ወላጆች የማያውቋቸው ልጆች ራሳቸውን እንዲያጠፉ የሚያበረታቱ ድረ ገጾች

ህይወቱን ያጣው ቭላድ

የፎቶው ባለመብት, Family photo

የምስሉ መግለጫ, ህይወቱን ያጣው ቭላድ

አና ኒኮሊኬዝሊ የመጨረሻ ልጇ ዛሬ ከእሷ ጋር የለም። የልጇን የመጨረሻ ደቂቃዎች ታስታውሳለች። "ልጄ ለመጨረሻ ሕቅታው ሲታገል አይቸዋለሁ። ያለፈው በከፍተኛ ስቃይ ነው" ትላለች።

አና ቭላድ የተባለው የ17 ዓመት ልጇ ሕይወት ያለፈው በአንድ ድረ ገጽ ምክንያት እንደሆነ ታምናለች። ይህ እስካሁን ያለ እና ራስን ማጥፋት የሚያበረታ ቡድንን የያዘ ገጽ ልጇ መረዝ እንዲጠጣ "እንደገፋው" ትናገራለች።

የቭላድ ቤተሰቦች ባለፈው ሰኔ ወር እጅግ አሰቃቂውን የልጃቸውን አሟሟት የተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለሌሎች ማንቂያ እንዲሆን በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ሃምፕሸር ይፋ አድርገዋል።

የዩኬ መንግሥት በዚህ ዓመት ያወጣው የበይነ መረብ ደኅንነት ሕግ ማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ራስን ማጥፋት እና መጉዳት ላይ የሚያጠነጥኑ ይዘቶችን እንዲያስወግዱ ያዛል።

ሆኖም ይህ ሕግ ብቻውን በቂ አይደለም በሚል ትችት የሚሰነዝሩ አሉ።

ማሰሰቢያ፡ ይህ ጽሁፍ የአንባቢያን ስሜትን ሊረብሽ የሚችል ይዘት አለው

ሚያዝያ 29/2016 ዓ.ም. ከሌሊቱ 8፡40 አና በወንድ ልጇ የድረሱልኝ ጥሪ ከእንቅልፏ ነቃች። ልጇ ቭላድ "እናቴ፣ ሐኪም ጥሩ!" ሲላት ሰማች።

ከዚያም የጠጣውን መርዝ ስም እና የጠጣበትን ሰዓት ጮክ ብሎ ጠራው።

"ያ ንጥረ ነገር ምን እንደሆነ አልወቅም ነበር" የምትለወ አና "ነገር ግን ራሱን የማጥፋት ሃሳቡን ቀይሮ ወደ እኔ መጥቶ እንድረዳው፣ እንድታደገው ጠየቀኝ" ስትል የሆነውን ታሰታውሳለች።

የቭላድ አባት ግርሃም ኪዝሊ ልጃቸው በመኝታ ክፍሉ ወለል ላይ ከመውደቁ አስቀድሞ እንዴት ደረጃ መውጣት እንደተቸገረ ይገልጻል።

"እጆቹ ዝለው ነበር ይነቀጠቁም ነበር። ሁኔታው ሁሉ የፍርሃት ነበር።"

"በጣም ኃይል የተሞለበት እና ድንገተኛ ነበር" ስትል እናቱ አና ጭምራለች። የልጇ ሰውነት በተደጋጋሚ ሲንቀጠቀጥ ነበር "በሕይወት ለመቆየት በጣም ሲታገል ነበር - የነበበትን ሰቆቃ መገመት ራሱ በጣም ይከብደኛል" ብላለች።

ከደቂቃዎች በኋላ ከጤና ባለሙያ በስልክ በተነገረው መሠረት ግርሃም ልጁን ጉልበቱ ላይ አስቀመጦ የመጀመሪያ እርዳታ ለማደረግ ወሰነ።

"የልጄን ሕይወት ለመታደግ ማድረግ የምችለውን አደረኩ" ሲሉ ከዓይኖቹ እንባ ይወርድ ነበር። "በጣም አሰቃቂ ነበር።"

የቭላድ ታላቅ እህቶች ሚላ እና ማሻ ከወላጆቻቸው አና እና ግራሃም ጋር
የምስሉ መግለጫ, የቭላድ ታላቅ እህቶች ሚላ እና ማሻ ከወላጆቻቸው አና እና ግራሃም ጋር

በፖሊሶች ልብስ ደረት ላይ የሚንጠለጠሉ ካሜራዎች ያሳዩት ምሥል የደንገተኛ አደጋ ሠራተኞች የቭላድን ሕይወት ለመታደግ ወደ ቤቱ ሲገቡ የነበውን የስሜት ስብራት እና ግርግር "ቁልጭ" አድርገው አሳይተዋል።

ከቭላድ ህልፈት በኋላ ቤተሰቦቹ ልጃቸው በበይነ መረብ አማካኝነት ያሰላፋቸወን "መጥፎ ጊዜያት" ለሌሎች ያጋራ እንደነበር ሲያውቁ ድንጋጤ ውጧቸዋል።

እናቱ "በጣም ምሥጢራዊ" ስብስብ እንደነበር እና "ራስን ማጥፋት የሚያበረታታ" እንደነበር ትገልጻለች።

ቭላድ ይህንን ቡደን ከተቀለቀለ በኋላ የገዛቸውን "ራስ ማጥፊያ" ቁሶች ሳውዛአምፕተን በሚገኘው መኖሪያቸው ፖሊስ አግኝቷል። ይህም መርዛማ ንጥረ ነገሮች፣ እንክብሎች እና ሌሎች ቁሶችን ያካተተ ነው።

"እነዚህን ነገሮች የት እንደሚሸጡ አጣርቶ አውቋል። እነዚህ ነገሮች የት እንደሚሸጡ እና ምን እንደሚያስፈለገውም ተነግሮታል" ሲሉ የሀምፐርሸር የወንጀል መርማሪው ክሪስ ባሮው ገልጸዋል።

ቀጥለው "ቭላድ ያለድረ ገጹ ድጋፍ ሕይወቱን የቀጠፉትን እነዚህ ቁሶች እና ንጥረ ነገሮች በአንድ ላይ ሊሰበስባች አይችልም ነበር" ብለዋል።

ቭላድ በደስታ የተሞላ የልጅነት ጊዜ አሳልፏል። ሆኖም ከጊዜ በኋላ በአስራዎቹ መጀመሪያ ኦቲዝም፣ ደብርት እና ጭንቀት ታይቶበታል። ራሱን ባጠፋበት ወቅት በአእምሮ ጤና ባለሙያዎች ክትትል ይደረግለት ነበር። በተጨማሪም ከፍተኛ ህመም የለው የነርቭ ችግርም አጋጥሞታል።

ቤተሰቦቹ የአእምሮ ጤናው እየተሻሻለ እንደሆነ ተመለክተዋል። ጓደኞች ማፍራት እና ጉዞዎች ላይ መሳተፍ ጀምሮም ነበር። ሆኖም መሻሻል ቢያሳየም ሕይወቱ ባለፈችበት ጊዜ ሙሉ ለሙሉ አላገገመም ሲሉ እህቶቹ ማሻ እና ሚላ ተናግረዋል።"

የወንጀል መርማሪው ክሪስ ባሮው
የምስሉ መግለጫ, የወንጀል መርማሪው ክሪስ ባሮው በቭላድ ቤት ከተገኘው ማስረጃ ጋር

"በስብስቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች በሙሉ ፈተና ውስጥ ቢወድቁም፣ ወንድሜ በራሱ ሕይወቱን የተመለከቱ ነገሮችን መወሰን እንደማይችል አያወቅም" ነበር ትላለች ማሻ።

ከድረ ገጹ ተቆጣጣሪዎች ጋር የተጻጻፈችው እህቱ ሚላ ገጹን "ሰዎችን ወደ ጠረዝ የሚገፉ ናቸው" ስትል ትገልጻቸዋለች።

ይህ ራስ ማጥፋትን የሚያበረታታው ድረ ገጽ 50 ሺህ ተከታዮች በዓለም ዙሪያ አለው። የቭላድ ቤተሰቦች ድረ ገጹ እንዲወርድ ወይም እንዲታገድ ይፈልጋሉ።

ቢቢሲ ቭላድ አባል የነበረበትን ድረ ገጽ ለመረዳት ዓመታት የፈጀ ምርመራ አደርጓል። በአጋጣሚ ቢቢሲ ከማጋለጡ አስቀድሞ ቭላድ መርዛመውን ንጠረ ነገር ሊዎንዲ ዛኩቴንኮ ከተባለ ዩክሬን ከሚገኝ ሻጭ ነበር ያዘዘው።

ሆኖም ያንን ንጥረ ነገር ቭላድ አልወሰደውም። የተጠቀመው መርዛማ ኬሚካል ከፖላንድ የመጣ እና የሐሰት ገለጻ የተለጠፈበት ነበር። ይህም የጉሙሩክ ቁጥጥርን ለማለፍ የተደረገ ሊሆን ይችላል።

'የሞት መንገድ'

ከልጃቸው ህልፈት በኋላ የቭላድ ቤተሰቦች ቭላድ ድረ ገጹ ላይ ያሰፈራቸውን ጽሁፎች እና የመልዕክት ለውውጦች ተመልከተዋል። ነገሮች እንዴት ቀስበቀስ እየጠነከሩ እንደሄዱም ተረድረዋል።

እናቱ አና "አስበው፣ ምሥጢራዊ የሆነ የመልዕክት ለውውጥ አለህ እናም ያ ወደ ሞት የሚወድ መንገድ ነው። ማንኛውም ሰው ሊያልፈበት የሚችል ነው። ህጻን ልጅ ሊያልፈበት ይችላል። የሚቆጣጣር የለም" ስትል ታሰረዳለች።

"መርዙን የሚሸጡ አሉ፣ መርዙን እንድትወስድ የሚያበረታቱም አሉ። ይህ እንዴት ነው ሕጋዊ የሆነው?" ስትል ትጠይቃለች።

አባቱ ግራሃም ይቀጥል "እነሱ በሕይወት አሉ። የእኛ ልጅ ግን ሞቷል" ሲል ተናግሯል።

ፖሊስ ቭላድ ሕይወቱን ባጣበት ድረ ገጽ አማካይነት የተፈጸሙ ወንጀሎች በተመለከተ ምርመራ እያደረገ ነው።

ቭላድ ከሚወዳት ድመቱ ጋር

የፎቶው ባለመብት, Family Photo

የምስሉ መግለጫ, ቭላድ ከሚወዳት ድመቱ ጋር

ይህ ድረ ገጽ በደቡብ አሜሪካ የሚገኝ ሲሆን አሜሪካ ውስጥ የሚገኝ ሰርቨርን ይጠቀማል። የተለያዩ ሀገራት የተለያዩ ሕጎች ስላላቸው በኢንትርኔት ወንጀሎችን ለመካላከል ለፖሊስ እጅግ ከባድ ነው።

ከብሔራዊ ስታትስቲክስ ድርጅት የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በአንግሊዝ እና በዌልስ ባለፉት 6 ዓመታት ራስን ማጥፋት በ10 በመቶ ጨምሯል። ከ25 ዓመት በታች ያሉ ሰዎች ራሳቸውን የሚያጠፉበት ቁጥር የተለመደ ባይሆንም እጅግ በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል።

የመንግሥት ቃል አቀባይ ራስን ማጥፋት ቤተሰብን እያናጋ እንደሆነ ገልጸዋል። ሆን ብሎ ሰዎች ራሳቸውን እንዲያጠፉ ወይም እንዲጎዱ ማደረግ ወንጀል እንደሆነም አክለዋል።

"የበይነ መረብ ደኅንነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ ማኅበራዊ መድረኮች ራስን ማጥፋትም ሆነ መጉዳትን የሚያበረታቱ መድረኮችን ማስወገድ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለህጻናት ራስን ማጥፋት የሚያሳዩ ይዘቶችን ማሳየትም አይፈቅደም።"

"ድርጅቶች ሕግ እስኪወጣ መጠበቅ የለባቸውም። ተጠቃሚዎቻቸውን ለመጠበቅ አሁን ሥራ መጀመር አለባቸው።"

"ሳማሪታን" የተሰኘ የበጎ አደራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ችላ የተባሉ ግን ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ አንስተኛ ድረ ገጾች ከትላቆቹ እኩል እርምጃ ሊወስደባች ይገባል ብለዋል።

"ሕጋዊ ግን ጎጂ ይዘቶች ለአዋቂም ሆነ ለህጻን በጥበቅ ሊከለከሉ ይገባል" ካሉ በኋላ፣ መንግሥት እጅግ ከመርፈዱ በፊት መንቃት አለበት ሲሉ አክለዋል።