ኢትዮጵያ እስካሁን በኦሊምፒክ ያገኘቻቸው ሜዳሊያዎች ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር ሲነጻጸር

የአፍሪካ አገራት በተለያዩ የኦሊምፒክ ውድድሮች የሚሳተፉት በውስን የስፖርት ዓይነቶች ነው። የአትሌቲክስ ስፖርቶች በተለይ ደግሞ የረጅም ርቀት የሩጫ ውድድሮች ለአፍሪካ ወርቅን የሚያስገኙ ዘርፎች ናቸው።
በዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ዋነኛወነ ስፍራ ይይዛሉ። ደቡብ አፍሪካ በበርካታ የስፖርት ዘርፎች በመሳተፍ ከአፍሪካ ቀዳሚ ቦታውን የምትይዝ ስትሆን፣ በዚህም በርከት ያሉ ሜዳሊያዎችን ለማግኘት ችላለች።
እስካሁን በተካሄዱ የኦሊምፒክ ውድድሮች አጠቃላይ በርካታ ሜዳሊያዎችን በማግኘት፣ ከፍተኛውን የወርቅ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ እንደ ቅደም ተከተላቸው ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ያለውን ቦታ ይዘዋል።
ሦስቱ አገራት በእስካሁኖቹ ኦሊምፒኮች በአጠቃላይ ከ20 በላይ የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ ከሌሎቹ የአፍሪካ አገራት ርቀው ይገኛሉ።
ለንጽጽር በአፍሪካ አገራት የሜዳሊያ ሠንጠረዥ በአራተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ግብፅ እካሁን በኦሊምፒክ ውድድር ያገኘችው የወርቅ ሜዳሊያ ስምንት ብቻ ነው።
ከታች ያሉት የምሥል መረጃዎች የአፍሪካ አገራት በኦሊምፒክ ውድድሮች እስካሁን ያሸነፏቸውን ሜዳሊያዎች በዝርዝር ያሳያሉ።
ለመሆኑ ኢትዮጵያ ከኬንያ እና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ስትነጻጸር ምን ያህል የኦሊምፒክ የወርቅ፣ የብር እና የነሐስ ሜዳሊያዎችን አሸነፈች?








