በእስራኤል እና በሊባኖሱ ሄዝቦላህ መካከል ሙሉ ጦርነት ከፈነዳ ምን ሊከሰት ይችላል?

እስራኤል እና ሄዝቦላህ እሑድ ምሽት ተኩስ ተለዋውጠዋል

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, እስራኤል እና ሄዝቦላህ እሑድ ምሽት ተኩስ ተለዋውጠዋል

ከተከታታይ የሄዝቦላ መሪዎች ግድያ እና ጥቃቶች በኋላ በእስራኤል፣ በሄዝቦላህ እንዲሁም በደጋፊው ኢራን መካከል ያለው ውጥረት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ብሏል።

ቀጥሎ የሚሆነውን ለመተንበይ ቁልፍ የሚሆነው መቀመጫውን በሊባኖስ ያደረገውን ታጣቂ ቡድን ወታደራዊ አቅም እና ከእስራኤል ጋር ያለውን ታሪካዊ ግጭት መረዳት ያስፈልጋል።

ሄዝቦላህ እና እስራኤል በአውሮፓውያኑ በአውሮፓውያኑ 2006 ያካሄዱት ጦርነት 18 ዓመት የሞላው ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ለወራት ዝግ ባለ ሁኔታ ሲካሄድ የነበረው ጦርነት ወደ አዲስ ሁሉን አቀፍ ጦርነት ሊሸጋገር የሚችልበት አጋጣሚ ተፈጥሯል።

በዚህ ውስጥ የእስራኤል የአየር እና የስለላ ወታደራዊ ብልጫ ሲታይ በሌላ በኩል ደግሞ የሄዝቦላህ የሚሳኤል ክምችት እና ወታደራዊ ድሮኖች አጠቃቀም ይጠቀሳሉ።

በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚካሄደው መጠነ ሰፊ ጦርነት ምን እንደሚመስል ለመረዳት ሁለት አስፈላጊ ሁኔታዎች መጤን ይኖርባቸዋል። ከግንቦት 2006 (እአአ) ጦርነት እና በሁለቱ ወገኖች መካከል ለ10 ወራት ያህል ከታዩ ዕለታዊ ግጭቶች በመነሳት ግንዛቤ መውሰድ ያስፈልጋል።

ምንም እንኳን የእስራኤል የላቀ የአየር ኃይል አቅም በሊባኖስ ከፍተኛ ውድመት ሊያስከትል ቢችልም፣ የእስራኤል ጦር ከበርካታ አሥርተ ዓመታት በኋላ በጋዛ የሚያካሂደው የተራዘመ ጦርነት የመዋጋት ሞራሉን አዳክሟል።

ሄዝቦላህ በእስራኤል በደረሰበት የአየር ድብደባ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዡን ፉአድ ሽክርን እና ሦስት ታዋቂ መሪዎቹን ጨምሮ ከ350 በላይ ተዋጊዎቹን ማጣቱን አስታውቋል።

ባለፈው ሳምንት በእስራኤል የተገደለውን የቡድኑን አዣዥ ፉዐድ ሹክርን አስከሬን በዋና ከተማዋ ቤይሩት ውስጥ የሄዝቦላህ ተዋጊዎች ተሸክመው suburbs of the Lebanese capital Beirut on 1 August 2024

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ባለፈው ሳምንት በእስራኤል የተገደለውን የቡድኑን አዣዥ ፉዐድ ሹክርን አስከሬን በዋና ከተማዋ ቤይሩት ውስጥ የሄዝቦላህ ተዋጊዎች ተሸክመው

የሺአ ሙስሊም ፓርቲ የሆነው ሄዝቦላህ ለዓመታት በተደረገው የሶሪያ ጦርነት ውስጥ በመሳተፍ ያገኛቸውን አዳዲስ ልምዶችን ያዳበሩ የጦር አዛዦችን አካቶ ይዋጋል።

ሄዝቦላህ ከኢራን የገንዘብ እና ወታደራዊ እርዳታ ይፈስለታል።

ቡድኑ በአሜሪካ እና በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአንዳንድ የአረብ አገራት እና በበርካታ ምዕራባውያን ዘንድ አሸባሪነት ተብሎ ተፈርጇል።

የሊባኖስ መንግሥት በበኩሉ እስራኤልን የሚቃወም ሕጋዊ ቡድን አድርጎ ይቆጥረዋል። በአገሪቱ በፓርላማ ውስጥ ጉልህ ውክልና ያለው የፖለቲካ ፓርቲ ሆኖም ዕውቅና አግኝቷል።

በእስራኤል ጥቃት በተገደለው የሄዝቦላህ አዛዥ ቀብር ላይ ፎቶውን የያዙ የቡድኑ ደጋፊዎች ቤይሩት ውስጥ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በእስራኤል ጥቃት በተገደለው የሄዝቦላህ አዛዥ ቀብር ላይ ፎቶውን የያዙ የቡድኑ ደጋፊዎች ቤይሩት ውስጥ

እአአ በ2006 ሄዝቦላህ ድንበር ተሻግሮ ስምንት የእስራኤል ወታደሮችን ገድሎ እና ሁለቱን በማገት ከእስራኤል ጋር የእስረኞች ልውውጥ እንዲደረግ መጠየቁን ተከትሎ በሁለቱ ወገኖች መካከል ጦርነት ተካሂዷል።

ታዛቢዎች እንደሚሉት ከሆነ አሁን በእስራኤል እና በሄዝቦላ መካከል ሁሉን አቀፍ ጦርነት ከተቀሰቀሰ እስራኤል በ2006 የገጠማትን ዓይነት ሁኔታ ሊገጥማት ይችላል። ከባድ የአየር ዘመቻ በማድረግ የምድር ጦሯን ታዘምታለች።

በወቅቱ እስራኤል ወታደሮቿን እና የጦር መሳሪያዎቿን ብታሰማራም ሙሉ በሙሉ ዓላማዋን ማሳካት አልቻለችም። ይህ ዓላማዋ ሁለቱን የታገቱ ወታደሮችን ማዳን እና የሄዝቦላህን ወታደራዊ ኃይል መጨፍለቅ ነበር።

በአውሮፓውያኑ 2006 እስራኤል ሊባኖስ ውስጥ የአየር ጥቃት በፈጸመችበት ጊዜ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በአውሮፓውያኑ 2006 እስራኤል ሊባኖስ ውስጥ የአየር ጥቃት በፈጸመችበት ጊዜ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የውሳኔ ሃሳብ ማሳለፉን ተከትሎ ለ34 ቀናት የዘለቀው ጦርነት ቆመ።

እስራኤል ማጥቃቷን ካቆመች በኋላ ሄዝቦላህም እስራኤል ላይ የሚቃጣውን የሚሳኤል ጥቃትን አቆመ።

ሂዝቦላህ እና እስራኤል የውሳኔ ሃሳቡን ጥሰዋል ተብለው ተከሰዋል። ይህ የሆነው ሄዝቦላህ ትጥቁን ባለመፍታቱ እንዲሁም እስራኤል የሊባኖስን ግዛትን ይዛ ከመቆየቷ ባለፈ የሊባኖስን የአየር ክልል በተደጋጋሚ በመጧሳ ነበር።

በአውሮፓውያኑ 2006 የሄዝቦላህ ሮኬት የእስራኤል ከተማ የሆነችውን ሃይፋን በመታበት ጊዜ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በአውሮፓውያኑ 2006 የሄዝቦላህ ሮኬት የእስራኤል ከተማ የሆነችውን ሃይፋን በመታበት ጊዜ

ሄዝቦላህ በእስራኤል ላይ ጥቃት ሰነዘረ

ሐማስ መስከረም ወር ማብቂያ ላይ የፈጸመውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ እስራኤል ጋዛ ላይ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ማካሄድ በጀመረችበት ወቅት ነበር ሄዝቦላህ በእስራኤል ይዞታዎች ላይ ጥቃቶችን መፈጸም የጀመረው።

ይህንን ያደረገው “ጋዛን ለመደገፍ ነው” በሚል ነው። ይህም ሐማስ ዘመቻ አል-አቅሳ ጎርፍ በሚል መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በደቡብ እስራኤል በሲቪሎች እና በወታደሮች ላይ ለከፈተው ጥቃት ቴል አቪቭ ምላሽ መስጠቷትን ተከትሎ ነው።

ሄዝቦላህ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እስኪደረስ ድረስ በጥቃቱ እንደሚገፋ አስታውቋል።

በተጨማሪም በኢራን የሚደገፉት ሄዝቦላህ፣ ሐማስ፣ ኢስላሚክ ጂሃድ፣ ሁቲዎች እና ኢራቅ ቡድኖች የተለያዩ ወታደራዊ ጥምረትን መፍጠር ጀመሩ።

ባለፈው መጋቢት ላይ እስራኤል ውስጥ በሄዝቦላህ ሮኬት የተመታ ሕንጻ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ባለፈው መጋቢት ላይ እስራኤል ውስጥ በሄዝቦላህ ሮኬት የተመታ ሕንጻ

የሄዝቦላህም እና የእስራኤልም ባለሥልጣናት ለጦርነት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። እስራኤል ከሄዝቦላ ጋር በሚደረግ ጦርነት ሊባኖስን ወደ “የድንጋይ ዘመን” እንደምትመልስ ብታስፈራራም ሁለቱም ወገኖች ሁሉን አቀፍ ግጭት እንዳይፈጠር ይመርጣሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በድንበር ተሻጋሪ ጥቃቶች በሊባኖስ ከ90 ሺህ የሚበልጡ (አብዛኞቹ ሲቪሎች) ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል ብሏል። እስራኤል በፈጸመቻቸው ጥቃቶች 100 ንፁሀን ዜጎች እና 366 የሄዝቦላህ ተዋጊዎች ተገድለዋል ሲልም አክሏል።

በእስራኤል ባለሥልጣናት በበኩላቸው 60 ሺህ ንጹሀን ዜጎች ቤታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ እና 33 ሰዎች (10 ሲቪሎች) በሄዝቦላህ ጥቃት ሞተዋል ብለዋል።

ቢቢሲ በደቡባዊ ሊባኖስ ከ3200 በላይ ሕንጻዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በጦርነቱ ምክንያት መጎዳታቸውን የሚያሳዩ የሳተላይት ምስሎች ትንታኔዎችን ይፋ አድርጓል። የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው በሰሜን እስራኤል ከአንድ ሺህ በላይ ሕንጻዎች ተጎድተዋል ብለዋል።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በእስራኤል የአየር ድብደባ በደቡባዊ ሊባኖስ የደረሰ ጉዳት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ከጥቂት ሳምንታት በፊት በእስራኤል የአየር ድብደባ በደቡባዊ ሊባኖስ የደረሰ ጉዳት

በጣም አስቸጋሪው ቡድን”

ሄዝቦላህ “በአሁኑ ጊዜ ለእስራኤል በጣም አስቸጋሪው ቡድን” ሊሆን ይችላል ሲሉ የብሪታኒያ የጦር ኃይል ባለሙያው ጀስቲን ክራምፕ ተናግረዋል። አክለውም ግጭቱ እየሰፋ ከሄደ ትልልቅ ያልታሰቡ ነገሮችን ሊፈጥር ይችላል ብለዋል።

በዩናይትድ ኪንግደም ጦር ውስጥ ለብዙ ዓመታት ያገለገሉት እና በለንደን ሲቢሊን የተባለውን የጦር አማካሪ ድርጅት የመሠረቱት ክራምፕ “ሄዝቦላህ በ2006 የነበረውን ነገር ሁሉ አሻሽሎ፤ ዛሬም አለሁ እያለ ነው” ብለዋል።

የአሜሪካው ማዕከላዊ የስለላ ኤጀንሲ (ሲአይኤ) በበኩሉ ሄዝቦላህ ወደ 150 ሺህ የሚጠጉ ሚሳኤሎች እንዲሁም 45 ሺህ ተዋጊዎች አሉት። የቡድኑ መሪ ሐሰን ናስራላህ ከዚህ ቀደም ከ100 ሺህ በላይ ተዋጊዎች እንዳላቸው ተናግረዋል።

Iron Domeየእስራኤል የሚሳዔል መከላከያ የሆነው አይረን ዶማት የተባለው ሚሳዔል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የእስራኤል የሚሳዔል መከላከያ የሆነው አይረን ዶማት የተባለው ሚሳዔል

በ2006 ከእስራኤል ጋር በተደረገው ጦርነት ቡድኑ ሮኬቶችን እና ፀረ-ታንክ ሚሳኤሎችን እንዲሁም ሩሲያ ሠራሽ የሆነውን ኮርኔት ሚሳኤልን ጨምሮ ዘመናዊ ሚሳኤሎችን በሰፊው ተጠቅሟል።

እስራኤል የአየር የበላይነት ቢኖራትም “ሄዝቦላህ በጣም አስቸጋሪውን ምድር የመጠቀም አቅም አለው። ይህንን ጥንካሬውን ይጠቀምበታል” ሲሉ ክራምፕ ተናግረዋል።

“ሄዝቦላህ አሁን ተሽከርካሪዎቹን እና የሚሳኤል ማስወንጨፊያ ቦታዎቹን ከእስራኤል የአየር ጥቃት በተሻለ ሁኔታ መደበቅ ችሏል። በዚህ ምክንያት የእስራኤል የአየር ጥቃት ብቻውን የቡድኑን የሚሳኤል ጥቃትን ሊያስቆመው አይችልም። ስለዚህ እስራኤል በምድር ወረራ ማድረግን ልታስብ ትችላለች።”

“እኔ [የታንክ አዛዥ] ብሆን ከሄዝቦላህ እና ከፀረ ታንክ ሚሳኤሎቹ ጋር እንዲፋለሙ ታንኮቼን ከሊታኒ ወንዝ ወደ ደቡብ በመላክ ደስተኛ አልሆንም።”

የጦር መሳሪያ እና ሚሳኤል

ሄዝቦላህ የመሳሪያውን መጠን ወይም የሚሳኤሎቹን ዓይነት አይገልጽም። የሚታወቁት ጥቅም ላይ ከዋሉ በኋላ ነው።

ባለፉት ዓመታት ይፋ ተደረጉ በርካታ የስለላ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ኢራን የሄዝቦላህ የጦር መሳሪያዎች ዋና ምንጭ ናት። የጦር መሳሪያዎቹ በኢራቅ እና በሶሪያ በኩል በየብስ ለሄዝቦላህ ይደርሳሉ።

ከእነዚህ መሳሪያዎች መካከል የአልማስ-3 የተባለው አዲስ የኢራን ፀረ-ታንክ ሚሳኤል ሚሳኤሎች ይገኙበታል።

ሄዝቦላህ በ2015 በሶሪያ በተገደለው የቡድኑ መሪ ስም የሚጠራውን የቡርካን እና ጂሃድ ሙግኒዬህን ሚሳኤሎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል ላይ ተጥቅሟል።

በካርዲፍ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት እና በሄዝቦላህ ዙሪያ መጽሐፍ ያሳተሙት አማል ሳድ በበኩላቸው “ዛሬ እያየነው ያለነው ቡድን በ2006 ከተመለከትነው የላቀውን እና የዳበረውን ሄዝቦላህ ነው” ብለዋል።

አክለውም “ሄዝቦላህ የመደበኛ ሠራዊት ባህሪያትን እና የኢመደበኛ ወታደራዊ ቡድኖችን ባህሪያት የሚያጣምር የድብልቅ ጦር መገለጫን ተላብሷል” ብለዋል።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሄዝቦላህ የተተኮሱ ሮኬቶች በእስራኤል ፀረ ሚሳዔል አይረን ዶም አየር ላይ ሲከሽፍ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሄዝቦላህ የተተኮሱ ሮኬቶች በእስራኤል ፀረ ሚሳዔል አይረን ዶም አየር ላይ ሲከሽፍ

ይህ የተባለውም በወታደራዊ አደረጃጀት፣ በመጠን፣ በታክቲክ፣ በሥልጠና ደረጃ እና በሄዝቦላህ ልዩ ኃይል ባለቤትነት ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል። ቡድኑ ያለው የጦር መሳሪያዎች አቅም በተለይም ሚሳኤሎቹ ላይ ይመሠረታል።

የሄዝቦላህ መሪ ሐሰን ናስራላህ ቡድኑ መሐል እስራኤል ድረስ በጥልቀት ሊደርሱ የሚችሉ የላቁ ሚሳኤሎች እንዳሉት ከዚህ ቀደም ተናግረው ነበር።

በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ በሚሰጠው ትንተና የሚታወቀው ጋዜጠኛ እና ለሂዝቦላህ ቅርብ የሆነው አሊ ጃዚኒ ይህ አባባል 300 ኪ.ሜ ሊጓዙ የሚችሉ አጫጭር እና ረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎች እንዳላቸው ፍንጭ ሊሆን ይችላል ብሏል።

ይህ ዓይነቱ ሚሳኤል ለእስራኤል ካለው ቅርበት የተነሳ እና የእስራኤል ጦር ምላሽ ሚሰጥበትን ጊዜ ከመገደቡ አንጻር ቡድኑን ሊጠቅም እንደሚችልም አክሏል። እነዚህ ሚሳኤሎች የኢራኖች ዜልዛል እና ፋቴህ 110 ሊሆኑ ይችላሉ።

በአንዳንድ ሚሳኤሎች ወይም በከፊል ከተሰራጩት አንዳንድ ፎቶዎችም ሄዝቦላህ የሩሲያ ሚሳኤሎችን እየተጠቀመ እንደሆነም ግልጽ ሆኗል።

እንደ ክራምፕ ገለጻ ሄዝቦላህ እነዚህን ሚሳኤሎች ከሶሪያ አግኝቶ ሊሆን ይችላል። ኢራን በርካታ የሩሲያ መሣሪዎችን ቀድታ ታመርታለች። ስለዚህ ለሂዝቦላህ ተመሳሳይ የጦር መሳሪያ ማቅረብ ትችላለች።

የድሮን ጦርነት

ከሚሳኤል በተጨማሪ የወቅቱ የጦርነት ቁልፍ መገለጫ በድሮኖች ላይ ያለው ከፍተኛ ጥገኛነት ነው። በተለይም ሄዝቦላህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሚሳኤሎች የሚገጠሙላቸው ድሮኖች አሉት።

“ሄዝቦላህ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በተሻለ እና ፈጠራ በታከለበት መንገድ እየተጠቀመ ነው” ብለዋል ክራምፕ።

ሄዝቦላህ ከ2006 በፊት ወታደራዊ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ቡድን እንደነበረው የብሪታንያው ወታደራዊ ባለሙያ ገልጸዋል።

“ዛሬ ግን ልክ እንደ ሁሉም የታጠቁ ቡድኖች እና የአገራት ጦሮች ከገበያ በሚገኙ ድሮኖች ላይ የበለጠ አተኩረዋል። ምክንያቱም በጦርነቶች ውስጥ የድሮኖች ሚና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል” ብለዋል።

ጃዚኒ በበኩላቸው ማንኛውም ወታደራዊ ያልሆኑ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በቀላሉ እንዳይወገዱ ማሻሻያ ሊደረግባቸው ይችላል ሲሉ አጥበቀው ይከራከራሉ። ሄዝቦላህ በሰሜናዊ እስራኤል ያሉትን ወታደራዊ ተቋማት ለመቅረጽ ወታደራዊ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መጠቀም እንዳለበት ያምናሉ።

የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሄዝቦላህ ድምፅ አልባ ድሮን መጠቀም መጀመሩን ተናግረዋል።

ሻሂድ 101 የተባለው በኤሌትሪክ ኃይል የሚንቀሳቀስ የኢራን ድሮን ሲሆን፣ በሚበርበት ወቅት ምንም ዓይነት ድምጽ አያሰማም። በተለይ በዝቅተኛ ከፍታ ላይ ስለሚበር እና በራዳሮች በቀላሉ ስለማይለይ ይህም ለመለየት አስቸጋሪ ያደርገዋል።

ለሄዝቦላህ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት ይህ ሰው አልባ አውሮፕላን ቀደም ሲል በየመን እና በኢራቅ ቡድኖች ጥቅም ላይ ውሎ ነበር።

በድሮን አማካይነት አየር ላይ የሚታይ የሄዝቦላህ አርማ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በድሮን አማካይነት አየር ላይ የሚታይ የሄዝቦላህ አርማ

ጃዚኒ በመስከረም 2023 ሄዝቦላህ እና በአሁኑ ሄዝቦላህ መካከል ትልቅ ልዩነት ስለመኖሩ “የእስራኤል ጦር በሲግናል ስለላ እና በኮሙኒኬሽን ዘርፍ በዓለም ላይ እጅግ የላቀ ቴክኖሎጂ አለው። ስለዚህ ሄዝቦላ ከድንበር 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው ሳፌድ የሰው አልባ አውሮፕላኖችን መላኩ ከእስራኤል የቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር በተያያዘ ትምህርት መውሰዱን ያሳያል” ብለዋል።

ከድሮኖቹ አቅም ማሳያ ባለፈ ሄዝቦላህ በርካታ እጅግ የተራቀቁትን ሄርሜስ 450 ወይም ሄርሜስ 900 የተባሉ የእስራኤል ድሮኖችን መምታት መቻሉ ወይም የጦር አውሮፕላኖች ከሊባኖስ አየር ክልል ለቀው እንዲወጡ ማድረጉን ማስታወቁን አንዳንዶች እንዲናገሩ አድርጓቸዋል።

ታዛቢዎች ግን ይህ በጣም የተጋነነ ነው ብለው ያስባሉ።

ጃዚኒ “የአየር ኃይል የበላይነት ጉዳይ ውስብስብ ነው። ምክንያቱም አውሮፕላን ላይ ማነጣጠር ብቻ ሳይሆን፣ ከቀጣይነቱም ጋር የተያያዘ ነው። አውሮፕላኖችን ለ10 ቀናት የመጣል አቅም እና ከዚያ በኋላ ግን ምንም ማድረግ አለመቻልን አስቡት? ባለው ግብም ይወሰናል። ግቡ የእስራኤልን ጥቃት መቀነስ ከሆነ ግቡ ላይ ይደረሳል” ብለዋል።

“በተጨባጭ ካየነው ሄዝቦላህ የእስራኤል አየር ኃይል በሊባኖስ የአየር ክልል ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንዳይሠማራ ለመከልከል ብዙ ይቀረዋል” ሲሉ አክለዋል።

ሄዝቦላህ በዝቅተኛ ከፍታ ላይ የሚበሩትን የእስራኤል አውሮፕላኖች ሊገድብ ይችላል ብለው ከሚያምኑት ከክራምፕ ግምገማ ጋር የሚመሳሰል ነው። ሆኖም ግን እስራኤል በከፍታ ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች። እናም “ሄዝቦላ የአየር ክልሉን ከእስራኤል አውሮፕላኖች መዝጋት አይችልም” ብለዋል።

የሄዝቦላህ ተዋጊዎች በልምምድ ላይ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የሄዝቦላህ ተዋጊዎች በልምምድ ላይ

“የመከላከያ ትብብር”

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ክራምፕም አክለውም ሄዝቦላህ የየመን ሁቲዎች የሚጠቀሙበት መሳሪያ ሊኖረው እንደሚችል ያምናሉ። ሐማሶች ወይም ሁቲዎች ያላቸውን እና ሌሎች የጦር መሣሪያዎች ባለቤት ሊሆን እንደሚችልም ያምናሉ።

“እነዚህ ቡድኖች ልምዶችን፣ ቴክኖሎጂዎችን እና የጦር መሣሪያዎችን ይጋራሉ። ሄዝቦላህ ደግሞ ከእነሱ በጣም የላቀ ነው።”

አማል ሳድ እንደሚሉት ከሆነ ጦርነቱ ይስፋፋል ተብሎ የሚገመተው የትኛውም ትንበያ እየተካሄደ ያለውን አውድ ማለትም እስራኤልን በመቃወም በአንድ የሚንቀሳቀሱትን የተለያዩ ወታደራዊ ቡድኖችን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት “የመከላከያ ትብብር” ይመለከታል።

“ቀደም ሲል 'አንድነት' የሚባል ነገር አልነበረም። ዛሬ እየታገሉ ያሉት እየተጠናከረ ሊሄድ በሚችል ስልታዊ ጥምረት ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

ይህ ትብብር በኢራን የሚደግፉ ወታደራዊ ቡድኖችን የያዘ ቢሆንም እያንዳንዳቸው የተለየ መለያ አላቸው።

አብዛኞቹ እነዚህ ቡድኖች በአሜሪካ እና በአንዳንድ የአረብ አገራት በአሸባሪነት የተፈረጁ ናቸው።

ትብብሩ ከሊባኖሱ ሂዝቦላህ በተጨማሪ የፍልስጤሙ ሐማስ፣ ኢስላሚክ ጂሃድ፣ በየመን የሁቲ አንሳር አላህ እና የኢራቅ ቡድኖችን ያጠቃልላል።

እነዚህ ቡድኖች ከሄዝቦላህ ጋር በሚኖረው ጦርነት ውስጥ ስለሚኖራቸው ሚና አይታወቅም። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “በሊባኖስ ውስጥ ለሚደረጉ ማናቸውም አዳዲስ ድርጊቶች ያልተጠበቀ ውጤት ይኖራል” ሲሉ እስራአኤልን አስጠንቅቀዋል።

እአአ በ2006ቱ ጦርነት እና ሐማስ በደቡብ እስራኤል መስከረም 26 ባደረሰው ጥቃት መካከል በሊባኖስ እና በእስራኤል መካከል ያለው የድንበር አካባቢ ለረዥም ጊዜ የተረጋግቶ ቆይቷል።

ይህ ግን በምንም መልኩ ለመጪው ነገር ቅድመ ዝግጅት አልተደረገም ማለት አይደለም። ምናልባት ይህ በቅርቡ ሊሆን ይችላል።