የኬንያ መንግሥት በፕሬዚደንቱ ላይ ጫማ የተወረወረበትን ክስተት "አሳፋሪ' ሲል አወገዘ

የኬንያ መንግሥት እሁድ ዕለት በተካሄደው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ በአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ላይ ጫማ የተወረወረበትን ክስተት "አሳፋሪ" ሲል አወገዘ።

በሰፊው የተጋሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደሚያሳዩት ፕሬዚዳንቱ ንግግር ሲያደርጉ የተወረወረው ጫማ ወደ ላይ ከፍ ያደረጉትን ግራ እጃቸውን መትቷል።

የመንግሥት ቃል አቀባይ አይዛክ ምዋውራ የሆነውን አውግዘው ከጀርባው ያሉት "እንዲያዙ" ጠይቀዋል።

"ሁላችንም ጫማ ለመወርወር ብንወስን ምን ይሆናል? ልጆቻችንን ምን ዓይነት እሴቶች እያስተማርን ነው?" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ እንዲከበሩ በ ኤክስ ገጻቸው ላይ ባጋሩት ልጥፍ ጠይቀዋል።

የኬንያ መገናኛ ብዙኃን ሦስት ሰዎች መያዛቸውን እየዘገቡ ቢሆንም ፖሊስ ግን ይህን አላረጋገጠም።

አንዳንድ የፓርላማ አባላትም ከፍተኛ የጸጥታ ክፍተት መሆኑን በማንሳት ጫማ መወርወሩን ተችተዋል።

ክስተቱ የተፈጸመው ፕሬዝዳንቱ በምዕራብ ሚጎሪ አውራጃ በተካሄደው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ንግግር እያደረጉ ባሉበት ወቅት ነው።

ፕሬዝዳንት ሩቶ ወደ አካባቢው ያቀኑት በክልሉ ለሦስት ቀናት የሚቆይ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማስጀምር ነው።

የአንዳንድ ኬንያውያን ጫማ መወርወሩ ክብር የጎደለው ነው የሚል ስሜት ቢያንጸባርቁም፣ ሌሎች ደግሞ ይህ በኢኮኖሚው ላይ ያለውን ብስጭት ያሳያል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በኤክስ ላይ በፕሬዚዳንቱ የተጋራው የክስተቱ ኦፊሴላዊ ቪዲዮ ከካሜራ ውጭ የተከሰተ የሚመስለውን የጫማ ውርወራ አያሳይም።

ይኹን እንጂ በሕዝቡ መካከል ያለው ግርግር በአጭሩ ይታያል።

ፕሬዚዳንቱ ወንጀለኛውን እየፈለጉ የነበሩትን የደህንነት መኮንኖቻቸው የድርጊቱ ፈጻሚዎቹን ብቻቸውን ለታዳሚው እንዲተውላቸው ሲጠይቁ ተደምጠዋል።

ጫማ መወርወሩ የተከሰተው በሕዝብ ባለስልጣናት ደህንነት ላይ ስጋት እየጨመረ በመጣበት ወቅት ነው።

ባለፈው ሳምንት አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ አባል በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በሞተር ሳይክል ላይ በነበሩ ታጣቂዎች ተገድለዋል።

የፕሬዚዳንቱ ፓርቲ የፓርላማ አባል ኔልሰን ኮይክ የእሁዱ ክስተት "ዲሞክራሲያችንን የሚነካ ነው" ካሉ በኋላ "ቀልዱ ድንበሩን አልፏል" ብለዋል።

"ይህ ጫማ ጥይት ቢሆን ኖሮ መገመት ትችላለህ... ሰዎች በፕሬዚደንቱ ደህንነት ላይ ይቀልዳሉ። አንድ ሰው ጫማውን አውልቆ በፕሬዚዳንቱ ላይ በመወርወሩ በጣም ድፍረት የተሞላበት እርምጃ ወስዷል።

"የአገሪቱን ፕሬዝዳንት መጠበቅ አለብን" ሲሉ ለሲቲዝን ቲቪ ተናግረዋል።

ሚጎሪ በ2022 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሩቶ ተፎካካሪ የነበሩት አንጋፋው የተቃዋሚ እና በኋላ ላይ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ስምምነት ላይ የደረሱት ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ ጠንካራ ደጋፊዎች ይገኙበታል ተብሎ በሚታሰበው ክልል ውስጥ ትገኛለች።

ባለፈው ዓመት ከተካሄደው ተከታታይ የፀረ-ታክስ ሰልፎች በኋላ በመጋቢት ወር በኦዲንጋ እና ሩቶ መካከል "በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ውጥረት ለማርገብ" ስምምነት ተፈርሟል።

ሩቶ እንደ አውሮፓውያኑ በ 2022 ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ በኑሮ ውድነት እና በታክስ ጭማሪ ምክንያት ከኬንያውያን ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።