ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ

‘ክፍቱ እስር ቤት’ በመባል የምትጠራው ጋዛ በትንሽ ቦታ ላይ በርካታ ሰዎች ከሚኖሩባቸው የዓለማችን ቦታዎች አንዷ ናት ናት።

የሐማስን ጥቃት ተከትሎ በእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ቀን ከሌት የምትደበደበው ጋዛ ነዋሪዎቿ በከባድ ችግር ውስጥ ይገኛሉ።

ለመሆኑ ጋዛ ለነዋሪዎቿ ምን ትመስላለች? ለምን ይህች አነስተኛ የተጎሳቆለች ግዛት የዓለምን ቀልብ በድጋሚ ለመሳብ በቃች?