ቢትኮይንን ለሁሉም አገልግሎትና ግብይት የምትጠቀመው አገር

የቢትኮይን ዋጋ ከሌላው ጊዜ በተለየ በእዚህ ሳምንት በጣም ቀንሷል። የኤል ሳቫዶር መንግሥት ግን ቢትኮይንን ሕጋዊ መገበያያ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል።

ይህንን ለማበረታታትም በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ነው። ይህ ውሳኔ ከተወሰነ ከ9 ወር ወዲህ መንግሥት 200 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለቢትኮይን ፈሰስ አድርጓል።

አሁን ደግሞ የውሻ ባለቤቶች በቢትኮይን የሚከፍሉ ከሆነ በጣም በርካሽ እንዲታከሙ አንድ ሆስፒታል አመቻችቷል።