Unit 2: Essential English Conversation
Select a unit
- 1Essential English Conversation
- 2Essential English Conversation
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
Session 46
Listen to find out how to start making arrangements.
ውጥኖችን ወይንም ዕቅዶችን እንዴት መጀመር እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Activity 1
Are you free later?
Listen to find out how to start making arrangements.
ውጥኖችን ወይንም ዕቅዶችን እንዴት መጀመር እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይመልሱ።

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን። ሁሉም የእንግሊዝኛ ተማሪ ማወቅ ያለበትን የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ምህረተስላሴ እባላለሁ። በዚህ ክፍል ስለ ዕቅድ እና አንዳች ነገር ለማከናወን ሁኔታዎችን ስለማመቻቸት እንዴት ማውራት እንደሚቻል ይማራሉ።
ሁለት ጓደኛሞች ስለ እቅዶቻቸው እያወሩ ነው። ሁለተኛዋ ተናጋሪ ወዴት እንደምትሄድ ያዳምጡ።
Chris
What are you doing today?
Penny
I'm going to the market.
Chris
Are you free later?
Penny
Yes, let's do something!
ምህረተስላሴ
ንግግሩን ካልተረዱት አይጨነቁ። ውይይቱን እንከፋፍለውና ደግመው እንዲሉት ጊዜ እንሰጥዎታለን።
ክሪስ ፔኒን ዛሬ ምን እንደምታደርግ ጠየቃት።
What are you doing today?
ምህረተስላሴ
የወደፊት ጊዜን ለመጠቆም እንደ 'this evening' እና 'tonight' ያሉ ጊዜ ገላጭ ቃላትን በአረፍተ ነገር መጨረሻ ላይ መጠቀምም ይችላሉ።
What are you doing this evening?
What are you doing tonight?
What are you doing tomorrow?
ምህረተስላሴ
ፔኒ ወደ ገበያ እንደምትሄድ ተናግራለች። መሄድ ያቀድንበትን ቦታ ለመግለፅ 'I'm going to'ን እንጠቀማለን።
I'm going to the market.
ምህረተስላሴ
ወደ ሱቆች 'the shops'፥ ወደ ባህር ዳርቻ 'beach' ወይም ወደትምህርት ቤት 'to school'. እሄዳለሁ ማለትም እንችላለን።
I'm going to the shops.
I'm going to the beach.
I'm going to school.
ምህረተስላሴ
ከዚያም ክሪስ ፔኒን ኋላ ላይ መገናኘት ይችሉ እንደሆነ 'Are you free later?' ሲል ጠየቃት።
Are you free later?
ምህረተስላሴ
ፔኒ 'yes' አዎ ስትል በአዎንታ መለሰች። ጠቆም ለማድረግ 'let's' ብላ ጀመረች። ተገናኝተው አንዳች ነገር እንዲያደርጉ 'do something' አለች። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Yes, let's do something!
ምህረተስላሴ
ትርፍ ጊዜ ከሌለዎት በትህትና 'sorry' በማለት አሉታዊ መልስ መስጠት ይችላሉ።
No, sorry, I'm not free later.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ። አሁን ሶፊያ እና ፖል ነገ ምን እንደሚያደርጉ ሲነጋገሩ ያዳምጡ። ፖል ምን ያደርጋል?
Sophie
What are you doing tomorrow?
Paul
I'm working all day.
Sophie
Me, too.
ምህረተስላሴ
ፖል ስለሚያደርገው ነገር እያወራ ነው። 'I'm' ካለ በኋላ 'work' የሚለው ቃል ላይ '-ing' ጨምሮበታል። 'Meet' መገናኘት ወይም 'visit' መጎብኘት የመሳሰሉ ድርጊት ገላጮች መጠቀምም ይችላሉ።
I'm meeting my friend.
I'm visiting my friend.
ምህረተስላሴ
እሺ፤ እስኪ በድጋሚ እንሞክረው። እንግሊዝኛውን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
What are you doing today?
I'm going to the market.
Are you free later?
Yes, let's do something!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ። አሁን የምትለማመዱበት ጊዜ ነው። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ አዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን በሉ።ምን ያህል ታስታውሱ ይሆን?
ዛሬምንታደርጊያለሽ?
What are you doing today?
ገበያእሄዳለሁ።
I'm going to the market.
ኋላላይነፃነሽ?
Are you free later?
አዎ።እስኪየሆነነገርእናድርግ።
Yes, let's do something!
ምህረተስላሴ
ግሩም። ስለወደፊት ውጥኖችዎ እንዴት መናገር እንደሚችሉ ተምረዋል። ለክሪስ ወደ ገበያ እንደሚሄዱ በመናገር ይለማመዱ። ከዚያም አንዳች ነገር ስለማድረግ ይጠቁሙ።
What are you doing today?
Are you free later?
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሙሉውን ውይይት ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Chris
What are you doing today?
Penny
I'm going to the market.
Chris
Are you free later?
Penny
Yes, let's do something!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ። ስለወደፊት ውጥኖችዎ በእንግሊዝኛ ማውራት ችለዋል። ለምን ከጓደኛዎ ጋር የተማሩትን አይለማመዱም? አብረውን ስለቆዩ እናመሰግናለን። ለተጨማሪ Essential English በሚቀጥለው ዝግጅታችን ይጠብቁን።
Check what you’ve learned by putting the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል በማስቀመጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
በኋላ ትርፍ ሰዓት ይኖርሻል/ ይኖርሀል?
3 Questions
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ኣመት
ጥያቄ ለማቅረብ የምንጠቀምበትን የቃላት ቅደም ተከተል ያስታውሱ።Question 1 of 3
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ኣመት
የመጨረሻው ቃል ቦታ ነው።Question 2 of 3
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ኣመት
ጥያቄ ስንጠየቅ ከ 'are' በኋላ የምንጠቀመው ቃል የቱ ነው?Question 3 of 3
Excellent!Great job!ሕማቕ ዕድል!ዘመዝገብኩምዎ ነጥቢ ...:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ ኢሴንሻል ኢንግሊሽ መሰናዷችን ይጠብቁን።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
What are you doing today?
ዛሬ ምን ታደርጊያለሽ?
this evening
ዛሬ ምሽት
tonight
ዛሬ ማታ
tomorrow
ነገ
Are you free later?
በኋላ ትርፍ ጊዜ ይኖርሻል?
I’m going to (the market).
ወደ (ገበያ) እሄዳለሁ
I’m meeting my friend.
ጓደኛዬን አገኛለሁ
I’m working all day.
ቀኑን ሙሉ ስራ አለኝ