የማንችስተር ሲቲው ተከላካይ ሜንዲ በሁለት ተጨማሪ የመድፈር ወንጀሎች ተከሰሰ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የማንችስተር ሲቲው ተከላካይ ቤንጃሚን ሜንዲ በሁለት ተጨማሪ የመድፈር ወንጀሎች ተከሷል።
ሜንዲ ረቡዕ በስቶክፖርት ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ይጠበቃል።
በእስር ላይ የሚገኘው የ27 ዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች ስድስት የመድፈር እና አንድ የወሲብ ጥቃት ክስ ቀርቦበታል።
ክሶቹ ከ16 አመት በላይ በሆናቸው አራት ቅሬታ አቅራቢዎች የተመሰረተበት ሲሆን ጥቃቶች በእአአ 2020 እና 2021 መካከል የተፈጸሙ ናቸው ተብሏል።
ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል ያለፈው የውድድር ዘመን የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ለሆነው ማንችስተር ሲቲ ከ2017 ጀምሮ ተጫውቷል። ከሞናኮ በ52 ሚሊዮን ፓውንድ ነበር ሲቲን የተቀላቀለው።
ሜንዲ ክስ ተመስርቶበት ምርመራ እስኪደረግ ድረስም በክለቡ ታግዷል።
የሜንዲ ጓደኛ ነው የተባ ሉዊስ ሳሃ ማቱሪ በተመሳሳይ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ከተፈጸመ ወሲባዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ በአራት የመድፈር ወንጀል ተከሷል።
የ40 አመቱ ግለሰብ በሁለት ተጨማሪ የመድፈር እና የጾታዊ ጥቃት ተከሶ ፍርድ ቤት ይቀርባል።
ሁለቱም ጥር 24 ቀን 2022 ችሎት ፊት ይቀርባሉ።












