ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች የገና በዓልን እንዴት እንደሚያከብሩ የሚያሳዩ ፎቶዎች
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኦሮቶክስ ክርስትና ምዕመናን ወደ አብያተ-ክርስትያናት በማቅናት የገና በዓልን እያከበሩ ይገኛሉ።
ምንም እንኳ አብዛኛው የዓለም ክፍል የገና በዓልን ታኅሣሥ 16 ቢያከብርም 200 ሚሊዮን ገደማ ለሚሆኑ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች የጌታ ልደት ቀን የሚውለው ታኅሣሥ 29 ነው።
ይህ የሆነው ምዕመናኑ የጁሊያን ጊዜ መቁጠሪያን ስለሚከተሉ ነው። የተቀረው የክርስትና እምነት ተከታይ የሚከተለው ደግሞ የግሪጎሪን የጊዜ መቁጠሪያ ነው።
ቦሌ በሚገኘው መድኃኒዓለም ቤተ-ክርስትያን የገና ዋዜማ በድምቀት የተከበረ ሲሆን በርካታ ምዕመናን በቤተ-ክርስትያኗን ቅጥር ግቢ እና በአካባቢው ጧፍ እያበሩ በዝማሬ ዋዜማውን አክብረውታል።
የገና በዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው ሌላኛው ስፍራ ላሊበላ ነው። በላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስትያናት ዋዜማው እና በዓሉ በድምቀት ይከበራል።