በድምቀት ያስመርቅ የነበረው በዚህ አዳራሽ ነበር።

ሚሊኒየም አዳራሽ፤ ልዩ በሆነ አጋጣሚ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና ቀዳማዊት እመቤት አዜብ መስፍን በሱዳን ሙዚቃ ሲደንሱም አሳይቶናል።

በ2017 ዓ. ም. በሚሊኒየም አዳራሽ መጠነኛ የእሳት አደጋ ተነስቶም ነበር።

በ20ሺህ ስኩዌር ሜትር ላይ ያረፈው ሚሊኒየም አዳራሽ እስከ 25,000 ሰዎች እንደሚያስተናግድ ይነገርለታል።

የሚሊኒየም አዳራሽን የሚያስተዳድረው በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሥር የሚገኘው አዲስ ፓርክ ነው።

ሚሊኒየም አዳራሽ ፈርሶ እንደ አዲስ እንደሚገነባ ሚድሮክ ይፋ አድርጓል። መልሶ ግንባታው ለ32ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ (ኮፕ27) የሚደረገው ዝግጅት አካል እንደሆነም ተገልጿል።

ለኮፕ32 የሚያገለግሉ ሆቴሎችን የማስፋፋት ዓላማ እንዳለው የገለጸው ሚድሮክ፤ በሚሊኒየም አዳራሽ የማርዮት ሞክሲ ሆቴልን እንደሚገነባ አስታውቋል።

ያለፉትን 18 ዓመታት መለስ ብለን በሚሊኒየም አዳራሽ የተከናወኑ ጉልህ ክንውኖችን ስንቃኝ ሦስት ማሳያዎችን መውሰድ እንችላለን።

ዐቢይ እና ኢሳያስ በሚሊኒየም

ከስምንት ዓመት ገደማ በፊት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአዲስ አበባ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያደርጉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሚሊኒየም አዳራሽ ተገኝተው ነበር።

መሰናዶው "የኢትዮ-ኤርትራ ሰላም ማብሰሪያ" መድረክ ተብሎ ተሰይሞ እንደነበር ይታወሳል።

ጦርነትም ሰላምም ሳይታይበት የቆየው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን መምጣት በኋላ ተለውጧል።

አሁን ላይ አገራቱ ቢቃቃሩም በወቅቱ ሁለቱ መሪዎች የሞቀ ወዳጅነት ነበራቸው።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2010 ዓ.ም. ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር በሚሊኒየም አዳራሽ ሲገኙ ከታዳሚዎች ከፍተኛ ድጋፍ ተችሯቸው ነበር።

በሚሊኒየም አዳራሽ በነበረው ኮንሰርት ወደ 5,000 ሰዎች መታደማቸው ተገልጾ ነበር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በሚሊኒየም አዳራሽ በነበረው የቢዮንሴ ኮንሰርት ወደ 5,000 ሰዎች መታደማቸው ተገልጾ ነበር

ቢዮንሴ በሚሊኒየም

ቢዮንሴ ለኢትዮጵያ ሚሊኒየምን አዲስ አበባ ከተገኙ ገናና ድምጻዊያን አንዷ ናት። በሚሊኒየም አዳራሽ በነበረው ኮንሰርት ወደ 5,000 ገደማ ሰዎች መታደማቸው ተገልጾ ነበር።

ከቢዮንሴ በፊት ዝነኛው ራፐር ሉዳክሪስ ሙዚቃውን አቅርቧል። ሰፊ ትኩረት ያገኘችው ግን ቢዮንሴ ነበረች።

ቢዮንሴ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አጠገብ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መገኘቷ በርካቶችን ያነጋገረ ክስተት ነበር።

ቢዮንሴ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ደማቅ አሻራ ካላቸው ድምጻዊያን መካከል በግንባር ቀደምነት ትጠቀሳለች።

በወቅቱ ዝነኛ የነበረው የአሜሪካው 'ብላክ አይድ ፒስ' የሙዚቃ ቡድን አርቲስቶች ኮንሰርታቸውን ያቀረቡት በዚሁ አዳራሽ ነበር።

ባለፉት ዓመታት በሚሊኒየም አዳራሽ አስቴር አወቀ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ፣ መሐሙድ አሕመድ እና ሌሎችም አንጋፋ ድምጻውያን አቀንቅነዋል። ከአፍሪካውያን ድምጻውያን መካከል ዴቪዶ እና ፒ-ስኩዌር ይጠቀሳሉ።

ሚሊኒየም አዳራሽ የኮሮናቫይረስ ሕሙማን መቆያ ሆኖ አገልግሏል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሚሊኒየም አዳራሽ የኮሮናቫይረስ ሕሙማን መቆያ ሆኖ አገልግሏል

የኮሮናቫይረስ ማዕከል የሆነው ሚሊኒየም አዳራሽ

ከስድስት ዓመት በፊት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሲከሰት ሚሊኒየም አዳራሽ ሕሙማንን አስተናግዷል።

የሚሊኒየም የኮቪድ-19 ማዕከል ዋና ኃላፊ ሆነው ያገለገሉት ዶ/ር ውለታው ጫኔ በወቅቱ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት፤ አዳራሹ ለጤና ሚኒስቴር በነጻ ከተሰጠ በኋላ ሥራ ጀምሯል።

አዳራሹ 200 ሜትር በ170 ሜትር ገደማ ስፋት ቢኖረውም ለሕክምና አገልግሎት የተዘጋጀ አለመሆኑ ፈታኝ እንደነበር ዶክተሩ ገልጸዋል።

በሒደት የሕሙማን ለይቶ ማቆያ ክፍሎች በማዘጋጀት ሕክምና ተሰጥቷል። አዳራሹን እንደ ተለዋጭ ሆስፒታል ሲጠቀሙ መነሻ አድርገው የወሰዱት ኒው ዮርክ እና ጣሊያንን እንደነበር ተናግረዋል።

በቫይረሱ ሳቢያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከቫይረሱ ማገገም የቻሉ ሰዎች ከሚሊኒየም አዳራሽ ሲወጡ የሕክምና ባለሙያዎች ያደርጉላቸው የነበረው ሽኝት የሚዘነጋ አይደለም።

የሚሊኒየም ትውስታ በምሥል

ሚሊኒየም አዳራሽ በግንባታ ላይ ሳለ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሚሊኒየም አዳራሽ በግንባታ ላይ ሳለ
ከዘጠኝ ዓመት በፊት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአዲስ አበባ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያደርጉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሚሊኒየም አዳራሽ ተገናኝተው ነበር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ከዘጠኝ ዓመት በፊት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአዲስ አበባ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያደርጉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሚሊኒየም አዳራሽ ተገናኝተው ነበር
ቢዮንሴ ለኢትዮጵያ ሚሌኒየምን አዲስ አበባ ከተገኙ ገናና ድምጻዊያን አንዷ ናት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ቢዮንሴ ለኢትዮጵያ ሚሊኒየም አዲስ አበባ ከተገኙ ገናና ድምጻዊያን አንዷ ናት
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ከቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር አል-በሽር እና ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር የኢትዮጵያ ሚሌኒየም ሲከበር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ከቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር አል-በሽር እና ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር የኢትዮጵያ ሚሊኒየም ሲከበር
ከአራት ዓመት በፊት አሸንዳ በአዳራሹ ሲከበር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ከአራት ዓመት በፊት አሸንዳ በአዳራሹ ሲከበር
ከአራት ዓመት በፊት አሸንዳ በአዳራሹ ሲከበር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ከአራት ዓመት በፊት አሸንዳ በአዳራሹ ሲከበር
ሚሌኒየም አዳራሽ የኮሮናቫይረስ ሕሙማን መቆያ ሆኖ አገልግሏል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, አዳራሹ 200 ሜትር በ170 ሜትር ገደማ ስፋት ቢኖረውም ለሕክምና አገልግሎት የተዘጋጀ አለመሆኑ ፈታኝ እንደነበር የማዕከሉ ዋና ኃላፊ ተናግረው ነበር
ሚሌኒየም አዳራሽ የኮሮናቫይረስ ሕሙማን መቆያ ሆኖ አገልግሏል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, አዳራሹን እንደ ተለዋጭ ሆስፒታል ሲጠቀሙ መነሻ አድርገው የወሰዱት ኒው ዮርክ እና ጣሊያንን እንደነበር ተናግረዋል
በየዓመቱ ለገና የሚካሄደው ባዛር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በየዓመቱ ለገና የሚካሄደው ባዛር
በየዓመቱ ለገና የሚካሄደው ባዛር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በየዓመቱ ለገና የሚካሄደው ባዛር
በየዓመቱ ለገና የሚካሄደው ባዛር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በየዓመቱ ለገና የሚካሄደው ባዛር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወጣቶች ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወጣቶች ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በአዳራሹ የኢፍጣር ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በአዳራሹ የኢፍጣር ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በአዳራሹ የኢፍጣር ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በአዳራሹ የኢፍጣር ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል
‘አዲስ ፋሽን ዊክ’ በአዳራሹ የሚከናወን የፋሽን ትዕይት ነበር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, 'አዲስ ፋሽን ዊክ' በአዳራሹ የሚከናወን የፋሽን ትዕይት ነበር
‘አዲስ ፋሽን ዊክ’ በአዳራሹ የሚከናወን የፋሽን ትዕይት ነበር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, 'አዲስ ፋሽን ዊክ' በአዳራሹ የሚከናወን የፋሽን ትዕይት ነበር
የሚሊኒየም ከአዳራሹ በተጨማሪ ግቢ ውስጥ የሙዚቃ ኮንሰርቶች ይካሄዱበት ነበር

የፎቶው ባለመብት, Rophnan

የምስሉ መግለጫ, የሚሊኒየም ከአዳራሹ በተጨማሪ ግቢ ውስጥ የሙዚቃ ኮንሰርቶች ይካሄዱበት ነበር
በሚሌኒየም አዳራሽ መዝሙር እና ስብከትን ጨምሮ ሌሎችም ሃይማኖታዊ ክንውኖች ተስተናግደዋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በሚሊኒየም አዳራሽ መዝሙር እና ስብከትን ጨምሮ ሌሎችም ሃይማኖታዊ ክንውኖች ተስተናግደዋል
በሚሌኒየም አዳራሽ መዝሙር እና ስብከትን ጨምሮ ሌሎችም ሃይማኖታዊ ክንውኖች ተስተናግደዋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በሚሊኒየም አዳራሽ መዝሙር እና ስብከትን ጨምሮ ሌሎችም ሃይማኖታዊ ክንውኖች ተስተናግደዋል
15ኛው የቡና ኮንፈረንስ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, 15ኛው የቡና ኮንፈረንስ