ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ያገለገሉ የኤሌትሪክ መኪኖች ባትሪ ዕድሜ ምን ያህል አስተማማኝ ነው?
ኬሪ ደንስታን እና ጓደኛው አዲስ የኤሌትሪክ መኪና ለመግዛት ሲያስቡ መጀመሪያ የጠየቁት ጥያቄ "ባትሪው እንዴት ነው?' የሚል ነበር።
ያገኙት የ2021 ኒሳን ሊፍ ሞዴል 29 ሺህ ማይል ብቻ የተነዳ ነበር።
የመኪና ሻጩ የባትሪው ሁኔታ 93 በመቶ በመሆኑ ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ነገራቸው።
12 ሺህ 500 ፓውንድ አውጥተው በቂ ሰው መያዝ የሚችል ከፍ ያለ የኤሌትሪክ መኪና ገዙ።
ደንስተን ሌላ ቮልቮ ኤስዩቪ የኤሌትሪክ መኪና ያለው በመሆኑ በመኪናዋ ብዙም አልተመሰጠም።
"ዘናጭ የሆነ መኪና እወዳለሁ፤ ይህ እስከዚህም ነው" ይላል።
ነገር ግን የገዙት ኒሳን ሊፍ መኪና በመጀመርያዎቹ ሦስት ወራት ውስጥ ጥሩ ማገልገሉን ይገልጻል።
ያገለገሉ የኤሌትሪክ መኪኖችን በሚገዙ ሰዎች የሚጠየቀው ቀዳሚ ጥያቄ ምን ያህል ኪሎ ሜትር ተነድቷል እና የባትሪው ዕድሜ ምን ያህል ነው? የሚለው ነው።
ነገር ግን በርካታ ሰዎች የኤሌትሪክ መኪና ወደ መጠቀም ፊታቸውን ሲያዞሩ የመኪናውን ባትሪ ዕድሜ በሚገባ መመርመር የበለጠ አንገብጋቢ እየሆነ መጥቷል።
ባትሪውን የቀድሞው የመኪና ባለቤት እንዴት ነበር የሚከታተለው? 100 ፐርሰንት እስኪደርስ ድረስ በሚገባ ቻርጅ ያደርገው ነበር? ያ ካልሆነ የኤሌትሪክ መኪኖችን የባትሪ ዕድሜ በከፍተኛ ሁኔታ የማሳጠር አቅም አለው።
የባትሪ ብላክ ቦክስ ችግር ያገለገሉ የኤሌትሪክ መኪና ለመግዛት የሚፈልጉ ሰዎችን ፍላጎት ከሚቀንሱ ነገሮች መካከል ናቸው።
ነገር ግን ትንተና የሚሰሩ ኩባንያዎች ያገለገለ የኤሌትሪክ መኪና ዕድሜ በአስተማማኝ ሁኔታ መናገር እንችላለን ይላሉ።
የኢንዱስትሪ ኤክስፐርቶች ደግሞ የኤሌትሪክ መኪኖች ባትሪ ከሚገመተው በላይ ለረዥም ጊዜ ያገለግል ሲሉ ይመሰክራሉ።
ደንስተን የገዛው ኒሳን ሊፍ የኤሌትሪክ መኪና አሰራሩ ወስሰብ ያለ እና ዘመናዊ ነው።
ባትሪው በሌሎች የኤሌትሪክ መኪኖች ላይ እንደተለመደው ራሱን ማቀዝቀዝ የሚችል ስርዓት የተገጠመለት ነው።
ኒሳን በቅርቡ አምርቶ ለገበያ ባቀረባቸው የኤሌትሪክ መኪኖቹ ላይ ያሻሻለው ቢሆንም የከዚህ በፊት ሞዴሎች ግን ከዓመት ዓመት በከፍተኛ ሁኔታ ዕድሜያቸው እየቀነሰ እንደሚመጣ የአሜሪካ ኢንሹራንስ እና የምርምር ኩባንያው ኒምቢልፊንስ ጥናት ያሳያል።
ደንስተን ግን ምንም ስጋት የገባው አይመስልም።
"የኤሌክትሪክ መኪኖቼን 100 ፐርሰንት ድረስ ቻርጅ አድጋለሁ እናም ቻርጅ ማድረግ በሚኖርብኝ ወቅት ሁሉ ቻርጅ አደርጋለሁ። ምንም አያስጨንቀኝም" ብሏል።
በባትሪ ዕድሜ ጭንቀት ለተሰቃዩ ያገለገሉ የኤሌትሪክ መኪኖችን ለሚገዙሰዎች በኦስትሪያ የሚገኘው አቪሎ የተሰኘው ድርጅት መፍትሄ እንዳለው ይናገራል።
ዋና የምርት ኦፊሰር የሆነው ፓትሪክ ሻቡስ "በእርግጥ የባትሪውን የጤና ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በተናጥል መወሰን እንችላለን" ይላል።
አቪሎ በገበያ ውስጥ ካሉ በርካታ የባትሪ ዕድሜኡን በመተንተን ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች አንዱ ነው።
የኤሌትሪክ መኪና ባለቤቶች መኪናውን በሚጠቀሙበት ጊዜ የባትሪውን አፈጻጸም ለመከታተል እንዲችሉ የሚሰኩት፣ የመነጽር ማስቀመጫ የምታክል የተለየች መመርመሪያ ሳጥን አለች። ይህም የባትሪው ዕድሜ ከ100% ወደ 10% እስኪቀንስ ያለውን በመከታተል መረጃ ይሰጣል።
ወይም ደግሞ ፈጣን ፍተሻን ማድረግ የሚያስችላቸውን መንገድ መመርጥ ይችላሉ።
ይህም ከመኪናው የባትሪ ሶፍትዌር መረጃን በመውሰድ እና በኮምፒተር ሞዴል በመታገዝ የባትሪውን ዕድሜ የሚገልጽ መረጃን ያደራጃል።
"ይህን መኪናው ቆሞ ከሁለት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ማድረግ እንችላለን" ይላል ሻቡስ።
የመጀመርያው የተለየ ፍተሻ የባትሪውን ፍሰት በቅርበት ይከታተላል፤ የአሁኑን ወይም የቮልቴጅ መለዋወጥን በመውሰድ እንዲሁም በባትሪው ውስጥ ስላሉት ነጠላ ህዋሶች ጤና ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ያሳያል ሲል አቪሎ ያብራራል።
የአቪሎ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርከስ በርገር የኩባንያው የትንታኔ ውጤቶች አንዳንድ ጊዜ በአንዳንድ የኤሌትሪክ መኪኖች አብሮ በተሰራው የትንታኔ ስርዓት ከሚመረተው የባትሪ ዕድሜ መቶኛ "በተጨባጭ" ይለያያሉ ብለዋል።
ከ 80 በመቶ በታች የሆነ የባትሪ ዕድሜ ያላቸው የኤሌትሪክ መኪናዎች በጣም ያገለገሉ ናቸው የሚለውን የተለመደ ሃሳብ ይሞግታል።
"ከ 80 በመቶ በታች የሆነ የባትሪ ዕድሜ ያለው የኤሌትሪክ መኪና አሁንም ትሩ መኪና ሊሆን ይችላል… ዋጋው ግን ሊጤን ይገባዋል።"
በኒውዚላንድ ነዋሪ የሆነችውነ እና ኤሌትሪክ መኪና የምታሽከረክረው ሉሲ ሃውክሮፍት ከሦስት ዓመት በፊት ኒሳን ሊፍ ገዝታ ነበር።
የመኪና ሻጩ የባትሪው ዕድሜ 95% ወይም ከዚያ በላይ መሆኑን እንዳሳያት ታስታውሳለች። ከአንድ ዓመት በኋላ ግን አንድ መካኒክ የባትሪውን ዕድሜ እንደገና ፈትሸላት።
"በጣም ወርዷል" በማለት ታስታውሳለች። "ባለቤቴ በጉዳይ ተገርሞ ወይም አሳስቦት ነበር።"
ነገር ግን ባትሪው ሙሉ ሲሆን አሁንም መኪናው ወደ 160 ኪሜ (100 ማይል) ርቀት ይጓዛል።
ጥንዶቹ በአብዛኛው መኪናውን የሚጠቀሙበት እስከ 10 ኪሎ ሜትር ለሚደርስ አጭር ጉዞ ብቻ ነው።
ሃውክሮፍት አንዴ ቻርጅ ተደርጎ እስከ 400 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችል መኪና ያላቸው ጓደኞቿ እንዳሏት በመጥቀስ "ይህ በጣም ጥሩ ነው" ትላለች።
በቼልተንሃም ክሊቭሊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሽያጭ ዳይሬክተር ለሆነው ለዴቪድ ስሚዝ፣ ያገለገሉ የኤከሌትሪክ መኪናዎች ባትሪዎች በአግባቡ መተንተን መቻል ወሳኝ መሆኑን ይናገራል።
አብዛኛዎቹ ደንበኞች ይህንን መረጃ ይጠይቃሉ ይላል። የእሱ ኩባንያ የባትሪ ዕድሜ ሪፖርቶችን ክሊር ዋት ከተሰኘ የባትሪ ዕድሜ ተንታኝ ድርጅት ይጠቀማል።
"ሙሉ በሙሉ ነፃ ናቸው። በሪፖርቶቹ ውስጥ ጣልቃ መግባት አንችልም" ይላል።
"ደንበኞች ሪፖርቱን አንዴ ካዩት በኋላ መግዛት ከፈለጉ ከ10 ውስጥ ዘጠኙ ይስማማሉ።"
የ ክሊቭሊ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማት ክሊቭሊ አክለውም በባትሪ ጥቅል ውስጥ ያሉ ሴሎችን ወይም ሞጁሎችን መተካት ይቻላል ይላሉ።
ይህ ደግሞ አዲስ ባትሪ ከመቀየር በጣም ርካሽ ነው።
የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሲሞና ኦኖሪ ባትሪውን በተሻለ ሁኔታ ለመንከባከብ የኤሌትሪክ መኪናዎን እንዴት ቻርጅ ማድረግ እንዳለብዎት "ጥቅም የሚሰጥ መረጃ" አለ ትላለች።
"በተደጋጋሚ ቶሎ ቶሎ ቻርጅ ማድረግ እና ሙሉ በሙሉ በፍጥነት ቻርጅ የማድረግን በማስቀረት መካከል ጠቃሚ መረጃ ሊኖር ይችላል" ትላለች።
ሆኖም ግን ይህ ገና በጥልቀት የተጠና እንዳልሆነ ትናገራለች።
አንዳንድ ሸማቾች ጥንቁቅ ቢሆኑም፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የባትሪ ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻል አሳይቷል ይላሉ ማክስ ሬድ።
በሲአርዩ ውስጥ የገበያ ጥናት ባለሙያ የሆኑት ማክስ ሬድ "ያገለገሉ ባትሪዎች ምናልባት ከ500 እስከ 1,000 (ቻርጅ ለመሙላት) ዑደቶች ሊቆዩ ይችላሉ" ሲል ያስረዳል።
"አሁን ግን ከእነዚህ አዳዲስ የኤሌትሪክ መኪናዎች ከመምጣት በኋላ 10,000 ዑደቶች ይሄዳሉ።"
ፖል ቻውንዲ የኤሌትሪክ መኪናዎች ባትሪ ቢደክሙም ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ ይላል።
የተወሰኑ ደንበኞቹ እና ቢዝነሶች ያገለገሉ የኤሌትሪክ መኪና ባትሪዎችን በቤታቸው ኃይል ለማመንጨት ይገለገሉበታል።
ምናልባት ስድስት የኤሌክትሪክ ፎርክሊፍቶች ሊኖራቸው ይችላል ነገር ግን የኤሌእሪክ መስመራቸው በአንድ ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት መኪኖችን ቻርጅ ለማድረግ ብቻ በቂ ነው።
የመኪና አምራቾች የባትሪ ዕድሜን በሚመለከት ሪፖርቶችን ተሽከርካሪዎች ለማውጣት የተለያዩ ዘዴዎችን ስለሚጠቀሙባቸው "በዚያ ዙሪያ ተጨማሪ መመዘኛዎች የሚያስፈልግ ይመስለኛል" ብለዋል ቻውንዲ።