ሊቨርፑል፣ አርሰናል፣ ማንቸስተር ዩናይትድ... ቀጣይ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሊቨርፑል ባለፈው ሳምንት በፉልሃም ተሸንፏል።
"የአርን ስሎት ቡድን ትንሽ የተቀዛቀዘ መስሎ ቀርቧል" ሲል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ገልጿል።
"ዋንጫውን ማንሳት የሚችሉ ቢሆንም ባለፉት ጥቂት ጨዋታዎች ግን አቋማቸው ወርዷል" ብሏል።
ሱተን የሊጉን መሪ ሊቨርፑልን ጨምሮ ቀሪዎቹን የሳንቱን ጨዋታዎች እንደሚከተለው ገምቷል።
ቅዳሜ
ማንቸስተር ሲቲ ከ ክሪስታል ፓላስ
ክሪስታል ፓላስ በደንብ የተደራጀ ቡድን ከመሆኑ አንጻር ሲቲን ሊፈትነው ይችላል።
ፓላሶች ካለፉት 5 ጨዋታዎች አራቱን አሸንፈው አንዱን አቻ ሲወጡ፤ ሲቲ ግን ሁለቱን ብቻ አሸንፏል።
ሲቲ የነበረውን ማራኪ አጨዋወት ባለፈው ሳምንት በማንቸስተር ደርቢ ማሳየት ከብዶት ታይቷል።
ግምት፡ 2 - 1

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ብራይተን ከ ሌስተር
ሌስተር ያለፉትን ስምንት ጨዋታዎች ከመሸነፋቸውም በላይ ጎልም አላስቆጠሩም።
የቡድኑ ውጤት ማጣት ከአሠልጣኙ ሩድ ቫንኒስተልሮይም በላይ ነው።
ብራይተኖች ካለፉት ሦስት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ነው ማግኘት የቻሉት።
ይህንን ጨዋታ በቀላሉ ያሸንፋሉ።
ግምት፡ 2 - 0
ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ኤቨርተን
ይህ ለመገመት የሚከብድ ጨዋታ ነው። ፎረስት ካለፈው ሳምንት ሽንፈት ለማገገም ሲጫወት ኤቨርተን ደግሞ አስቸጋሪ ቡድን ሆኖ ቀርቧል።
ኤቨርተኖች ያለፉትን ስምንት ጨዋታዎች ስድስቱን አቻ ቢያጠናቅቁም፣ ይህ ጨዋታ በባለሜዳው ቡድን የበላይነት ይጠናቀቃል።
ግምት፡ 1 - 0
ሳውዝሃምፕተን ከ አስቶን ቪላ
ቪላ በሳምንቱ አጋማሽ በፒኤስጂ ተሸንፎ ከሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ውጪ ሊሆን ከጫፍ ደርሷል።
ከፈረንሳዩ ክለብ በፊት ከሳውዝሃምፕተን ጋር ያላቸው መርሃ ግብር ቀላል የሚባል ነው።
ሳውዝሃምፕተን አሠልጣኙ ኢቫን ጁሪችን አሰናብቷል። በሜዳቸው ላለመሸነፍ ቢጫወቱም ድሉ የቪላ ይሆናል።
ግምት፡ 1 - 2

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
አርሰናል ከ ብሬንትፎርድ
አሠልጣኝ ማይክል አርቴታ ባለፈው ሳምንት ከኤቨርተን ጋር በነበረው ጨዋታ ተጫዋቾችን አሳርፈው በሳምንቱ አጋማሽ ሪያል ማድሪድን አሸንፈዋል።
በዚህ ጨዋታም የተወሰኑ ተጫዋቾች ሊያርፉ ስለሚችሉ ውጤቱን ለመገመት ከባድ ይሆናል።
ብሬንትፎርድ ጨዋታውን በበላይነት ማጠናቀቅ ቢችልም ድሉ የመድፈኞቹ ይሆናል።
ግምት፡ 2 - 1
እሑድ
ቼልሲ ከ ኢፕስዊች
ኢፕስዊች በመጀመሪያው ዙር በሜዳው ቼልሲን ማሸነፍ የቻለ ከመሆኑ አንጻር አሁንም ተመሳሳይ ውጤት ሊያስመዘግብ ይችላል።
ቼልሲ ባፈው ሳምንት ከብሬንትፎርድ ጋር በነበረው ጨዋታ አሳማኝ አልነበረም።
ኮል ፓልመር ወደ አቋሙ መመለስ ባይችልም ቡድኑ ከሚፈጥረው ዕድል አንጻር ይህንን ጨዋታ በቀላሉ ማሸነፍ ይችላል።
ግምት፡ 3 - 0

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሊቨርፑል ከ ዌስት ሃም
ዌስት ሃም ያለፉትን ጥቂት ጨዋታዎች አቋሙ ወርዷል።
ቡድኑ አሠልጣኝ ግርሃም ፖተር ከተሾሙ በኋላ መሻሻል ባያሳይም ችግሩ ግን የአሠልጣኙ አይደለም።
ሊቨርፑል ወደ ጥሩ አቋሙ ለመመለስ ይህ ምርጥ አጋጣሚ ይሆናል።
ሊቨርፑል ጥሩ ባይጫወት እንኳን በሜዳው ማሸነፍ እንደሚችል ደጋግሞ አሳይቷል።
ግምት፡ 3 - 1
ዎልቭስ ከ ቶተንሃም
አሠልጣኝ አንጅ ፖስትኮግሉ አንዳንድ ተጫዋቾቻው ከጉዳት ቢመለሱም በዩሮፓ ሊግ ከኢንትራ ፍራንክፈርት ጋር ላለባቸው የመለስ ጨዋታ ተጫዋቾችን አሳርፈዋል።
ዎልቭስ በአሠልጣኝ ቪቶር ፔሬራ ስር በተለይም የተከላካይ መስመራቸው ጠንካራ ሆኗል።
ያለፉትን ሦስት ጨዋታዎች በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና መራቅ ችለዋል።
ግምት፡ 2 - 0
ኒውካስል ከ ማንቸስተር ዩናይትድ
ማንቸስተር ዩናይትድ በተለይም ጎል በማስቆጠር በኩል ያለበት ችግር ተደምሮ ቡድኑ አሰልቺ መስሏል።
እንደቶተንሃም ሁሉ የቡድኑ የውድድር ዓመት የተንጠለጠለው በዩሮፓ ሊግ ላይ ነው።
ኒውካስል በቻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ እየተጫወተ ከመሆኑ እና ካለው ጥንካሬ አንጻር ጨዋታውን የማሸነፍ ዕድል አለው።
ከካራባኦ ዋንጫ ድላቸው በኋላ አሁን ትኩረታቸው ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ ሆኗል።
ግምት፡ 2 - 0
ሰኞ
በርንመዝ ከ ፉልሃም
በርንመዝ ባለፈው ሳምንት ከዌስት ሃም ጋር በነበረው ጨዋታ ማሸነፍ ነበረበት።
ፉልሃም ሊጉ መሪ ሆነውን ሊቨርፑልን በማሸነፍ ብቃቱን አሳይቷል።
ይህ ለመገመት ከባድ ሆነ ጨዋታ ነው።
ግምት፡ 1 - 1












