በናይጄሪያ ሰራተኞች አድማ ለማድረግ እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት የደመወዝ ጭማሪ ተደረገ

በናይጄሪያ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ ባቀዱበት ሰዓት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ በዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ላይ ለ6 ወራት የሚቆይ ጭማሪ እንዲደረግ አዘዋል።

የሰራተኞች ማህበር ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከያዙበት ሰኔ ወር ጀምሮ እያሻቀበ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም ወርሃዊ ደመወዝ ወደ 255 ዶላር እንዲያድግ ሲጠይቁ ቆይተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ያደረጉት ጭማሪ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ላይ ብቻ የሚያተኩር ሲሆን ከ32 ዶላር ወደ 70 ከፍ እንዲል አድርገዋል።

በተጨማሪም በሀገሪቱ የሶስት እጥፍ ጭማሪ ያሳየውን የነዳጅ ዋጋ ለመቀነስ ዝቅተኛ ዋጋ በሚፈልግ ነዳጅ የሚንቀሳቀሱ አውቶብሶችን ወደ ስራ ለማስገባትም ቀል ገብተዋል።

በሀገሪቱ የነዳጅ ዋጋ ያሸቀበው ፕሬዝዳንት ቲንቡ ለአስርት ዓመታት በናይጄሪያ የነበረውን የነደጅ ድጎማ ካነሱ በኋላ ነው።

በተጨማሪም በሰኔ ወር ሀገሪቱ በነጻ ንግድ እንድትሳተፍ የሚያደርገውን የገንዘብ ፖሊስ ከሻሩ በኋላ በሀገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ናይራ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ማሽቆልቆል ተመዝግቧል።

እነዚህ ውሳኔዎች ቀድሞው ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ምርቶች ምክንያት ከከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን እየተጋፈጡ ለነበሩት ናይጄሪያውያን ህይወትን አስቸጋሪ አድርጎባቸዋል።

ናይጀሪያ ከዩናይትድ ኪንግደም ቅኝ ግዛት ነጻ የወጣችበትን 63ኛ ዓመት አስመልክቶ የተቀረጸ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ ዜጎች አሁን ያለውን የኢኮኖሚ ችግር ለመቋቋም ያስችላቸዋል ያሉትና የሚወሰዱ እርምጃዎችን ይፋ አድርገዋል።

ፕሬዝዳንት እያከናወኑት ያሉት ማሻሻያ አሰቸጋሪ ቢሆንም መንግሥት እየሰጠ ከነበረው የነደጃ ድጎማ ቢሊዮኖችን በመቆጠብ ወደ የተፈጥሯዊ ጋዝ ወደሚጠቀም የአውቶብስ ስርዓት ማተኮሩ ጠቃሚ እንደሆኑ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ የናይጄሪያ ዋነኛው ሁለት የሰራተኛ ማህበራት የጊዜ ገደብ ያልተቀመጠለትን የስራማ ማቆም አድማቸውን የማድረግ ዕቅዳቸውን እንዳልሰረዙት አስተውቀዋል።

የማህበራቱ መሪዎች መንግሥት የነዳጅ ድጎማን በማንሳቱ ምንክንያት ዜጎች እየተፈተኑበትን ያለውን ችግር ለመፍታት አልቻለም ብለዋል።

የሰራተኛ ማህበራቱ የያዙትን ዕቅድ እንዲያቆሙና ለድርድር ጊዜ እንዲሰጡ መንግስት ተማጽኖ ነበር።