በኢራን ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ነው የተባለው ተቃውሞ ምን አስከተለ?
ከመስከረም ወር መጀመሪያ አንስቶ በኢራን ውስጥ የተቀሰቀሰው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በአስርት ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ እንደሆነ ይነገራል።
አንዲት ወጣት በሃይማኖታዊ ፖሊሶች ተፈጽሞባታል በተባለ ድብደባ ሕይወቷ ማለፉን ተከትሎ ዋና ከተማዋ ቴህራንን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ከ300 በላይ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መደረጋቸው ተመዝግቧል።
ይህንን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ምን የተለየ ያደርጋዋል? ምንስ አስከተለ?









