ማንቸስተር ዩናይትድ ከቼልሲ ማን ያሸንፋል? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶች

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከዛሬ ማክሰኞ ምሽት ጀምሮ ይከናወናሉ።

ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት እንዲከናወኑ መርሃ ግብር ወጥቶላቸዋል።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን የእነዚህን ጨዋታዎች ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል።

ዛሬ [ማክሰኞ] ምሽት

ዎልቭስ ከ በርንሌይ

ሼፊልድን ካሸነፉ በኋላ ብርንሌይዎች በጥሩ የራስ መተማመን ላይ ይገኛሉ።

ዎልቭስ ደግሞ ካለፉት አራት ጨዋታዎች በሦስቱ ተሸንፏል።

ዎልቭስ በሜዳው በቀላሉ ይህንን ጨዋታ ያሸንፋል።

ግምት፡ 2 – 0

ሉተን ከ አርሴናል

አርሴናሎች በማጥቃት ረገድ እንደባለፈው ዓመት ባይሆኑም ጥሩ ጉዞ እያደረጉ ነው።

ሉተኖች በሜዳቸው ጥሩ ቢሆኑም፣ አርሴናል ይህንን ጨዋታ ያሸንፋል።

ከአውሮፓውያኑ 1984 ወዲህም የመጀመሪያውን ሦስት ነጥብ በሉተን ሜዳ ያሳካሉ።

ግምት፡ 0 – 2

ረቡዕ

ብራይተን ከ ብሬንትፎርድ

እሑድ ዕለት ብራይተኖች በ10 ተጫዋች ባካሄዱት ግጥሚያ በቼልሲዎች መሸነፋቸው በራስ መተማመናቸውን የሚጎዳ ነው።

ይኼኛው ጨዋታም ለአሠልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዜርቢ ከባድ እንደሚሆን እገምታለሁ።

ብሬንትፎርዶች በመልሶ ማጥቃት በመጫወት ነጥብ የሚያገኙ ይመስለኛል።

ግምት፡ 2 – 2

ክሪስታል ፓላስ ከ በርንመዝ

በርንመዞች በማጥቃት ላይ የተመሠረተ አጨዋወት በመምረጣቸው ውጤት እያስገኘላቸው ይመስላል።

በጠባብ ውጤት ክሪስታል ፓላስ ያለማሸነፍ ጉዞውን የሚገታ ይመስለኛል።

ግምት፡ 1 – 0

ፉልሃም ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ፉልሃሞች ዕድለኛ ባለመሆናቸው ከአንፊልድ ያለምንም ነጠብ ተመልሰዋል።

ፎረስት ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎችን በመሸነፉ ውጤቱ እስኪስተካከል ድረስ አሠልጣኝ ስቲቭ ኩፐር ላይ ያለው ጫና የሚበርድ አይመስልም።

ጨዋታው ተቀራራቢ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን በአቻ ውጤትም ይጠናቀቃል ብዬ አገምታለሁ።

ግምት፡ 1 – 1

ሼፊልድ ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል

አሠልጣኝ ፖል ከሼፊልድ ኃላፊነታቸው መነሳታቸው የጊዜ ጉዳይ ይመስላል።

አዲስ አሠልጣኝ የሚይዘው ቡድን ለውጥ ቢያሳይም የሼፊልድ ተከላካይ መስመር ደካማ መሆን ይህንን እንዳልገምት ያደርገኛል።

ሊቨርፑሎች ከፉልሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ ወደ ዋንጫ ፉክክር መመለሳቸውን ያሳዩበትን ድል አስመዝግበዋል። ከዚህ ጨዋታም በቀላሉ ሦስት ነጥብ ያሳካሉ።

ግምት፡ 0 – 3

አስቶን ቪላ ከ ማንቸስተር ሲቲ

ማንቸስተር ሲቲ በርካታ ጎሎችን ማስተናገድ መጀመሩ አስገራሚ ሲሆን ቪላ በዚህ ጨዋታ ጎል ያስቆጥራል።

ሲቲ በቅጣት የሮድሪ እና የጃክ ግሪሊሽን ግልጋሎት ባያገኝም አሁንም በቡድኑ ላይ እምነት ማጣት ላይ አልደረስኩም።

በቶተንሃም ጨዋታ ዳኛው በድሎናል በሚል ስሜትም የሚጫወቱ ይመስለኛል።

ግምት፡ 1 – 2

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ኒውካስል

ሴንት ጀምስ ፓርክ ላይ ማንቸስተር ዩናይትድ ከመሸነፉም በላይ ተጫዋቾቹም ግድ የለሽ መሆናቸውን አሳይተዋል።

አሠልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግም በአንዳንድ ተጫዋቾቻቸው ተከድተዋል።

ኒውካስሎች ተሯሩጠው ሲጫወቱ የዩናይትድ ተጫዋቾች ምንም ፍላጎት ካለማሳየታቸው አንጻር በሰፊ የጎል ልዩነት መሸነፍ ነበረባቸው።

በዚህ ጨዋታ ጥሩ ሊንቀሳቀሱ ቢችሉም ዘንድሮ ከደረጃ ሰንጠረዡ ግማሽ በላይ ያሉ ቡድኖችን ማሸነፍ አልቻሉም።

ቼልሲ የሚዋዥቅ አቋም ቢያሳይም ይህ የሚያሸንፈው ጨዋታ ነው።

ግምት፡ 1 – 2

ሐሙስ

ኤቨርተን ከ ኒውካስል

ይህ ለማሸነፍ በሚጥሩ ሁለት ቡድኖች መካከል ስለሚሆን ድንቅ ጨዋታ እንደሚሆን እጠብቃለሁ።

ኤቨርተን በሜዳው ጥሩ ባይሆንም ቡድኑ ለአንድ ዓላማ የሚጫወቱ ተጫዋቾች አሉት።

ኒውካስል ያለው የቡድን አንድነት እና ለአሠልጣኝ ኤዲ ሃው አጨዋወት መገዛታቸው ደግሞ ይበልጥ ይታያል።

ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል የሚል ስሜት ቢኖረኝም፣ ቀድሞው ኤቨርተን የክንፍ ተጫዋች ልዩነት ፈጣሪ እንደሚሆን አስባለሁ።

ግምት፡ 1 – 2

ቶተንሃም ከ ዌስት ሃም

ቶተንሃም በማጥቃት ላይ የተመሠረተ ጨዋታ ቢመርጥም፣ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞዬስ ይህ እንዲሆን አይፈቅዱም።

በመልሶ ማጥቃት ላይ የተመሠረተ አጨዋወት በመከተል ወደ ሜዳ ይገባሉ።

ቶተንሃሞች በዚህ ጨዋታ ዌስት ሃምን የሚያሸንፉ ቢሆንም በቀላሉ አያሳኩትም።

ግምት፡ 3 – 2