ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ድመቶች ዝር የማይሉበት የኒውዚላንድ መንደር
በኒውዚላንድ የምትገኝ ኦማዊ የተሰኘች አንድ መንድር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ድመት የሚባል ነገር እንዳናይ ሲሉ ተደምጠዋል።
የመንደሪቱን ከባቢያዊ ሁኔታ የሚቆጣጠር አንድ ድርጅት ድመቶች ወደ መንደሪቱ እንዳይገቡ የሚል ሃሳብ ያመጣው የዱር አራዊትን ለመጠቅ በሚል ነው።
ድመት ያላቸው የመንደሪቱ ነዋሪዎች ድመቶቹ ሕይወታቸው እስኪያልፍ ድረስ እንዲያኖሯቸው ከዚያ በኋላ ግን ማሳደግ እንደማይችሉ ተደንግጓል።
ነዋሪዎቹ ድመቶች ለበርካታ የዱር እንስሳት ሕይወት መጥፋት በተለይ ደግሞ ለአእዋፍ፤ ተጠያቂ ናቸው በሚለው ሃሳብ የተስማሙ ይመስላሉ።
በአካባቢው የሚገኝ አንድ የአእዋፋት ማቆያ ሥፍራ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ፒት ማራ «ምንም እንኳ ከድመቶች ጋር ፀብ ባይኖረንም ያሰብነውን ለማሳካት እነሱን ማስወገድ ዋነኛ መፍትሄ ነው» ይላሉ።
«ድመቶች የፈለጉበት ውለው መምጣት ይችላሉ፤ ውሾች ግን ከክልላቸው ንቅንቅ አይሉም። አሁን ጊዜው ድመቶችን እንደ ውሾች የምናይበት ነው።»
ውሳኔው የተላለፈባቸው ድመቶች እየተዘዋወሩ የዱር እንስሳትን ሲያድኑ በካሜራ እይታ ውስጥ ገብተዋል።
ሕጉን አንክተልም የሚሉ ነዋሪዎች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንዲደርሳቸው ለጥቆም ድመቶቹ እንዲወገዱ እንደሚደረግ ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ።
ድመቶች ለዱር አራዊት ፀር ናቸው የሚለው ሃሳብ አከራካሪነቱ እንደቀጠለ ነው፤ የኒውዚላንዷ መንደርም ድመቶችን በማስወገድ የመጀመሪያዋ አይደለችም።
የዱር ሕይወት አጥኚዎች ዓለም ላይ አድጋ ተጋርጦባቸው ላሉ የአእዋፍ ዝርያዎች ድመቶች ተጠያቂ ናቸው ይላሉ።
በተለይ ደግሞ እንደ ኒውዚላንድ ባሉ የዱር እንስሳት ከሰው ጋር ተደባልቀው በሚኖሩባቸው ሃገራት።
«ጥፋቱ እኮ የድመቶቹ አይደለም፤ የአሳዳገዎች እንጂ» የዶክትር ማራ ሃሳብ ነው። «ድመቶች አዳኝ ሆነው እንዲያድጉ የምናሳድጋቸው እኛው ሰዎች ነን።»
ድመቶች በሰው ዘንድ ያላቸው ተወዳጅነት ጉዳይን ከበድ እንዲያደርገው ግን አልሸሸጉም።
ምንም እንኳ ትክክለኛውን ቁጥር ማስቀመጥ አዳጋች ቢሆንም በአሜሪካ ብቻ 86 ሚሊዮን ገደማ የቤት ድመቶ ች አሉ።