አርሰናል ከዌስት ሀም፡ የሱተን ግምት ምን ይላል?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ዩናይትድ በሜዳው፤ በደጋፊው ፊት አሁንም ሽንፈትን ይቀምሳል ቢልም ዩናይትድ በድል አጠናቋል።
ሌሎችም የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች ማክሰኞና ረቡዕ ተካሂደዋል።
ዛሬ ምሽት 4፡30 ብራይተን ከቶተንሃም ቀጥሎ ምሽት 5፡15 ደግሞ አርሰናል ከዌስት ሀም ይጫወታሉ።
የቢቢሲ ስፖርት ተንታኙ ክሪስ ሱተን ሁሉንም 380 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምቱን መስጠቱን ቀጥሏል።
* ማክሰኞ እና ረቡዕ የነበሩት ጨዋታዎችን ውጤት ከሱተን ግምት ግርጌ አስቀምጠናል።

ብራይተን ከ ቶተንሃም
ስለዚህ ጨዋታ ሳስብ ቀድሞ ወደ አእምሮዬ የመጣው ብዙ ጎል የምንመለከትበት ጨዋታ እንደሚሆን ነው።
ቶተንሃም የዋንጫ ፉክክር ውስጥ እንዳሉ ይሰማኛል። ግን ኤቨርተንን ያሸነፉት በዕደል ጭምር እንደሆነ አስባለሁ።
ብራይተን ደግሞ ባለፈው ዓመት የነበራቸውን አይነት ምርጥ ብቃት እያየሁት አይደለም። ጎል ቢያስቆጥሩም በቶተነሃም ሊሸነፉ እንደሚችሉ እገምታለሁ።
ግምት፡ ብራይተን 2 - 3 ቶተንሃም

አርሰናል ከ ዌስት ሃም
ይህ ለአርሰናል ፈታኝ የሆነ ጨዋታ እንደሚሆን እገምታለሁ። ዌስት ሃም ጥሩ አቋም ላይ ይገኛል። በደረጃ ሰንጠረዡ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ይሁን እንጂ ይህን ጨዋታ አርሰናል እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። በሜዳቸው 7 ተከታታይ ጨዋታዎችን እንደማሸነፋቸው የዌስት ሃም እጣም ሸንፈት እንደሚሆን አስበላሁ።
ግምት፡ አርሰናል 3 - 0 ዌስት ሃም
ማክሰኞ

ኒውካስል ከ ፎረስት
ኤዲ ሃው ከዚህ ጨዋታ ሙሉ ነጥብ መሰብሰብ መቻል አለባቸው ምክንያቱም ኒውካስል የሚጥለው ውጤት አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል።
ኒውካስል በሁሉም ውድድሮች ካለፉት 6 ጨዋታዎች በአምስቱ ተሸንፏል።
ሴንት ፓርክ ጄምስ እንደመጫወታቸው በደጋፊዎቻቸው ታጅበው ፎረስትን ያሸንፋሉ የሚል ግምት አለኝ።
ታዲያ አዲሱ የፎረስት አሰልጣኝ ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ ቡድኑን ወደ ወራጅ ቀጠና እንዳይገባ የሚያደርጉት ጥረት ማየት አጓጊ ነው።
ግምት፡ ኒውካስል 2 - 0 ፎረስት
* ውጤት፡ 1 - 3
ቦርንመዝ ከ ፉልሃም
ዶሚኒክ ሶላንኬ የሚያቆመው ያለ አይመስልም። ይህን ብቃት ያሳያል የሚል ግምትም አልነበረኝም። በተመሳሳይ ፉልሃም በሜዳው በበርንሊ ይሸነፋል ብሎ መገመትም ከባድ ነበር።
የዚህን ጨዋታ ውጤት መገመት እንዲሁ ከባድ ነው።
ግን የቅርብ ጊዜ ውጤትን ከግምት በማስገባት ሁለቱም ቡድኖች ግብ እንደሚያስቆጥሩ እና ቦርንመዝ ይህን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።
ግምት፡ ቦርንመዝ 2 - 1 ፉልሃም
* ውጤት፡ 3 - 0

ሼፊልድ ዩናይትድ ከ ሉተን
እነዚህ ሁለት ክለቦች በቅርቡ ያሳዩት እንቅስቃሴ በእርግጠኝነት ከሊጉ ተሰናባች ይሆናሉ የሚል ግምትን ዳግም እንድናጤን ሊያደርግ ይችላል።
በተለይ ሉተን ኒውካስልን ማሸነፋቸው እጅግ በጣም ነው ያስደነቁኝ። ሼፊልድም ቢሆን ወደ ቪላ ተጉዞ ትልቅ የሚባሉት ክለቦች ማግኘት ያልቻሉትን ውጤት ይዘው ተመልሰዋል።
አዲሱ አሰልጣኝ ክሪስ ዋይልደር በሜዳቸው አንድ ድልን ከዚህ ቀደም አጣጥመዋል። ሁለተኛ ድላቸውንም ነገ ያገኛሉ ብዬ እገምታለሁ።
ግምት፡ ሼፊልድ ዩናይትድ 1 - 0 ሉተን
* ውጤት፡ 2 - 3
በርንሊ ከ ሊቨርፑል
በርንሊ ወደ ፉልሃም ሜዳ አቅንቶ ያስመዘገበው ድል በጣም ወሳኝ ነው። አሁንም በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ክለብ ላለመውረድ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደርጋል።
ሊቨርፑል በአንጻሩ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አጥቅቶ እየተጫወተ 47 የጎል ሙከራዎችን ቢያደርግም ማስቆጠር የቻለው ግን አንድ ግዜ ብቻ ነው። ታዲያ ከ47ቱ 34 የጎል ሙከራዎችን ያደረገው ዩናይትድ ላይ ነው።
የክሎፑ ሊቨርፑል ይህን ጨዋታ እንደሚያሸንፉ እገምታሉ።
ግምት፡ በርንሊ 0 - 3 ሊቨርፑል
* ውጤት፡ 0 - 2

ዩናይትድ ከ ቪላ
በጠባብ ውጤት የሚጠናቀቅ ጨዋታ ቢሆንም ቪላ ይህን ጨዋታ የሚያሸንፍ ይመስለኛል። ዩናይትድ ለአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ጎል ያስቆጥራል ብዬ አልጠብቅም።
ቀያይ ሴጣኖቹ በ18 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ኳስን ከመረብ ማገናኘት የቻሉት 18 ጊዜ ብቻ ነው። በሊጉ ያነሰ ግብ ያስቆጠረው ሼፊልድ ዩናይትድ ብቻ ነው። ይህን የሚያሳየው የቴን ሃግ ቡድን አሳሳቢ የሆነ የአጥቂ ችግር እንዳለበት ነው።
ታዲያ ዩናይትድ ወጥ አቋም፤ በሁሉም አሰላለፍ ላይ የተመጣጠን ቡድን የሆነውን ቪላን ያሸንፋል ብዬ አልጠብቅም።
ቪላ ምንም እንኳ ከሜዳቸው ውጪ ያን ያክል አስፈሪ ባይሆኑም ዩናይትድን ለማሸነፍ አንድ ግብ ይበቃቸዋል።
ግምት፡ ዩናይትድ 0 - 1 ቪላ
* ውጤት 3 - 2
ብሬንትፈርድ ከ ዎልቭስ
ብሬንትፈርድ ካለፉት ስድስት ጨዋታዎች በአምስቱ ጨዋታዎች ተሸንፏል። እንዲሁ በተመሳሳይ ዎልቭስ በሞለኒዩ በቼልሲ ላይ ካስመዘገቡት ድንቅ ውጤት ውጪ ይህ ነው የሚባል ወጥ አቋም እያሳዩ አይደለም።
ይህን ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ያሸንፋሉ ብዬ እገምታለሁ።
ግምት፡ ብሬንትፈርድ 2 - 0 ዎልቭስ
* ውጤት 1 - 4

ቼልሲ ከ ፓላስ
ቼልሲ በሜዳው እና ከሜዳው ውጪ የማይጠበቅ ሽንፈትን ሲያስተናግድ መጥቷል። ፓላስን በስታንፈርድ ብሪጅ ማስተናገዱ ምንም የሚጠቅመው አይመስለኝም።
ምንም እንኳ ፓላስ ቼልሲን እንደሚፈትን ብገምትም ይህን ጨዋታ የፖቸቲኖ ቡድን ሊያሸንፍ እንደሚችል እገምታለሁ።
ግምት፡ ቼልሲ 2 - 1 ፓላስ
* ውጤት 2 - 1
ኤቨርተን ከ ማንቸስተር ሲቲ
ኤቨርተን እየተጫወተ ያለበት ሁኔታ በጣም አስደሳች ነው። በጉዲሰን ፓርክ ሻምፒየኖቹን እንደሚፈትኗቸው አስባለሁ።
ሲቲዎች ወደ አስፈሪ አቋመቸው በቅርቡ እንደሚመለሱ እገምታለሁ። ይህ ግን ከኤቨርተን በሚያደርጉት ጨዋታ የሚጀምር አይመስለኝም።
ኤቨርተን ከጥሩ ባህሪያቸው መካከል አንዱ ያለ ማቋረጥ በትጋት ተጋጣሚዎቻቸውን መፈተናቸው ነው። በዚህ ጨዋታ ከሲቲ ነጥብ ተጋርተው የሚወጡ ይመስለኛል።
ግምት፡ ኤቨርተን 1 - 1 ማንቸስተር ሲቲ
* ውጤት፡ 1 - 3












