በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች የገና በዓልን እንዴት እንደሚያከብሩ የሚያሳዩ ፎቶዎች
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኦሮቶክስ ክርስትና ምዕመናን ወደ አብያተ-ክርስትያናት በማቅናት የገና በዓልን እያከበሩ ይገኛሉ።
ምንም እንኳ አብዛኛው የዓለም ክፍል የገና በዓልን ታኅሣሥ 16 ቢያከብርም 200 ሚሊዮን ገደማ ለሚሆኑ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች የጌታ ልደት ቀን የሚውለው ታኅሣሥ 29 ነው።
ይህ የሆነው ምዕመናኑ የጁሊያን ጊዜ መቁጠሪያን ስለሚከተሉ ነው። የተቀረው የክርስትና እምነት ተከታይ የሚከተለው ደግሞ የግሪጎሪን የጊዜ መቁጠሪያ ነው።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, ምዕመናን በሶሪያ መዲና ደማስቆ በአርሜኒያን አፖስቶሊክ ማር ሳርኪስ ቤተ-ክርስትያን ተገኝተው በዓሉን እያከበሩ ይገኛሉ። ይህ ከባሽር አል-አሳድ መንግሥት መውረድ በኋላ በሶሪያ የመጀመሪያው ገና ነው።
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, በመካከለኛው ምስራቁ ትልቁ የክርስትና ማኅበረሰብ የሆነው የግብፅ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ምዕመናን በመዲናዋ ካይሮ በሚገኘው በቅዱስ ሚካዔል ኮፕቲክ ቤተ-ክርስትያን ተገኝተው በዓሉን ያከብራሉ።
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, በዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ሻራጃህ ኦሮቶዶክስ ምዕመናን የገና ዋዜማን በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን ተገኝተው አክብረዋል።
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, ኢየሱስ ክርስቶስ የተወደለባት ናት በምትባለው የዌስት ባንኳ ቤቴልሔም ምዕመናን እና የኃይማኖት አባቶች በዋዜማው ተሰባስበው ቅዳሴ ታድመዋል
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, ኢትዮጵያዊያን የኦሮቶዶክስ እምነት ተከታዮች በቦሌ የመድኃኒአለም ቤተ-ክርስትያን ተገኝተው ጧፍ በማብራት እና በዝማሬ ታጅበው የገና በዓል ዋዜማን አክብረዋል። ቦሌ በሚገኘው መድኃኒዓለም ቤተ-ክርስትያን የገና ዋዜማ በድምቀት የተከበረ ሲሆን በርካታ ምዕመናን በቤተ-ክርስትያኗን ቅጥር ግቢ እና በአካባቢው ጧፍ እያበሩ በዝማሬ ዋዜማውን አክብረውታል።
የገና በዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው ሌላኛው ስፍራ ላሊበላ ነው። በላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስትያናት ዋዜማው እና በዓሉ በድምቀት ይከበራል።

የፎቶው ባለመብት, EPA
የምስሉ መግለጫ, በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሩሲያዊያን በዓሉን እያከበሩ ሲሆን ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን (በስተግራ) በሞስኮው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስትያን ተገኝተው በዓሉን አክበረዋል።
የፎቶው ባለመብት, EPA
የምስሉ መግለጫ, ሞስኮው በመብራት ደምቃ የገና በዓልን በማክበር ላይ ትገኛለች
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, በሰርቢያ መዲና ቤልግሬድ ልዑል ፊሊፕ በሀገሪቱ ባሕል መሠረት ችቦ በማብራት የገና በዓልን አብስረዋል
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, በአርሜኒያ መዲና የሬቫን የአርሜኒያ አፖስቶሊክ ክርስትያኖች በቅዱስ ግሪጎሪ ካቴድራል ተገኝተው ቅዳሴ ታድመዋል
የፎቶው ባለመብት, AFP
የምስሉ መግለጫ, በጆርጂያ መዲና ቲብሊሲ ምዕመናን ሻማ አብርተው ነው በዓሉን የተቀበሉት