ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አርሰናል ከማንቸስተር ዩናይትድ - ማን ያሸንፋል? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት
የ14ኛው ሳምንት እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ሲካሄዱ አርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።
ሊቨርፑል ሊጉን በዘጠኝ ነጥብ መምራት ጀምሯል። ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ ተንሸራቷል።
በዋንጫው ፉክክር ውስጥ አርሰናል እና ቼልሲ መካተታቸውን የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን አስታውቋል።
ሱተን ተጠባቂውን ጨዋታ ጨምሮ በሳምንቱ አጋማሽ የሚከናወኑ የሊጉን ጨዋታዎች በሙሉ ገምቷል።
ማክሰኞ
ኢፕስዊች ከ ክሪስታል ፓላስ
ቅዳሜ እለት ኢፕስዊች ጥሩ ቢጫወትም ከፍጹም ቅጣት ምት በተቆተረበት ግብ ለመሸነፍ ተገዷል። ክሪስታላ ፓላስ ደግሞ ከኒውካስል ጋር ነጥብ ታገርቷል።
ፓላስ ጥሩ ቡድን ቢሆንም ውጤት ከወዲሁ መሰብሰብ ካልጀመረ የመውረድ አደጋ ይገጥመዋል።
ሁለቱም ቡድኖች በመጀመሪኣዎቹ 13 የሊግ ጨዋታዎች አንድ አንድ ድል ብቻ አስመዝግበዋል።
ሁለቱም ለማሸነፍ ስለሚፈልጉ ጨዋታው በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ይመስላል።
ግምት፡ 1 – 1
ሌስተር ከ ዌስት ሃም
ሁለቱም ቡድኖች በሳምቱ መጨረሻ በሰፊ የጎል ልዩነት ተሸንፈዋል። የዌስትሃሙ አሰልጣኝ ዩሊየን ሎፕቴግዩ በሽንፈቱ ምክንያት ጫናው በርትቶባቸዋል።
የሌስተር ደካማ የተከላካይ መስመር የመጀመሪያ ጨዋታውን በሚያደርገው አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኒስተልሮይ የሚቀረፍ አይመስልም።
ዌስት ሃም እስካሁን አሳማኝ ቡድን ባይሆንም የአጥቂ መስመሩ ለቡድኑ ሦስት ነጥብ ሊያስገኝ ይችላል።
ግምት፡ 1 – 2
ረቡዕ
ኤቨርተን ከ ዎልቭስ
ኤቨርተን ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በነበረው ጨዋታ ጥሩ ቢጀምርም እንደተለመደው የአጨራረስ ችግር አለበት። ዎልቭስ ደግሞ ጎሎችን ማስቆጠር ቢችልም ተከላካይ መስመሩ ስስ ነው።
የጋሪ ኦኒዬል ቡድን ባለፉት 13 ጨዋታዎች 32 ጎሎችን አስተናግዷል።
የኤቨርተኑ ሾን ዳይሽ ጫናው ቢበረታባቸውም የክለቡን ችግር ወደ አሰልጣኙ መጎተት ተገቢ አይመስልም።
በውጤት መጥፋቱ ቢጠየቁም ቡድኑን ለማሻሻል ተጫዋች አለማግኘታቸው ግን ውጤት እንዲርቃቸው አድርጓል።
ግምት፡ 2 – 1
ማንቸስተር ሲቲ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት
የሲቲ ውጤት ሊቀየር የሚገባው ቢሆንም በዚህ ረገድ ምንም ፍንጭ እየታየ አይደለም።
ዘንድሮ ሊቨርፑል በማሸነፍ ብቸኛው የሆነው ፎረስት በዚህ ጨዋታም ውጤት ለማግኘት ጥረት ያደርጋል።
የኑኖ እስፕሬንቶ ሳንቶ ቡድን በመከላከል ረገድ ድንቅ በመሆኑ ሲቲ ውጤት ለማግኘት ይቸገራል።
ሲቲ ጥሩ ተጫዋቾች ቢኖሩትም ወደ ሙሉ አቋሙ አልተመለሰም። ፎረስት ደግሞ በአካላዊ ብቃት ረገድ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋቾች በራስ መተማመን ጥሩ ባለመሆኑ ቡድኖች የልብ ልብ ተሰምቷቸዋል።
ግምት፡ 2 – 2
ኒውካስል ከ ሊቨርፑል
ኒውካስል ባለፉት ጨዋታዎች ወደ ጥሩ አቋሙ አለመመለሱን አሳይቷል።
ከሪያል ማድሪድ እና ከማንቸስተር ሲቲ ድል በኋላም ይህ ለሊቨርፑል አዲስ ፈተና ነው።
ኒውካስል ዘንድሮ አርሰናልን ቢያሽነፍም የሊጉን መሪ ለመርታት በጥሩ አቋም ላይ አይገኙም።
አርን ስሎት ከቋሚ ቡድናቸው ውጭ ያሉ ተጫዋቾችም ጠንካራ በመሆናቸው የተለያየ መንገድ ተጠቅመው ለማሸነፍ እይላሉ።
ግምት፡ 1 – 2
ሳውዝ ሃምፐተን ከ ቼልሲ
የሳውዝሃምፕተኑ አሰልጣኝ ረስል ማርቲን ባለፈው አርብ ከብራይተን ጋር አቻ መለያየታቸው ጥሩ ቢሆንም የተሻረባቸው ጎል ግን የሚኣስቆጫቸው ነው።
ሁለቱም ቡድኖች ሳቢ የሆነ አጨዋወትን ቢመርጡም ቼልሲ ሦስቱን ነጥብ ያሳካል።
የኤንዞ ማሬስካ ቡድን ጥሩ ተጫዋቾችን ከመያዙም በላይ በጥሩ አቋም ላይ ይገኛሉ።
ድንቅ ብቃቱን እያስመሰከረ የሚገኘው አጥቂው ኖከላስ ጃክሰንም መረሳት የለበትም።
ግምት፡ 0 – 2
አርሰናል ከ ማንቸስተር ዩናይትድ
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በቃለ መጠይቅ ወቅት ያለው አቀራረብ በደጋፊዎች ዘንድ የፈጠረው ደስታ የሚጠበቅ ነው።
በመጀመሪያዎቹ ሦስት ጨዋታዎች ባለመሸነፍ ጥሩ አጀማመር ቢያደርግም ይህ መርሃ ግብር ግን ቡድኑ ያለበትን ደረጃ ለመገምገም የሚረዳ የመጀመሪያው ፈተናው ነው።
ሁለቱ ቡድኖች ከዓመታት በፊት ድንቅ ፉክክር ቢያሳዩንም አሁን ግን አርሰናል ከዩናይትድ ርቆ ተቀምጧል። የአምበሉ ማርቲን ኦዴጋርድ መመለስ ቡድኑን ወደ ሚጠበቅበት ደረጃ መልሶታል።
አይሳካም እንጂ ዩናይትድ ወደ ኤምሬትስ ተጉዞ ነጥብ ማግኘት ከቻለ ትልቅ መልዕክት ይኖረዋል።
ባለፉት ጨዋታዎች አርሰናል በርካታ ጎሎችን ያስቆጠረበት ሂደት ይቀጥላል። አርሰናል ያሸንፋል ብቻ ሳይሆን በጥሩ መልኩ ያሸንፋል።
ግምት፡ 3 – 1
አስቶን ቪላ ከ ብሬንትፎርድ
ብሬንትፎርድ ከሜዳው ውጭ ደካማ ቢሆንም ጎሎችን ማስቆጠር ግን ይችላል።
እንአስቶን ቪላ አይነት የተከላካይ መስመሩ ደከመ ቡድን ብሬትፎርድን መግጠም አይፈልግም።
እንደማንቸስተር ሲቲ ሁሉ ቪላም ከገባበት ቀውስ ለመውጣት ትልቅ ውጤት ማስመዝገብ ይፈልጋል።
አስልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ጫና ውስጥ ባይሆኑም ውጤታቸውን ማስተካከል ይኖርባቸዋል።
ይህ ጨዋታ ደግሞ ትክክለኛው አጋጣሚ ይመስላል።
ግምት፡ 2 – 1
ሐሙስ
ፉልሃም ከ ብራይተን
ፉልሃም በሳምንቱ መጨረሻ ከቶተንሃም ጋር በነበረው ጨዋታ ጥሩ ተንቀሳቅሷል።
ከብራይተን ጥሩ መሆን ጋር ተያይዞ ይህንን ጨዋታ ፉልሃም ያሸንፋል ለማለት ይከብዳል።
ሁለቱም ቡድኖች የሚያሽንፉበትን የተለያየ ምክንያት ማቅረብ ቢቻልም ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ማለት የተሻለው አማራጭ ነው።
ግምት፡ 1 – 1