የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ41 ዓመታት በኋላ ወደ ሶማሊያ በረራ ጀመረ

ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ ሰንደቅ አላማ የተሰራ ኬክ
የምስሉ መግለጫ, ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ ሰንደቅ አላማ የተሰራ ኬክ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ41 ዓመታት በኋላ ወደ ሶማሊያ በረራ አድርጎ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ አረፈ።

በቦይንግ 737 የተደረገው በረራ የተመራው በሴት አውሮፕላን አብራሪ ሲሆን፤ 50 ሰዎችን አሳፍሮ ነበር።

አውሮፕላኑ ሞቃዲሾ የደረሰው ከአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ሁለት ሰአት ገደማ ከበረረ በኋላ ነበር። ከተሳፋሪዎቹ መካከል በኢትዮጵያ የሶማሊያ ኤምባሲ ፈርስት ካውንስለር አቶ አብዱላሂ መሀመድ ዋርፋ ይገኙበታል።

አቶ አብዱላሂ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በረራው መጀመሩ የሁለቱን ሀገሮች የንግድ ግንኙነት ያጠናክራል።

አውሮፕላኑ ከአዲስ አበባ ሲነሳ፣ በበረራው እኩሌታ እንዲሁም ሞቃዲሾ ካረፈ በኋላ ልዩ ልዩ መሰናዶዎች ተካሂደዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሶማሊያ በረራ ማድረግ ያቋረጠው እንደ አውሮፓውያኑ በ1970ዎቹ በሁለቱ ሀገሮች የድንበር ግጭት ከተከሰተ በኋላ ነበር።

በአሁን ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሶማሊያው ፕሬዘዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆና ከኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ይገኛሉ።

የኬክ ቆረጣ ስነ ስርዓት ተካሂዷል

የፎቶው ባለመብት, OMAR FARUK OSMAN

የምስሉ መግለጫ, የኬክ ቆረጣ ስነ ስርዓት ተካሂዷል
ጋዜጠኞች ተገኝተው ነበር

የፎቶው ባለመብት, Omar Faruk Osman

የምስሉ መግለጫ, ጋዜጠኞች ተገኝተው ነበር
አቶ አብዱላሂ መሀመድ ዋርፋ

የፎቶው ባለመብት, Omar Faruk Osman

የምስሉ መግለጫ, አቶ አብዱላሂ መሀመድ ዋርፋ
አውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ
የምስሉ መግለጫ, አውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ
የሶማሊያ ባህላዊ ሙዚቃ ቀርቧል

የፎቶው ባለመብት, Omar Faruk Osman

የምስሉ መግለጫ, የሶማሊያ ባህላዊ ሙዚቃ ቀርቧል