በኬንያ 'የፀጥታ ኃይሎች' ተይዞ ለሁለት ዓመታት ደብዛው የጠፋው ኢትዮጵያዊ ሳምሶን ተክለሚካኤል

ከሁለት ዓመት በፊት በኬንያ መዲና ናይሮቢ ውስጥ “በፀጥታ ኃይሎች” ከመንገድ ላይ ተይዞ የተወሰደው ኢትዮጵያዊው ሳምሶን ተክለሚካኤል አስካሁን ደብዛው እንደጠፋ ነው።

ባለቤቱ ሚለን ኃለፎም እስካሁን ድረስ ባለቤቷ የት እንዳለ የሰማችውም ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግራለች።

ሁለት ዓመት ሙሉ የባለቤቷን መገኛ ለማወቅ በኬንያ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ላይ ታች የምትለው ሚለን “ሳሚን የመፈለጉ መንገድ እየረዘመ፣ እያደከመኝ ቢሄድም ተስፋ አልቆርጥም” ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች።